Sunday, October 29, 2023

የእሥራኤልን ልጆች ስትባርኳቸው እንዲህ በሏቸው


ሲሳለሙና ሲያሳልሙ

መሳለም ምንድነው?

·         እጅ መንሣት፣ ይቅር ማለት፣ መስቀል መሳም..

አሳላሚው ማነው? (ከ3ቱ የክህነት ደረጃዎች ሁለቱ ያሉት ካህን ነው አሳላሚው። ዲያቆን አያሳልምም)

·          ቄስ፣ኤጲስቆጶስ፣ፓትርያርክ(ፓትርያርክ የስልጣን እርከን ወይም ደረጃ ነው እንጂ የክህነት ደረጃ አይደለም፤ ቃሉ የግሪክ ሲሆን  “ርእሰ አበው ወይም የአባቶች አለቃ ማለት ነው። ፓቴር እና አርኺ)

ተሳላሚውስ ማነው?

·         ሁሉም ፆታ ምእመናን(ካህናት፣መነኮሳትና ምእመናን፤ ክህነት ያላቸው መነኮሳት ከካህናት፤ የሌላቸው ከምእመናን ይመደባሉ)

አሳላሚው ሲያሳልም ምን ይላል? ተሳላሚውስ ሲሳለም ምን ይመልሳል?

ቀሳውስትን፡

·          ሢመተ እዴሁ ለአቡነ ጴጥሮስ” - እግዚአብሔር ይሢምከ ውስተ ዘለዓለም መንግሥቱ

 

ዲያቆናትን፡

·         እግዚአብሔር ልዑል ይባርከ ወያብርህ አዕይንተ አልባቢከ” - ተሳላሚው፡ አሜን

·         በረከተ ጳውሎስ/እስጢፋኖስ ይህድር በላዕሌከ- አሜን

 

መዘምራንን፡

·         በረከተ ያሬድ ይህድር በላዕለከ - ተሳላሚው፡አሜን

 

መነኮሳትን፡

·         በረከተ እንጦንስ ወመቃርስ ይህድር በላዕሌከ- ተሳላሚው፡አሜን

 

ምእመናንን፡

·         “እግዚአብሔር ልዑል ይባርከ ወያርኢ ገጾ ላዕሌከ” -ተሳላሚው፡ አሜን

·         “እግዚአብሔር ልዑል ይባርኪ ወያርኢ ገጾ ላዕሌኪ” - ተሳላሚው፡አሜን

ስለመሳለምና ማሳለም መሠረቱ ምንድነው?

“ወነበቦ እግዚአብሔር ለሙሴ ወይቤሎ ንግሮሙ ለአሮን ወለደቂቁ ወበሎሙ ከመዝ ትባርክዎሙ ለደቂቀ እስራኤል።

ወትብልዎሙ ለይባርከ እግዚአብሔር ወለይዕቀብከ።

ወለያርኢ እግዚአብሔር ገጾ ላዕሌከ ወይምሐርከ።

ወለይሢም እግዚአብሔር ገጾ ኀቤከ ወየሀብከ ሰላመ።

ወይሰመይ ስምየ በላዕለ ደቂቀ እስራኤል ወአነ ዘእባርኮሙ።”

“እግዚአብሔርም፡ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኳቸው እንዲህ በሏቸው፦

እግዚአብሔር ይባርክህ፡ ይጠብቅህም፡ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ ይራራልህም፡

እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ ሰላምንም ይስጥህ።

እንዲሁ ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያደርጋሉ እኔም እባርካቸዋለሁ።” ዘኁል. 6፦22-27

 

የአሳላሚው/የካህኑ ሥልጣን ምን ያህል ነው?

በእግዚአብሔር ቃል መሠረት የካህኑ ሥልጣን መለኮታዊ ነው፤ ካህኑ ካሠረ የዓለም መንግሥታት በጋራ ሊፈቱት የማይችሉ ጽኑ እሥራት ይሆናል፤ ከፈታም ሙሉ ነጻነትን ያቀዳጃል።

“አማን እብለክሙ ዘአሰርክሙ በምድር ይከውን እሱረ በሰማያት፤ ወዘፈታሕክሙ በምድር ይከውን ፍቱሐ በሰማያት” ማቴ. 18፡18

 I am directing you to Amazon market place click the link below and enjoy the black Friday deal.

https://amzn.to/3Rdua3O

No comments:

Post a Comment