Sunday, February 2, 2020

አስተርዕዮታ ለማርያም ድንግል

አስተርዕዮታ ለማርያም ድንግል


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አምላካችን እግዚአብሔር በሰላም እና በጤና ጠብቆ ከዕድሜያችን ተጨማሪ የሆነችውን ይህችን ልዩ ዕለት ያለ ምንም ዋጋ በነፃ በመስጠት የእናቱን እና የእናታችንን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የዕረፍቷን መታሰቢያ በአል እንድናከብር ስለፈቀደ የተመሰገነ ነው። አሁንም በተለመደው ቸርነቱ የንስሐ ዕድሜን ጨምሮልን ለሚቀጥለው ዓመት በሕይወት አቆይቶን ይህንን በአል ለማሰብ እና ለማክበር ያብቃን አሜን።


በመግቢያችን እንዳየነው አስተርዕዮታ ለማርያም እያልን በየዓመቱ ጥር 21 ቀን የምናስበው በአል የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የዕረፍት ወይም ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ የተለየችበትን በአል ነው።

አዎ! በሥነ ፍጥረት ታሪክ አቻ ወይም አምሳያ ያልተገኘላት፥ ከምድራውያን ሰዎችም ሆነ ከሰማያውያን መላእክት የሚመስላት የሌለ፣ በፍጡር ሕሊና ሊመረመር በማይችል ምሥጢር ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ሕያው አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ፀንሣ የወለደች፣ ያሳደገችም ልዩ ፍጥረት እንደ ማነኛውም ፍጡር በሞተ ሥጋ ተለየች ማለት ለሰዎች አእምሮ ይከብዳል። ለዚህም ነው ታላቁ የዜማ ደራሲ ቅዱስ ያሬድ በሁኔታው እየተደነቀ “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም ያአጽብ ለኵሉ”

= ለሚሞት ሞት ይገባል፤ ነገር ግን የማርያም ሞት ሁሉን ያስደንቃል(ያስገርማል)  በማለት ለማነኛውም ሰብአዊ ታሪክ ላለው፣ ሞት ያለ፤ የነበረና የሚኖር ስለሆነ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን የተለየና በተፈጥሮ ታሪክ ሊፈጸም የማይችል ታሪክ ለተሰጣት ለእመቤታችን የሆነው ሞት አስደናቂ የሆነበት።

ምክንያቱም፡ ለእመቤታችን የተሰጠው ለማንም ፍጡር አልተሰጠም፤ የእሷን ዓይነት ምርጫ የተመረጠ የለም፤ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ታሪክ ያላት፤ ዓለም ከተፈጠረም በኋላ ከመወለዷ በፊት ምርጫዋ የተሰበከላት፤ ስለ እርሷ ያልተነበየ ነቢይ የሌለ፤ ለሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመናት የሕሊና ተስፋ የሆነች፤ አሁንም በአማላጅነቷ ዓለም የሚማፀናት ልዩ ፍጥረት፤
ዓለምን ለማዳን ኃያሉን አምላክ በድንግልና ጸንሣ በድንግልና እንደምትወልድ አዲስ እና ለዓለም እንግዳ የሆነ፣ በሥነ ተፈጥሮ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ፣ የተፈጥሮን ሕግ የጣሰ ታሪክ በነቢያትና በመላእክት የተነገረላት፤
የትንቢቱ ፍጻሜ በተቃረበ ጊዜ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የሚያበሥር መልአክ ወደሷ የተላከላት፤ ዓለም የሚጠባበቀው የድኅነት ሥራ በእርሷ እናትነት እንደሚፈጸም በግልጽ ያበሠራት።

ታዲያ ሁሉን ማድረግ የሚቻለው፣ የሚሆነውን እንዳይሆን፣ የማይሆነውን እንዲሆን ወይም የሚቻለውን የማይቻል፤ የማይቻለውን የሚቻል የሚያደርገውን፤ ለሚያደርገው ሁሉ ለምን በማለት ማንም የማይጠይቀውን ሁሉን ቻይ አምላክ ለወለደች እናት እንዴት ሞት ተገባት? ሲል ነበር ቅዱስ ያሬድ “ያስደንቃል፤ያስገርማል” በማለት የገለጸው። እውነትም ያስገርማል!

በሰብአዊ ባሕል ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ከኀዘን ቀጥሎ የሚደረግለት ነገር ቢኖር ከልደት እስከ ሕልፈት ያሳለፈውን ምድራዊ ታሪክ መተረክ ነው። ታዲያ የእመቤታችን የዕረፍት ታሪክ ከልደቷ ወይስ ከወላጆቿ  ከቅዱስ ኢያቄምና ከቅድስት ሐና ልደት! ከየት ነው መጀመር ያለብን?
ምክንያቱም፣ የእመቤታችን ታሪክ ከታሪክ በፊት ነው። ዓለም ከመፈጠሩ፣ ጊዜ ከመቆጠሩ በፊት፤ ዓለም የራሱን ታሪክ ከመጀመሩ በፊት እመቤታችን አስደናቂ ታሪክ ነበራት፤ ታዲያ ከየት ይጀመር? ያዐፅብ ለኵሉ” እውነትም ያስደንቃል።

ታሪኳ ልዩ፣ ምርጫዋ አስደናቂ፣ ከፍጡራን ሕሊና በላይ ቢሆንም “እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ” ብለን በማለፍ የእኛ ሕሊና በሚችለው መጠን በሚገባን እና በገባን ደረጃ መጻሕፍት የሚነግሩንን ታሪክ መናገራችን ግድ ነው። ለዚህም ነው ቅዱሳን አባቶች ለእመቤታችን ሰብእና ምሳሌ ስላጡለት “በመኑ ወበአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ” = በማን እና በምንስ እንመስልሻለን” በማለት የሚናገሩ።

ስለዚህ የእመቤታችንን ታሪክ ግልጽና ቀላል ለማድረግ በ 3 ዐበይት ክፍሎች ከፋፍየ ባጭሩ ለማስረዳት እሞክራለሁ ። ምክንያቱም ረጅሙን የእመቤታችንን ታሪክ ተርኮ መጨረስ የሚችል ማንም የለም፣ ቅዱሳንም አልጨረሱትም። በመሆኑም እኔም አልሞክረውም።

የመጀመሪያውን የታሪክ ክፍል

“እግዝእትነ ማርያም ነበረት እምቅድመ ዓለም በሕሊና አምላክ” የሚለው ዐረፍተ ነገር ይገልጸዋል ይህ ጽሁፍ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፎ ይገኛል። ቃሉ ወደ አማርኛ ሲተረጎም እመቤታችን ከዓለም በፊት በአምላክ ሕሊና ወይም ሐሳብ ውስጥ ነበረች ማለት ነው።

ዓለም ማለት ቃሉ ግእዝ ሲሆን በቀጥተኛ አማርኛ ፍጥረት ማለት ነው፤ ስለዚህ ከሥነ ፍጥረት በፊት ማለትም አዳም ተፈጥሮ በድሎ በኃጢአት ከመውደቁ በፊት እመቤታችን በአምላክ ሐሣብ ለድኅነተ  ዓለም ለሥጋዌው ተመርጣ ነበር ማለት ነው።
ይህ ምሥጢር በሰዎች አእምሮ በእኛ አቅም የሚመዘን ከሆነ መቸም ቢሆን ሊገባን አይችልም፤ በመሆኑም የሚመዘነው ሁሉን ማድረግ በሚችለው ለሚያደርገው ሁሉ ለምን? ብሎ ጠያቂ በሌለው ልዑል አምላክ አቅም ብቻ ነው። “እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ” የሚሳነው ነገር የለም።

