ግእዝ ክፍል 12 መልስና ማብራርያ ለመመዘኛ ጥያቄ አንድ
በዛሬው በክፍል 12 ዝግጅታችን ባለፈው ከአሥራ
አምስት ቀናት በፊት ማለት ነው የሰጠኋችሁን “ክፍል 11 የመመዘኛ ፈተና አንድ” ለሚለውን ክፍል አንድ የመመዘኛ ፈተና ሙሉ መልስና
ማብራርያ እሰጣለሁ እባካችሁ በሚገባ ተከታተሉ። እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን።
ወደ ትምህርቱ ከመግባቴ በፊት ስለፈተናው የወሰድኩትን
ግንዛቤ ላካፍላችሁ እወዳለሁ። ምክንያቱም የጎደለ ካለ ለወደፊቱ ማስተካከል እንድንቺል ማለት ነው።
1. ፈተናውን ሠርጎ የመለሰው የሰው ብዛት እንደ
ጠበቅሁት አይደለም የሚማረው ወይም ትምህርቱን የሚከታተለው ሕዝብ ብዛት ፈተናውን ከሠራችሁት እንደሚበልጥ በምንም አይነት መልኩ
አልጠራጠርም። ሆኖም ግን ለምን ፈተናውን መሞከር እንዳልፈለጋችሁ ባላውቅም ለወደፊቱ ብትሞክሩ እጅግ ጠቃሚ ነው በማለት እንደተለመደው
ሳላስታውሳችሁ አላልፍም።
2. መልሱን በወቅቱ ሠርታችሁ የመለሳችሁትን ሁሉ
በጣም ላደንቃችሁ እፈልጋለሁ በእውነቱ የሚያረካ ውጤት ነው ያየሁት። ለወደፊቱም በዚሁ ቀጥሉ። የግ እዝን ቋንቋ ማወቅ ምን ያህል
ጠቃሚና የኑሮ ብርሃን መሆኑን ለወደፊቱ ነው በደንብ የምትገነዘቡት ስታውቁት ማለት ነው።
3. ፈተናውን የሠሩ ተማሪዎች ስምንት ሲሆኑ ከስምንቱ
ውስጥ
ሁለት
ሰዎች 100/100
ሦስት
ሰዎች 90/100
ሁለት
ሰዎች 80/100
አንድ
ሰው 50/100 አግኝተዋል። በመሆኑም ሁሉም ፈተናውን አልፈዋል ማለት ነው። እንኳን ደስ ያላችሁ። እላለሁ።
የግእዝ
ትምህርት ክፍል 11 (አሥራ አንድ) የመመዘኛ ፈተና አንድ መልስ
መልስና ማብራርያ።
ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ የጥያቄውን ቍጥር እና የመልሱን
ፊደል በኮሜንት ቦታ እንደሚከተለው ያስቀምጡ
ምሳሌ አንድ::
1. “ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኃበ
እግዚአብሔር”.። ለዚህ
ዐረፍተ ነገር የሚስማማው መራሒ ወይም የስም ተለዋጭ የትኛው ነው?
A. ውእቱ
B. ይእቲ
C. አነ
የተውላጠ ስም ጥያቄ
ኢትዮጵያ ባለቤት
ታበጽሕ ማሠሪያ
እደዊሃ ቀጥተኛ ተሳቢ(የአብጽሐ ተሳቢ)
ሃ የባለቤት ዝርዝር (ባለቤትነትን የሚያመለክት)
ኀበ =ወደ አገባብ
እግዚአብሔር አገባብ የወደቀበት
ምሳሌ ሁለት፡
2. “አነ ውእቱ ብርሃኑ ለዓለም”።
የዚህ ዐረፍተ ነገር ባለቤት
ወይም የሥም ተለዋጭ ----ይባላል።
A. 1ኛ መደብ ነጠላ
B. 2ኛ መደብ ብዙ ለሴቶች
C. 3ኛ መደብ ነጠላ ቁጥር
ርማት
(አነ ለነጠላ ቁጥር ለሴትም ለወንድም ይሆናል ስለዚህ ለተባእታይ ፆታ የሚለው ይታረም
የተውላጠ
ስም ፣ የባለቤትነት እና የመደብ ጥያቄ
ኑ=
ባለቤትነትን የሚያመለክት
ለ=የ
ሁል
ጊዜም ዝርዝር (የባለቤት አመልካች) ካለ ቀጥሎ ለ የሚል ፊደል ይኖራል።
(ብርሃኑ
በአታ
ልደታ
ፍልሰታ)
This is comment area under
youtube video
Q.1.