እነ ነቢዩ አርምያስ፣ ኢሳይያስ መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎችም ቅዱሳን ገና ሳይወለዱ በእናታቸው ማሕፀን እግዚአብሔር መርጧቸዋል። አንዱን ብቻ ለመጥቀስ ያህል ነቢዩ ኢሳይያስ በ49ኛው ምዕራፍ አምላኩ አስቀድሞ እንዴት እንደመረጠው  “እም ከርሠ እምየ ሰመየኒ ስምየ፣ ወረሰዮ ለአፉየ ከመ መላፂ በልህ፣ ወከደነኒ ታሕተ ጽላሎተ እዴሁ” = በእናቴ ማኅፀን ስሜን ኢሳይያስ ብሎ ሰየመኝ፣ አንደበቴን እንደ ተሳለ ምላጭ አደረገው(አንደበተ ርቱዕ አደረገኝ) በእጁ ጥላ ሥርም ጠበቀኝ ። በማለት ይገልጸዋል።
ታዲያ ከነቢያት የምትበልጥ ከመላእክትም የምትልቅ ቅድስተ ቅዱሳን የአምላክ እናት በፈጠራትና ለታላቅ የሥጋዌው ምሥጢር ባቀዳት በአምላኳ ከዓለም በፊት መመረጧ ምን ያስደንቃል። ምንም የሚያስደንቅ የሚያስገርም ነገር የለም ምክንያቱም በአምላክ እቅድ የተለየ ክብር የተሰጣት የተለየች ፍጡር ናት፤ የተለየ ነገር በእርሷ ብቻ መታየቱ የአምላክ ልዩ ጥበብ ነው።

ሁለተኛው የታሪክ ክፍል

“በሐሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእትቤዘወከ በመስቀልየ ወበሞትየ” የሚለው ቃል ኪዳን ወይም ዐረፍተ ነገር ይገልጸዋል።  ሁለተኛው የታሪክ ክፍል ዓለም ከተፈጠረ በኋላ  በቅዱሳን ነቢያት አንደበት በሰፊው የተተረከ የታሪክ ክፍል ነው። አዳም በደለ በደሉም የሞት ዋጋን የሚያስከፍል ነበረ፤ የዚህ ዕዳ ተካፋይም አዳም በደሎ ሞት ሳይፈረድበት በፊት በአምላክ ሕሊና ከነበረቺው ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በስተቀር ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ነበር።

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከወላጆቻችን ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ በወላጆቹ በደል የሞተው ዓለም በአምላክ ሕሊና ለድኅነተ ዓለም አምላክ ለሥጋዌው የመረጣትን የቅድስተ ቅዱሳንን መወለድ በተስፋ ይጠባበቅ ነበር።

“አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት” = በሠራው ኃጢአት ምክንያት ከገነት በተባረረ ጊዜ እንደ ገና ወደ ክብሩ ለመመለስ ተስፋ የሚያደርገው አንቺን ነበር። ምክንያቱም ዓለምን የሚያድነው ሁሉን ማድረግ የሚችለው ኃያሉ አምላክ ቢሆንም ይህንን የድኅነት ሥራ ከእርሷ በመወለድ በፍጹም ተዋሕዶ እንደሆነ አስቀድሞ ስለ ነገረው ነበር።

በመቀጠልም ብዙ ነቢያት በልዩ ልዩ ምሳሌ ስለ እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ተነበዩ በ4800 ዓ/ዓ አካባቢ ነቢዩ ኢሳይያስ በግልጽ “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወትሰምዮ ስሞ አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ” = እንሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፤ አማኑኤል ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። በማለት በማያሻማ መልኩ ተናገረ። ታዲያ ይህ የነቢዩ ትንቢት እመቤታችን ከመወለድዋ ማለትም ከ5486 ዓመተ ዓለም 700 ዓመታትን ቀድሞ የተነገረ ትንቢት ስለሆነ እመቤታችን ከዓለም በፊት በአምላክ ሕሊና የተሟላ ታሪክ ነበራት የሚለውን እውነት ያረጋግጥልናል። ምክንያቱም ነቢዩ ሲተነብይም እመቤታችን አልነበረችም ወላጆቿም አልተወለዱም።

ይህ የነቢዩ የኢሳይያስ ቃል “ድንግል” አለ እንጂ ድንግል ማርያም ስለማይል በምን እናውቃለን ለምትሉና በትክክል ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም መነገሩን ማረጋገጥ ለምትፈልጉ ወንጌላዊው ማቴዎስ በምዕራፍ 1፡ ቍጥር 20 ጀምሮ
“ወዝ ኵሉ ዘኮነ ከመ ይትፈጸም ዘተብህለ እምኀበ እግዚአብሔር በነቢይ እንዘ ይብል። “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤል” ዘበትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ።

= ከእርሷ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። ልጅም ትወልዳለች እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። በነቢይ ከጌታ ዘንድ እንሆ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል፣ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው። በማለት ትንቢተ ኢሳይያስ ም 7 ቍ 14ን ጠቅሶ ይነግረናል።

 ይህ ቃል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የተናገረው ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ የጻፈው የማያጠራጥር ምስክርነት ነው።

ሦስተኛው የታሪክ ክፍል

“ወበሳድስ ወርኅ ተፈነወ ገብርኤል መልአክ እምኀበ እግዚአብሔር ኀበ አሐቲ ሀገር ዘገሊላ እንተ ስማ ናዝሬት። ኀበ ድንግል እንተ ተፍኅረት ለብእሲ ዘስሙ ዮሴፍ ዘእም ቤተ ዳዊት ወስማ ለይእቲ ድንግል ማርያም። ወቦአ መልአክ ኀቤሃ ወይቤላ ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ  እግዚአብሔር ምስሌኪ ወቡርክት አንቲ እምአንስት። ወርእያ ደንገፀት እምቃሉ።”

= በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፣ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። መልአኩም ወደ እርሷ ገብቶ ደስ ይበልሽ ጸጋ የመላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።

ይህ ቃል እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በአምላክ ሕሊና የመኖሯን አላማ፣ ዓለም ከተፈጠረ በኋላ ሲጠበቅ የነበረውን የሥጋዌ እና የድኅነተ ዓለም ተስፋ የነቢያትን ትንቢት ሁሉ እውን የሚያደርግ፤ በእመቤታችን ቅድመ ታሪክ ሁሉ ሲጠራጠሩ ለነበሩት ተግባራዊ እውነት ነበር።

የእመቤታችን ምርጫ ልዩና የተፈጥሮ ሕግን የጣሰ፣ በሥነ ፍጥረት ታሪክ ውስጥ ታስቦም ተፈጽሞም የማያውቅ በመሆኑ ለራሷ ለእመቤታችን ጭምር ፈጥኖ የሚታመን አልነበረም፤ በመሆኑም እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር ዘንድ በቀጥታ ተልኮ ከመጣው ከመላእክት አለቃ ከመልአኩ ከቅዱስ ገብርኤል ጋር ተከራክራ ነበር፤ እንዴት እንደዚህ ይሆናል በማለት ጠይቃ ነበር።

“ወርእያ ደንገፀት እምቃሉ ወኀለየት ወትቤ እፎኑ እንጋ ዘከመዝ አምኃ ይትአምኁ”
“እፎኑ ይከውነኒ ዝንቱ እንዘ ኢየአምር ብእሴ”

= እርሷም ባየቺው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች።

“ወአውሥአ መልአክ ወይቤላ መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ ወኀይለ ልዑል ይጼልለኪ ወዘኒ ይትወለድ እምኔኪ ቅዱስ ውእቱ ወይሰመይ ወልደ እግዚአብሔር ልዑል…”

“እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር” እመቤታችንን ያሳመናት ቃል ይህ ነበረ። ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም። አዎ የለም “በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሐለየ ይፌጽም”

እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ የተለየ ጸጋ የተለየ ምርጫ ስላላት ከፍጡራን ሁሉ የተለየ ክብር ተሰጥቷታል፤ ቅድስተ ቅዱሳን ማለትም ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ የተቀደሰች ማለት ነው፤ ከቅዱሳን መላእክትም ሆነ ከቅዱሳን ሰዎች እንደ እመቤታችን ያለ ፍጡር አልተገኘም ። ቅዱስ ኤፍሬም በድርሰቱ “የአቢ ክብራ ለማርያም እምኵሎሙ ቅዱሳን፤ ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል፤ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሐዱ ዘእም ቅድስት ሥላሴ” በማለት ስለ እመቤታችን ልዩ ፍጡርነት እና ክብር ይናገራል።

ኪሩቤል እና ሱራፌል የሚባሉት የአምላክን መንበር ተሸክመው ቅዱስ ቅዱስ እያአሉ የሚኖሩ ናቸው አምላክን በዐይናቸው እንኳን ማየት አይችሉም ፤ እመቤታችን ግን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማሕጸኗ ተሸከመቺው። ለዚህም ነው ከሁሉም የምትልቀው። አባ ሕርያቆስም “ነጸረ አብ እምነ ሰማይ ወኢረከበ ዘከማኪ” በማለት እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ዓለሙን ሁሉ ተመለከተ አየ እንዳንቺ ያለ አላገኘም የቅድስናሽን ደም ግባትም ወደደ አንድ ልጅንም ወደ አንቺ ላከ። ይላል።

በመግቢያየ እንደ ተናገርኩት ስለ እመቤታችን የተነገረውን ተርኮ የሚጨርስ ባለመኖሩ። እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የተነገረው የተተነበየው ሁሉ እውን ከሆነ በኋላ፤ ከእግዚአብሔር በቀጥታ የተላከው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የተናገረውን አስደናቂ መልእክት፤ ቅድስት ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱስ ተመልታ የሰጠቺውን ምስክርነት፤ ከሰማች በኋላ፤ ለመረጣት ለአምላኳና ለልጃ ያቀረበቺውን ምስጋና በመናገርና ከወላጆቿ ከተወለደችባት ቀጽበት ጀምራ እስከ ጥር 21 ቀን 50 ዓ/ም ድረስ የነበራትን ሥጋዊ ዕድሜ ጠቅሼ ትረካየን እገታለሁ።

ወትቤ ማርያም/ ማርያምም እንዲህ አለች።

“ታዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ወትትሐሠይ መንፈስየ በአምላኪየ ወመድኀኒየ፤ እስመ ርእየ ሕማማ ለአመቱ ናሁ እም ይእዜሰ ያስተበፅዑኒ ኵሉ ትውልድ። እስመ ገብረ ሊተ ኀይለ ዐቢያተ ወቅዱስ ስሙ ። ወሣህሉኒ ለትውልደ ትውልድ ለእለ ይፈርህዎ። ወገብረ ኀይለ በመዝራዕቱ ወዘረወሙ ለእለ ያዐብዩ ኀሊና ልቦሙ። ወነሠቶሙ ለኀያላን እመናብርቲሆሙ አዕበዮሙ ለትሑታን። ወአጽገቦሙ እምበረከቱ ለርኁባን ወፈነዎሙ  ዕራቆሙ ለብዑላን። ወተወክፎ ለእስራኤል ቍልዔሁ ወተዘከረ ሣህሎ። ዘይቤሎሙ ለአበዊነ ለአብርሃም ወለዘርዑ እስከ ለዓለም።” ሉቃስ 1፡47

ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥
መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና።
እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤
ስሙም ቅዱስ ነው።
ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።
በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤
ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ 
ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤
ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤
የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤
ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥
ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።

እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም
·        ነሐሴ 7 ቀን በ5486 ዓ/ዓ ከአባቷ ከቅዱስ ኢያቄምና ከእናቷ ከቅድስት ሐና ተፀነሰች
·        ግንቦት 1 ቀን 5486 ዓ/ዓ ተወለደች
·        ለ 3 ዓመታት በአባት በእናቷ ቤት ከቆየች በኋላ የሥዕለት ልጅ በመሆኗ በ3 ዓመቷ
ታሕሣስ 3 ቀን በ5489 ዓ/ዓ በሥዕለት ልጅነት ለቤተ መቅደስ ተሰጠች
·        ለ12 ዓመታት በቤተ መቅደስ ኖረች
·        3 ዓመት ከ 9 ወር ከ 5 ቀን በጠባቂዋ በቅዱስ ዮሴፍ ቤት፤ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር የግብፅ ስደትን ጨምሮ ኖረች
·        30 ዓመት ከ 2 ወር ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ኖረች
·        15 ዓመታት ከጌታ ስቅለት በኋላ በወንጌላዊው በዮሐንስ ቤት ኖራ ጥር 21 ቀን በ50 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለየች።

ልመናዋ ክብሯም በእውነት ይደርብን
ይሁን ይደረግ አሜን

ከአውደ ጥናት ዘግእዝ


Wednesday, January 8, 2020

ለግእዝ ቋንቋ ተማሪዎች መልካም ዜና/Good news for Ge'ez learners


6in1(፮በ፩)
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው፦

 በመጀመሪያ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ ልዑል አምላክ ለመጪው ዓመትም በሰላም ያድርሰን። በመቀጠልም የሚከተለውን መልካም ዜና አስታውቃችኋለሁ በትኩረት ተመልክታችሁ ተግብሩት



Download the best free open source video creator software Streamlabs OBS
https://streamlabs.com/editor?promo=melakubesetegn-e38b-10  

አውደ ጥናት ዘግእዝ “የግእዝ ቋንቋ ለሁሉም” በሚለው መርሕ መሠረት የትምህርቱ ፍላጎት ኑሯችሁ የመክፈል አቅም ላነሳችሁ ሁሉ ከተወሰኑ ፍላጎት ካላቸው እኅቶችና ወንድሞች ጋር በመሆን የትም ቦታ ልታገኙት በማትችሉት ልዩና ቀላል እንዲሁም  አቋራጭ በሆነ መንገድ የግእዝን ቋንቋ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ትማሩ ዘንድ በሚከተሉት መመሪያዎች መሠረት በመደራጀት ተመዝግባችሁ መማር እንድትችሉ መልካም ዜናን እንደሚከተለው አበሥራችኋለሁ ይህ ፕሮግራም እናንተንም እኔንም ሕብረተሰቡንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ስለሆነ የዚህ መልካም ሥራ ተካፋይ ብቻ ሳትሆኑ አስተባባሪም ልትሆኑ ይገባል እላለሁ፤ ምክንያቱም ብዙዎች ይህንን ትምህርት ለመማር ጥልቅ ፍላጎት አላቸውና ነው።