A. B.
Q.2.
A. A.
ከዚህ በላይ ለምሳሌነት የተሰጡት መልሶች ሲተነተኑ
ለጥያቄ አንድ መልሱ B.;
ለጥያቄ ሁለት ደግሞ መልሱ
A. ነው ማለት ይሆናል።
ትክክለኛውን መልስ
በመምረጥ የጥያቄውን ቍጥር እና የመልሱን ፊደል በኮሜንት ቦታ ያስቀምጡ
1.
ጳውሎስ ሆረ ኀበ አቴና። የዚህ
ዐረፍተ ነገር ተውላጠ ስም የትኛው ነው?
A.
ውእቱ
B.
ውእቶሙ
C.
አንተ
ሆረ=ሄደ
ኀበ= ወደ
2.
አቤል ----በእደ ቃኤል።
ለዚህ ዐረፍተ ነገር የሚስማማው አንቀጽ
A.
ቀተለ
B.
ተቀትለ
C.
አቅተለ
እድ የሚለው
ቃል ከሚቀጥለው ቃል ጋር ለመያያዝ ወደ ግእዝ ፊደል መቀየር አለበት
ሳድስ ወደ ግእዝ
ለምሳሌ፡ ገብረ ማርያም፤ ወለተ ማርያም፤ ኃይለ ሚካኤል
ሳልስ ወድ ሐምስ
ምሳሌ፡ ጸሐፊ የሚለው =ጸሐፌ ትእዛዝ ይሆናል ከት እዛዝ ጋር ለማያያዝ
This is passive voice
Abel was killed by Cain
3.
አርድእተ ግእዝ አእመሩ ሰዋስወ ግእዝ። የዚህ ዐረፍተ ነገር ባለቤት
A.
1ኛ መደብ ብዙ ተባእታይ
B.
2ኛ መደብ ነጠላ
C.
3ኛ መደብ
ብዙ ተባእታይ
4.
አእማድ ማለት ምን ማለት ነው?
አእማድ የሚባሉትስ ስንት ናቸው?
A.
መሪዎች፤ 5
B.
ምሰሶዎች፤ 10
C.
ምሰሶዎች፤
5
አምድ ማለት ለአንድ አእማድ ለብዙ
አድራጊ
አስደራጊ
አደራራጊ
ተደራጊ
ተደራራጊ
5.
አንቲ---ተስፋሁ ለአዳም አመ
ይሰደድ እም ገነት። በተማርነው መሠረት ለዚህ ዐረፍተ ነገር የሚስማማው ነባር ግሥ የቱ ነው?
A.
ውእቶሙ
B.
ውእቱ
C.
ውእቶን
ውእቱ እንደ ነባር ግሥ ሲሆን
ዝንቱ ውእቱ
አንቲ ውእቱ
አንተ ውእቱ
አነ ውእቱ
ንሕነ ውእቱ
አንትሙ ውእቱ
አንትን ውእቱ እንዲሁም ነበረ፣ ነብረሽ፤ነብርህ፤ነበርኩ፤ነብርን፤ነበራችሁ ወዘተ ይሆናል።
6.
አበይት አናቅጽ ወይም ታላላቅ ግሦች ወይም አናቅጽ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?
A.
ሃላፊ፤ ትንቢት፤
ዘንድ፤ እና ትእዛዝ
B.