ክፍያና መመሪያ (በሚከተለው መልኩ መመሪያውን በተግባር በማዋል ፈጥናችሁ መጀመር ትችላላችሁ።)
በመጀመሪያ እርስ በርሳችሁ ለመተዋወቅ ይረዳችሁ ዘንድ ትክክለኛ ስማችሁን እና የምትኖሩበትን አገር ከተቻለ ፎቷችሁንም ጭምር በዋትስአፕ ፕሮፋይላችሁ ላይ አድርጉ(ወይም ጻፉ)

1.  ክፍያ፦ ለያንዳንዱ ሰው (6ቱ ግሩፖች) ለአፍሪካ(ኢትዮጵያን ጨምሮ) $32 (ሠላሳ ሁለት) ዶላር እያንዳኑ ሰው ማለት ነው። ለሌሎቹ አገራት ሁሉ፦ $50(ሃምሣ ዶላር) (6ቱም እያንዳንዳቸው)

2.  6(ስድስት) ሰዎች በአንድ ላይ ለመክፈል ተስማሙ
(ከተቻለ በአንድ አካባቢ የምትኖሩና የምትተዋወቁ ብትሆኑ መልካም ነው፣ ካልሆነ ግን ከዚህ በፊት ባትተዋወቁም፣ በአንድ አገር ባትኖሩም በዚህ ግሩፕ ላይ ከተስማማችሁ ይቻላል)

3.  በያላችሁበት ሁናችሁ $50(ሃምሣ ዶላር) ወደ ባንክ ታስገባላችሁ
 ወይም በሌላ መንገድ ከፍላችሁ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ትልካላችሁ፣ ሁላችሁም ማለትም 6ቱ ሁሉ ክፍያቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ ግሩፑ አስገባችኋለሁ።

·        በአንድ ላይ የምትከፍሉ ሰዎች ስድስታችሁ ማለት ነው በደምብ መነጋገር አለባችሁ ምክንያቱም ሁሉም በያሉበት ከፍለው ካላጠናቀቁ የከፈሉት ሰዎች ያልከፈሉትን መጠበቅ ስላለባቸው ነው(ከተቻለ አንድ ሰው ሃላፊነቱን ወስዶ በደንብ ማስተባበር አለበት)

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ

Thursday, August 22, 2019

ታሪከ ፍልሰታ፣ ትንሣኤሃ ወእርገታ ለማርያም ድንግል

Filseta, Tinsaeha, we Ergeta Lemariam Dingle Belsane Geez 

ታሪከ ፍልሰታ፣ ትንሣኤሃ ወእርገታ ለማርያም ድንግል




ይህ በያመቱ የሚወጣው የታዋቂ ገጣምያን ግጥሞችን ያሰባሰበ ሲሆን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የእንግሊዘኛ ግጥሞቼ ታትመው ወጥተዋል።

Ring Video Doorbell with HD Video, Motion Activated Alerts, Easy Installation - Satin Nickel click to buy


Atomic Habits: An Easy & Proven Way to Build Good Habits & Break Bad Ones 

“ወብዙኃተ ካልኣተ ተአምራተ ገብረ እግዚእ ኢየሱስ በቅድመ አርዳኢሁ ዘኢተጽሕፈ ውስተ ዝንቱ መጽሐፍ” ወንጌለ ዮሐንስ 20፡ 30
“ወኵሉ መጽሐፍ ዘበ መንፈሰ እግዚአብሔር ተጽሕፈ ይበቁዕ ለኵሉ ትምህርት ወተግሣጽ ወአርትዖ ወጥበብ ወጽድቅ ከመ ይትገሠጽ ብእሴ እግዚአብሔር ውስተ ኵሉ ምግባረ ሠናይ” መልእክተ ጳውሎስ ካልእት ኀበ ጢሞቴዎስ ሣልሳይ ምዕራፍ ወኁልቍ ዐሠርቱ ወስድስቱ እስከነ ዐሠርቱ ወሰብአቱ።
ታሪከ ፍልሠተ ሥጋሃ ለማርያም ድንግል።

ቅድመ ኵሉ ነገር ይደልወነ ናእምር ትርጓሜሁ ለፍልሰት፤ ፍልሰት ብሂል ስደት፤አው ሑረት፤ ሶብ አሐዱ ነገር አው አካል ይሰደድ አው ይትወሰድ እምነ መካን ዘነበረ ቅድመ ኀበ ካልዕ ወሐዲስ መካን ንጸውኦ “ፍልሰት”
ወአመ ንቤ “ፍልሰታ” ንትናገር በይነ ፍልሰተ አሐቲ አንስታይ ፆታ፤ አላ ኢነአምር ዘመኑ ውእቱ ዝንቱ ፍልሰት፤ ኩለሔ ይደሉ ከመ ንጽሐፍ ከመ ዘይተሉ ዐረፍተ ነገር  “ፍልሰታ ለማርያም” አው ፍልሰተ ሥጋሃ ለማርያም” ዝንቱ ዐረፍተ ነገር ይነግረነ በይነ ፍልሰተ ሥጋሃ ለማርያም አው በእንተ ፍልሰታ ለማርያም፤ በይነ ፍልሰተ ሥጋሃ ለማርያም እምነ ብሔረ ሕያዋን ኀበ ጌቴ ሴማኒ።

በዝንቱ ትምህርትነ ነሐትት ወንትሜሀር በይነ ታሪከ ድንግል ማርያም፤ ወፆመ ሐዋርያት ቅዱሳን ወኀይለ ጸሎት ዘይጼለይ በእምነት ጽንእት እንተ አልባቲ ኑፋቄ። ዝንቱ ታሪክ ያርእየነ ከመ እግዚአብሔር ሰማኤ ስእለት ወተወካፌ ጸሎት ውእቱ፡

ጸሎት ብሂል ልሣነ አምላክ ወሰብእ እለ ይትናገሩ በበይናቲሆሙ፤ ወኵሉ ሰብእ ይደልዎ ከመ ይጼሊ ወትረ ኀበ አምላኩ እስመ አልቦቱ ሐብት፤ ጥኢና፤ ወሰላም እምኔሁ (እምነ ርእሱ) ። ወበእንተዝ ይደልዎ ይጤይቅ ኵሎ ነገረ እምነ አምላኩ። ንሕነሰ ነዳያን ወአልብነ ምንተ።

 አመ ነሐስስ ሰላመ ንጠይቅ ሰላመነ  እምኔሁ ወአመ ነሐምም  ንጠይቅ ጥኢናነ እምኔሁ፤ ወአመ ንርህብ ንጠይቅ እምኔሁ መብልአ፤ ወውእቱሰ ይሁበነ በፍቅር ኵሎ ዘነሐሥሥ።

በከመ ይቤሉ መጻሕፍተ ብሉያት ወክርስቶስ በወንጌሉ ኵሉ ሰብእ እመ ይጤይቅ አምላኮ እንዘ ይጼሊ እምልቡናሁ ምስለ አሚን ርትዕት ወጽንእት ይረክብ ዘየሐሥሥ ወዘይጤይቅ።

እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተካየደ ኪዳነ ምስሌነ ወምስለ ኵሎሙ ተላውያኒሁ ዘይስእለዎ አው ዘይጤይቅዎ በጸሎት ምስለ አሚን እንተ አልባቲ ነቅዕ።
ኦ ምእመናን! ነጽሩ ኀበ ዝንቱ ቃለ ክርስቶስ ዘተናገረ በወንጌለ ማቴዎስ በሳብዓይ ምዕራፍ ከመ ዘይተሉ።

“ሰአሉ ወይትወሀበክሙ ኅሡ ወትረክቡ፤ ጎድጉዱ ወይትረኀወክሙ እስመ ኵሉ ዘሰአለ ይነሥእ ወዘሂ ኀሠሠ ይረክብ ወለዘሂ ጎድጎደ ይትረኀዎ..” ማቴ 7፡7
ዝንቱ ውእቱ ቃለ ክርስቶስ ዘኢየሐልፍ ወንሕነ ነአምን ቦቱ ለእመ ንጼሊ በልቡና ንፁህ ወበአሚን ምሉእ ንክህል ከመ ናፍልስ ደብረ! ወአልቦ ነገር ዚኢይትከሐል በጸሎት።

ዝንቱ ውእቱ ምክንያተ ጾመ ሐዋርያት ወውእቶሙ የአምሩ ዘንተ ከመ እግዚአብሔር ይገብር ሎሙ እለ ይስእሉ እምኔሁ፤ ያጸምእ ጸሎቶሙ ወያወስእ ጥያቄሆሙ  ወበእንተዝ ጾሙ ከመ ይንስዑ ሥጋሃ ለማርያም ድንግል ዘሐሠሡ፤ እስመ እግዚአብሔር ተናገረ በመጻሕፍቲሁ በይነ ኃይለ ጸሎት ወእምነት።

ሐዋርያት ጾሙ ክልኤተ ሱባኤያተ አው አሠርተ ወአርባእተ ዕለታተ እንዘ ይዌጥኑ እም አመ አሚሩ ለነሐሴ እስከነ አሠርቱ ወአርባእቱ ለነሐሴ. ወአመ ፈጸሙ ሐዋርያት ሱባኤሆሙ አቀበ እግዚአብሔር ቃሎ ዘተናገረ ወተወክፈ ጸሎቶሙ ለሐዋርያቲሁ ወወሀቦሙ  ሥጋሃ ለማርያም ድንግል ዘይሐሥሡ፤ ወሐዋርያት አእረፉ ሥጋ በክብር በጌቴ ሴማኒ ወበ ሰሉስ ዕለት ተንሥአት ከመ ትንሣኤ ወልዳ ወአርገት ከማሁ መንገለ ሰማይ በክብር። 

ወናሁ እነግረክሙ በይነ ዕድሜሃ ወሕይወታ ለማርያም ድንግል እመ አምላክ በዝንቱ ዓለም፤ እግዝእተነ ማርያም ተጸንሠት አመ ሰብኡ ለነሐሴ እምነ አቡሃ ኢያቄም ወእማ ሐና፤ ወተወልደት  አመ አሚሩ ለግንቦት በሐምሣ ወአርባዕቱ ምዕት ሰማንያ ወስድስቱ ዓ/ዓ ።

 አምጣነ ይእቲ ተወልደት በስእለት ወበእንተዝ አመ ኮና ሠለስተ ዓመታ አቡሃ ወእማ ወሰድዋ ኀበ ቤተ መቅደስ አመ ሰሉሱ ለታህሣስ ለትትለአክ በቤተ እግዚአብሔር ከመ ይፈጽሙ  ቃሎሙ ዘተናገሩ እምቅድመ ይለዱ ኪያሃ።

 ወማርያም ድንግል ነበረት አሠርተ ወክልኤተ ዓመታተ እንዘ ይናዝዝዋ መላእክት ወትትልአክ በቤተ መቅደስ በከመ ይቤ መጽሐፍ ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ። በከመ ተጽሕፈ በወንጌል አብሠራ መልአክ ዘስሙ ገብርኤል በከመ ተሐርየት ወተሌለየት እምነ ኵሎን አንስት ዘደቂቀ አዳም ከመ ይትወለድ እምኔሃ አምላክ በሥጋ ከመ ያድኅን ደቂቀ አዳም እምኃጢአቶሙ።

እግዝእትነ ማርያም ነበረት በቤተ መቅደስ እስከነ በጽሐት መጠነ አንስት ወሶበ ልሕቀት  ወኮና አሠርተ ወሐምስተ ዓመተ ተጋብዑ ካህናተ ቤተ መቅደስ ከመ ይጠይቁ ፈቃደ እግዚአብሔር ወይርከቡ ላቲ አቃቤ  ወበ ፈቃደ እግዚአብሔር ረከቡ በከመ ተመነዩ ወተውህበት  ለዮሴፍ አምጣነ በጽሆ ዕፃ ከመ ይዕቀባ ወነበረት በቤተ ዚአሁ ተሠዐተ አውርሃ ወሐምስተ ዕለተ።

ወበጽሐ ጊዜ ወሊዶታ ሖረት ኀበ ቤተልሔም ምስለ ዮሴፍ፤ ወሰሎሜ ከመ ይጸሐፉ በትዕዛዘ ንጉሥ በበ ሐገሮሙ ወነበሩ በህየ እስከነ ወለደት ወልደ ዘበኵራ በውስተ ጎለ እንሥሳ ዘቦ በቤተልሔም።

ወበከመ ይቤ ወንጌል ተውህበት ለፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ እንዘ ሀሎ ክርስቶስ በዕፀ መስቀል ከመ ትኩን እመ ኵልነ ወንኵን ንሕነ ደቂቀ ዚአሃ በቃለ ክርስቶስ “ነዋ ወልድኪ ወነያ እምከ” ወነበረት አሠርተ ወሐምስተ ዓመታተ በቤተ ዮሐንስ፤ ወአመ ኮነ ዕድሜሃ ስድሳ ወአርባእቱ ዓመታተ፤ አመ ዕሥራ ወአሚሩ ለጥር በዐርብዓ ወሰመንቱ ዓመተ ምሕረት አዕረፈት እምዝንቱ ዓለም፤ በከመ ተጽሕፈ በመጻሕፍት ወመላእክት አእረፉ ሥጋሃ በብሔረ ሕያዋን በታሕተ ሥርወ ዕፀ ሕይወት እስከነ አሠርቱ ወአርባዕቱ ለነሐሴ።

ከመ ነበብኩክሙ በማዕከለ ዝንቱ ትምህርት ወሶበ ፈጸሙ ሐዋርያት ክልኤተ ሱባኤያተ እስከነ  አሠርቱ ወአርባእቱ ለነሐሴ  ተወክፉ ሥጋሃ ዘሐሰሱ በጸሎት ወአእረፍዎ ለሥጋሃ በጌቴ ሴማኒ ወበሳልስት ዕለት ተንሥአት ወአርገት ከመ ወልዳ ዋሕድ።

ወበእንተዝ ናከብር በዛቲ ዕለት ሠለስተ በአላቲሃ ለማርያም ዘይሰመያ ፍልሰተ ሥጋሃ፤ ዕርገታ ወትንሣኤሃ ። አበው ወአኃት በዝንቱ ጾም ረከቡ ሐዋርያት ዘሐሰሱ ወዘ ተመነዩ፤ እምነ አምላኮሙ፤ ወበእንተዝ ይደልወነ ንጤይቅ ርእሰነ ወንሕትት ግብራቲነ፤ ኵለሄ ንጸውም ወንጼሊ አላ ኢይሰምአነ እግዚአብሔር፤ ወኢንረክብ ዘነሐስሦ፤ ኢይመይጥ እግዚአብሔር እዝነ ምሕረቱ ኀበ ጽራህነ፤ ወኀበ ጸሎትነ።