ቅጽል፤ነባር፤ እና ግሥ
C.
አእማድና መራሕያን
አንቀጸ ማለት ማሠሪያ ወይም
ግሥ ማለት ነው።
ለምሳሌ ሆረ የሚለው ግሥ አበይት አናቅጽ
ሆረ=ሃላፊ አንቀጽ (ሄደ)
የሀውር=ትንቢት አንቀጽ(ይሄዳል)
ይሁር=ዘንድ አንቀጽ (ይሄድ ዘንድ)
ይሁር=ት እዛዝ አንቀጽ (ይህድ)
የሚሉት ናቸው።
7.
አነ ውእቱ ። ማለት ---ማለት ነው ወይም ይሆናል ።
A.
እኔ ነኝ
B.
እሷ ናት
C.
እኛ ነን
በዚህ ዐረፍተ ነገር ውእቱ ተውላጠ ስም ሳይሆን ግሥ(ነባር) ግሥ ነው። አነ የሚልው ደግሞ ተውላጠ ስም ነው።
ይህ ዐረፍተ ነገር ባለቤትና ማሠሪያ አንቀጽ ብቻ አለው። አንድ አረፍተ ነገር ቢያንስ
ባለቤትና ማሠሪያ አንቀጽ ሊኖረው
ይገባል።
8.
አበበ ወገብረ ማርያም ሐተቱ መጻሕፍተ። ለሚለው ዐረፍተ ነገር የሚስማማው ተውላጠ ስም
ወይም የስም ተለዋጭ የትኛው ነው?
A.
ንሕነ
B.
ውእቶን
C.
ውእቶሙ
አበበ እና ገብረ ማርያም ሁለት ሰዎች ስለሆኑ ብዙ ቁጥርን(ከአንድ በላይ)
የሆኑ ክፍሎችን የሚወክል ተውላጠ ስም ያስፈልጋቸዋል። ይህ ማለት
ውእቶሙ ሐተቱ መጻሕፍተ ማለት ነው።
ወ=And
9.
መርድአ ግእዝ ጸሐፈ መጽሐፈ።
የዚህን ዐረፍተ ነገር ባለቤት፤ ማሠሪያ
አንቀጽ፤ እና ቀጥተኛ
ተሳቢ የያዘውን የመልስ ሆሄ በመምረጥ መልስ ይስጡ።
A.
መርድእ፤ ጸሐፈ፤
መጽሐፍ(መርድአ፤ጸሐፈ፤ መጽሐፈ)
B.
ግእዝ፤ ጸሐፈ፤ ሰዋስው፤
C.
መርድእ፤ መጽሐፍ፤ ግእዝ፤
መርድእ ማለት ተማሪ ማለት ሲሆን ግእዝ ከሚለው ቃል ጋር ለማናበብ ወይም ለማያያዝ
እ የሚለው ሳድስ ሆሄ
ወደ ግእዝ ሆሄ ወደ አ ይቀየራል
ወይም ተቀይሯል። (ተማሪው የምን ተማሪ መሆኑን ለመግለጽ ማለት ነው)
10.
ገብረ ማርያም ቀደሰ ቅዳሴ
ሐዋርያት። በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ በአገባብ ትንታኔ ትምህርታችን መሠረት “ሐዋርያት”
የሚለው ቃል ወይም ስም ሙያው ምን ይባላል?
A.
የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት
B.
ማሠሪያ አንቀጽ
C.
የቅዳሴ ዘርፍ
እግዚአብሔር ይክስት ለክሙ ምሥጢረ ወየሐብክሙ ዘትትናገሩ
እግዚአብሔር ምሥጢርን ይግለጽላችሁ ፤ የምትናገሩትን ወይም የምትመልሱትንም
(መልስ) ይስጣችሁ፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር =ለእግዚአብሔር ምስጋና
ይሁን
አሜን=ይሁን ይደረግ (እንደ ተባለው ይደረግ)
አዘጋጅና አቅራቢ “አውደ ጥናት”