በከመ ይቤ በመጻሕፍት “ስማይ ወምድር የሐልፍ ወቃልየሰ ኢየሐልፍ” ኢይዌልጥ እግዚአብሄር ቃሎ ዘተናገረ ወውእቱ ወሀበነ ቃሎ  እንዘ ይብል  “ሰአሉ ወይትወሀበክሙ፤ ጠይቁ ወትረክቡ፤ ጎድጉዱ ሆኃተ ወይትረኀው ለክሙ” አላ ለምንት ኢንረክብ ንሕነ ዘንስእል?  ወለምንት ኢይትወሀበነ ዘንጤይቅ? ወኢይትረኀው ለነ ኆኃተ ምሕረቱ? አብያተ ዚአየ ወምክንያቱሰ ቀሊል ወሐጺር! ጾምነ ወጸሎትነ አኮ ከመ ጾም ወጸሎት ዘያሠምሮ ለእግዚአብሔር፤ ወበእንተዝ ንነስህ ወንእመን ከመ አበስኖ ለአምላክነ ወንትመየጥ ኀበ ምግባረ ሠናይ ወናርትዕ ፍኖተነ ምስሌሁ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አምላክነ በይነ ዘአብጸሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት አቂቦ በምሕረቱ፤፡

ጸሎታ ወበረከታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ይህድር በላእሌነ 

Monday, July 29, 2019

Preaching in Geez Languge/ስለ ቅዱስ ሐምሌ 19 የቅዱሳን በአል ስብከት በግእዝ ቋንቋ በመ/ር መላኩ



ስብከት በይነ ተራድኦተ መላእክት ወጽንአተ እምነተ ቅዱሳን ወኀይለ እምነት በውስተ አማንያን በመ/ር መላኩ

ቪዲዮም የድምፅ ጥራቱ ተስተካክሎ እንደገና የተዘጋጀ ነው

Sunday, July 28, 2019

Preaching in Geez Language about Hamle Gabriel/የሐምሌ ገብርኤል ስብከት በግእዝ ቋንቋ ...


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ 
አምላ
ሊቃውንት፤ ካህናት፤ ዲያቆናት ምእመናን አበዉ ወአኀው እማት ወአኀት ኵልክሙ በሐክሙ እብል በስመ እግዚአብሔር ወእግዚአብሔር ይሰባሕ በይነ ዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት አሜን።

ዮም በዛቲ ዕለት በፈቃደ እግዚአብሔር ንትሜሀር በይነ ተራድኦቱ ለቅዱስ ገብርኤል መልአክ ወክልኤቱ እም ወሕጻን ሰማዕታት ዘይሰመዩ ቅርቆስ ወኢየሉጣ፡ እለ ናከብር ሎሙ ዝክረ በአሎሙ  ዓመ ዐሠርቱ ወ ተሰዓቱ ለሐምሌ በበ ዓመቱ እስመ በዛቲ ዕለት ውእቶሙ ኮኑ ሰማዕተ በሐገረ ሮሜ።

 በዝንቱ በአል ንሐትት ሕየንተ ታሪክ ዘይሰመይ ዘመነ ሰማዕታት ወዘተፈጸመ ቅድመ እሥራ ምዕት ዓመተ ምህረት።

ዝንቱ ዘመን እምዐሠርቱ ምዕት ወስድሳ እስከነ ሠለስቱ ምእት ዐሠርቱ ወክልኤቱ ዓ/ም ድኅረ ክርስቶስ ውእቱ፤ ወንጼውኦ  “ዘመነ ሰማዕታት” አው “ዘመነ ስደት” ብሒለነ፤ እስመ በዝንቱ ዘመን ብዙኃን ክርስቶሳውያን ተሰዱ ወተቀትሉ በአላውያን ነገሥታተ ሮም፤ በእንተ ዘአምኑ በክርስቶስ ወሰምዑ ክርስቶስሃ ከመ ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ፤ ወተሰይሙ በስሙ ተብሒሎሙ “ፆታ ክርስቶስ”።

 ወነገሥታተ ዝንቱ ዘመን አው ነገስታተ ሮም እንዘ ያቀውሙ ጣዖታተ በስሞሙ ወበ መልክኦሙ፡ ወአዘዙ ኵሎሙ ዘይነብሩ በታሕተ ሥልጣኖሙ ከመ ይስግዱ ለጣዖታት ዘአቀሙ በስሞሙ ወያምልክዎሙ።

በከመ አለበውኩክሙ በሙባአ ትምህርትየ በዝንቱ በአል ንትሜሀር በይነ ተራድኦተ አሐዱ መልአክ ዘስሙ ገብርኤል ወበይነ ኀይለ እምነት በኀበ አማንያን ከመ ኢየሉጣ ወቂርቆስ ዘይመስሉ አው ከመ ክልኤቱ ሰማዕታት፡፡

ሰማዕት አው ሰማዕታት ቢሂል ሰብእ ዘተቀትለ በይነ ዘተናገረ ጽድቀ በእንተ ክርስቶስ አው በእንተ አሚን በክርስቶስ ቅድመ አላውያን ነገሥታት። አው ብእሲ ወብእሲት እለ ተቀትሉ በይነ ዘተናገሩ ጽድቀ በእንተ ክርስቶስ በቅድመ አላውያን እንበለ ይፍርሁ ሞተ ሥጋ።

በከመ ይቤ ጳውሎስ በመልእክቱ ኀበ ዕብራውያን፤ መላእክት ውእቶሙ መናፍስት ዘኢይትገሠሱ ወዘኢይትረአዩ በአካለ ሥጋ ወግብሮሙሰ ዘይትፌነዉ እም ኀበ እግዚአብሔር ለተራድኦት ወለአቂቦት ኪያነ ዘነአምን ክርስቶስሃ ከመ ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ። “አኮኑ ኵሎሙ መላእክት መንፈስ እሙንቱ ወይትፌነዉ ለመልእክት በእንተ እለ ሀለዎሙ ይረሱ ሕይወተ ዘለዓለም” ። ዕብ. 1፡14

ቅድመ እትናገር በይነ ታሪከ በአል ዘዮም መፍትው እንግርክሙ በእንተ ቅዱስ ገብርኤል ዘይሰመይ በአፈ ሊቃውንት ከመ ኮነ ሰባኬ ቃለ እግዚአብሔር  ወመጋቤ ሐዲስ በቅድምና፤ ወበእንተዝ ነአምሮ ለገብርኤል መልአክ በአበይት ተአምራት ሠለስቱ፡
ቀዳማይ ተአምር፡ ውእቱ ገብርኤል ወጠነ ትምህርተ ስብከት፡ ወሰበከ መላእክተ በዓለመ መላእክት በዕለተ ሰንበት እንዘ ይብል “ንቁሙ በበ ሕላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ” ወሰበኮ ለዝንቱ ስብከት ሶበ ተሀውኩ መላእክት በክህደተ ሳጥናኤል መልአክ አመ ይቤ “አነ ፈጠርክዋ ለዛቲ ዓለም ወፈጠርኩ ኪያክሙ አልቦ ካልእ ፈጣሪ ዘእንበሌየ”

ካልአይ ተአምር ፡ ገብርኤል ተፈነወ ፍጡነ እም ኀበ አምላኩ ከመ ይርድኦሙ ለዳንኤል ነቢይ ወለሠለስቱ ደቂቅ በአጺዎተ አፈ አናብስት ወበአጥፍኦተ እሳት ከመ ኢይሙቱ እንበለ ኃጢአቶሙ ወይትአወቅ ኀይለ እምነት ጽንእት። ወበዝንቱ ተአምር ብዙኃን ተመይጡ እምነ አምልኮ ጣኦት ወአምኑ በአምላከ ዳንኤል ወበሰለስቱ ደቂቅ

ወሣልስ ተአምር ፦ ገብርኤል ተፈነወ እምነ አምላኩ ኀበ ድንግል ወቅድስት ማርያም እመ አምላክ ከመ ያብሥራ ወይንግራ ምሥጢረ ሥጋዌ ወከመ ተሐርየት ለከዊነ እመ አምላክ። “ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ ወቡርክት አንቲ እምአንስት …”

ወራብዕ ተአምር፡ ገብርኤል አቍረረ ፍሉሐ ማየ፦
 ከመ መጽሐፈ ገድሎሙ ለቅድስት ኢየሉጣ ወቅዱስ ቂርቆስ ይቤ ሐገረ ኢየሉጣ ይትበሐል አንጌቤን ወዝንቱ መካን ውእቱ አድያም ዘሐገራት እለይትቀነዩ በታህተ ነገሥታተ ሮም። ወዝንቱ ዘመን ዘመነ አላውያን ውእቱ።

 ወአመ ኮነ ዕድሜሁ ለቂርቆስ ሠለተ ዓመተ ተጸውአት ኢየሉጣ ኀበ መኮንነ ሐገር ወተጠየቀት በእንተ አምልኮተ ጣዖት ወአውሥአቶ ወትቤሎ ኦ መኮንን ሀሎ ሕጻን ዘሠለስቱ ዓመት መዋዕሊሁ፤ ተሰአል ኪያሁ።

ወመኮንን ፈነወ ሐራሁ ኀበ ሀሎ ሕጻን ቂርቆስ ወሐራ ረከቦ ለቂርቆስ ሕፃን አብጽሆ ኀበ መኮንን፤ ወመኮንን ይቤሎ ለሕጻን በሐከ ኦ ፍሡሕ ሕፃን፤ ወነበቦ በእንተ አምልኮተ አማልክቲሁ፤

ወአውስአ ቂርቆስ በመንፈሰ እግዚአብሔር ወረገሞሙ ለንጉሥ ወለመኳንንቲሁ ወለአማልክቲሁ እስከ ይደነግፁ ኵሎሙ እለሀለዉ መስለ መኮንን ።

ወተምአ መኮንን ወአዘዘ አግብርቲሁ ከመ ይደዩ ማየ ውስተ ዐባይ ጽሕርት ዘብርት ወያፍልሕዋ ውስተ እሳት ወኮነ ድምጸ ፍልሐታ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት። ወይቤ ቅዱስ ያሬድ “ድምጻ ለጽሕርት ከመ ነጓድጓደ መብረቅ”

ሕፃን ወእሙ ሶበ ቦኡ ውስተ ጽሕርት እንዘ ይሠምዑ ክርስቶስ ከመ ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ ፍጡነ መጽአ መልአከ እግዚአብሔር ዘስሙ ገብርኤል ወአቁረሮ ለኃይለ እሳት ። በከመ ተጽሕፈ በኦሪት ዘከመ ፈነወ መልአኮ ወአድኀኖሙ ለሠለስቱ ደቂቅ እምእሳት ዘይነድድ፤ ወገብረ ከማሁ በኢየሉጣ ወቂርቆስ ፍቁራኒሁ ወዘተአመኑ ቦቱ።
ናሁ ንትመየጥ ኀበ ርእስነ ወንሕትት ልቡናነ። ዘፈነወ መልአኮ ወአድኀኖሙ ለዳንኤል፤ ወለሰለስቱ ደቂቅ ወለ ኢየሉጣ ወቂርቆስ ውእቱ እግዚአብሔር ዘትማልም ወዮም፤ ወናሁ ይረድአነ ወያድኅነነ አላ መፍትው ብነ እምነት ዘአልቦ ነቅእ ወዘአልቦ ፍርሃት።

በዝንቱ ዘመን ዘመነ ዚአነ ንሬኢ በዐይንነ ለዘሰማዕኖ በእዝንነ፤ ብዙሐን ይትቀተሉ በሰቂል፤ በሰይፍ፤ በእሳት፤ እንዘ ንሬእዮሙ በብንተ ዐዕይንቲነ። ወበእንተ ዝንቱ መፍትው ንጼሊ ወንመይጥ ልቡናነ ኀበ እግዚአብሔር ከመ ይሚጥ ዐዕይንተ ምሕረቱ ኀቤነ ወኀበ ሐገሪትነ ኢትዮጵያ። ወይፈኑ ለነ መልአኮ ከመ ያቁርር እሳተ ዘይነድድ በውስቴትነ።

እግዚአብሔር ለብዎቶ የሐበነ ወያኅድር በልቡናነ ለዘሰማእኖ ወያፍሪ ፍሬ ሠላሣ ስድሳ ወምዕተ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Sunday, July 7, 2019

ስብከት በልሣነ ግእዝ በመ/ር መላኩ አስማማው /Preaching in Geez Language by M/r Melaku A...



ስብከት በልሳነ ግእዝ


መጻሕፍቱን ለመግዛት የመጻሕፍቱን ከበር ይጫኑ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።
አበውየ ካህናት ወአኀውየ
ዲያቆናት፤  አኀትየ ወእማትየ ተለውተ ክርስቶስ ኵልክሙ እፎ ሀደርክሙ
ወእፎ ሀሎክሙ?
አምላክነ ሔር ወመስተሣህል ውእቱ በይነ ዘአብጸሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት ዘእንበለ ይዝክር አበሣነ ዘንገብር
በተናግሮ ፤ በሐልዮ ወበገቢር በበዕለቱ ወበበ ሰዓቱ። ወበእንተ ኵሉ ዘገብረ ወዘይገብር ለነ ይሰባሕ ስሙ ለእግዚአብሔር አምላክነ።
ከመ ፈቃደ እግዚአብሔር ዮም ንትሜሀር በይነ ተዋሕዶትነ በዋሕድ አምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ዘወሀበ ነፍሶ ለቤዛ ኵሉ ዓለም።

ወርእሰ ትምህርትነሰ ውእቱ ዘይትረከብ እመነ መዝሙረ ዳዊት በአሐዱ ምዕት ሠላሳ ወክልኤቱ መዝሙር
በቀዳማይ ኍልቁ ወይብል ከመዝ

“ ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም ሶበ ይሄልዉ አኀው ኅቡረ” መቅድመ ኵሉ ነገር ይደልወነ ከመ
ናእምር እሙነ ለርእሰ ትምህርት ዘንትሜሀር።

 ወበእንተዝ ለብዉ ኀበ ዝንቱ ቃል! እንዘ እተረጉም ለክሙ በቀሊላን ቃላት
ከመ ታእምሩ ምሥጢሮ ወመልእክቶ ለዘተነግረ።
ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም ሶበ ይሄልዉ አኀው ኅቡረ ብሂል፤

 አመ  ዕደው ወአንስት አው ሕዝበ እግዚአብሔር  ይትረከቡ በፍቅር ኅቡረ በአሐዱ መካን ወበ አሐዱ ልብ። ነቢየ እግዚአብሔር
ቅዱስ ዳዊት በዝንቱ ምንባብ ኢተናገረ በይነ ሰብእ አው ሕዝብ ዘይነብሩ በአሐዱ መካን አላ ዘአልቦ ውሕደት ውስተ ልቦሙ።
 ውእቱ ይቤ በይነ ሕዝበ እግዚአብሔር
ኵሎሙ በይነ እደው ወአንስት እለ ተዋሐዱ በፍቅር፤ እለ ይነብሩ በአሐዱ መካን፤ እለ ይትናገሩ አሐደ ቃለ፤ በአሐዱ ልብ።

በዝንቱ ዘመን ዘመነ ዚአነ ብዙሐን ይነብሩ ኀቡረ በአሐዱ መካን፤ አላ አልቦ ፍቅር በልቦሙ፤ አልቦ
ውሕደት በቃሎሙ።  ኢንሰይሞ ሠናየ ለዝንቱ ኅላዌ ወለዝንቱ ሕብረት
ዘአልቦ ውሕደተ ልቡና።

ናሁ ንኔጽር ኀበ ርእስነ ወአነ እጤይቀክሙ ወእጤይቅ ርእሰየ በዘይተልዉ ጥያቄያት
ንነብርኑ ምስለ ብእሲትነ አው ብእሲነ፤ ምስለ ደቂቅነ አው ምስለ አዝማዲነ በአሐዱ ቤት፤ በአሐዱ
መካን? ኦሆ ነነብር፤ኦሆ ተዋሐድነ በመካን፤ ተዋሐደን በአካለ ሥጋ።  ዝንቱሰ እሙን ውእቱ። አላ ይነብሩኑ ኅቡረ አልባቢነ? ንትናገርኑ አሐደ ቃለ?
ይትረከብኑ ፍቅር እንተ አልቦቱ ምክንያት በማዕከሌነ? ንትፋቀርኑ በበይናቲነ?

ለእመ ናወሥእ እሎንተ ጥያቄያተ በብሒለ ኦሆ፤ ንክህል ከመ ንብል ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም ሶበ ንሄሉ
ንሕነ አኀው ወአኃት ኅቡረ።
አላ ለእመ ናወሥእ እሎንተ ጥያቄያተ በብሂለ “አኮ” መፍትው ንብል አኮ ሠናይ ወአኮ አዳም ሶበ ንሄሉ
ኅቡረ በመካን ባሕቲቱ፤ አኮ በልብ ወበተፋቅሮ።

መኑመ ኢይነብር ባሕቲቶ በአካለ ሥጋ በዝንቱ ዓለም፤ ወምክንያቱሰ ሰብእ ኢይክህል ነቢሮተ ባሕቲቶ
ወይደልዎ ይገብር ግብረ ምስለ ሰብእ ከመ ይብላእ ወይስቲ፤ አላ ይክህል ይንበር ባሕቲቶ በልቡናሁ፤ እንበለ ያፍቅር ካልአነ  እስከነ የሐልቅ ዕድሜሁ በምድር።

አዝማድየ አጽምዑ በእዝነ ልብክሙ ወአኮ በእዝነ ሥጋክሙ ወነጽሩ በዓይነ ኅሊናክሙ ወአኮ በዓይነ ሥጋ
ክሙ። አምላክነ ይብለነ በቃሉ ሕያው ዘይተሉ።

“ ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ” ወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ
14 (ዐሠርቱ ወአርባዕቱ)፡ ኍልቁ ዐሠርቱ ወሐምስቱ(15) ። በከመ ሰማእክሙ አምላክነ ይኤዝዘነ ከመ ንግበር አው ንእቀብ ትዕዛዞ።

ምንት ውእቱ ትእዛዙ ለእግዚአብሔር? ትክህሉኑ ትንግሩኒ? ምንተ አዘዘነ ከመ ንግበር?
ውእቱ አዘዘነ ከመ ንትፋቀር በበይናቲነ፤ ወከመ ንንበር አው ንሄሉ በተፋቅሮ ወንትዋሐድ በዘንትናገር
ወነኀሊ በአሐዱ ልብ  ከመ ናክብር ኵሎ ሰብአ እንበለ ናድሉ ለገፀ
ሰብእ። ወንትራዳእ በበይናቲነ፤

አበው ወአኀት፦ አመ ታነብቡ ወትሰምዑ ቃለ እግዚአብሔር

ነጽሩ በዓይነ ሕሊናክሙ
ወአኮ በዓይነ ሥጋክሙ፤ ወአጽምዑ በእዝነ ልቡናክሙ ወአኮ በእዝነ ሥጋክሙ። ኢይሰምእ እዝነ ሥጋ እንበለ እዝነ ልቡና አው ተሌልዮ
እምነ እዝነ ልቡና፤ ወኢይሬኢ ዓይነ ሥጋ ዘእንበለ ዓይነ ኅሊና አው ተሌልዮ እምነ ዓይነ ኅሊና።፤ ዓይነ ሥጋ ወዕዝነ ሥጋ  ባሕቲቶሙ ኢይክሉ  ከመ ይግበሩ ምንተ ዘእንበለ ይትዋሐዱ ምስለ ዕዝነ ውሳጤ ወዓይነ ውሳጤ።

አበው ወእማት፤ አኀው ወአኀት፤ ከመ መጻሕፍት ይሜህሩነ ኵለሔ ኢንነብር ሕያዋነ ወአልብነ ጊዜ በዝንቱ
ዓለም፤ ወሐጺር ውእቱ ዕድሜሁ ለደቂቀ አዳም አቡነ። ወበእንተ ዝንቱ ንመውት ፍጡነ በዘኢነአምራ ቅጽበተ ሰዓት።
“ወመዋዕለ ዓመቲነ ሰብዓ ክራማት እመሰ በዝኀ ሰማንያ ዓም”
መዝሙር 89(ሰማንያ ወተሰዐቱ)

በከመ ይቤ ዳዊት በዝንቱ ዓለም ኢንሄሉ ነዊሐ መዋዕለ፤ ወበእንተዝ ነገር ይደልወነ ንሕንጽ ቤተነ
በመንግሥተ እግዚአብሔር፤ ዝንቱ ዓለም ተውሕበ ለነ ለጊዜሁ ከመ ንሕንጽ ቦቱ ቤተነ ዘልዓለማዌ።

ከመ ተአምሩ ኵልክሙ በዝንቱ ዘመን መኑመ ኢይነብር መጠነ ኍልቆ መዋዕል ዘተጽሕፈ በመዝሙረ ዳዊት፤
ብዙኀን ይመውቱ ቅድመ ሠላሣ መዋዕለ ዓመቲሆሙ። በይነዝ ይደልወነ ንንበር ድልዋኒነ።

እንዘ ንነብር በአካለ ሥጋ በዝንቱ ዓለም ወበዝንቱ መካን መፍትው ንኵን ኅቡራነ ወውሑዳነ በፍቅር
በአሐዱ ቃል ወበአሐዱ ኅሊና። ከመ ነገርኩክሙ ቅድመ በማዕከለ ትምህርትነ ኢንትዋነይ በሕይወትነ ወኢንቅትል ጊዜነ ዘበ ምድር እንተ
ጸገወነ እግዚአብሔር እንበለ ንዋይ እንዘ ንገብር ግብራተ እለ አልቦሙ ረብሕ።

ንሌቡ ፍጡነ ቅድመ ይንሥአነ ሞት እምቅድመ ንሕንጽ ቤተነ ዘበሰማያት።

እስመ ውእቱ መሐሪ ወመስተሣህል ይሐበነ ዐዕይንተ አእምሮ ወለብዎተ ቃሉ ዘሰማዕነ ከመንግበር ሠናየ
ወይሐበነ ዘመነ ንስሐ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

እምነ አውደ ጥናት ዘግእዝ
በመ/ር መላኩ አስማማው ቢሰጠኝ