ሴቷ ባለቅኔ
የግእዝ ቋንቋ ትምህርታችን በወቅቱ እንደ ተለመደው
ባለመተላለፉ በጣም ይቅርታ እላለሁ ። ያልተላለፈበት ምክንያት ማኅበረ አጋፒ ወይም የፍቅር ኅብረት የሚባል ወላጅ አልባ ሕጻናትን
የምናሳድግበት ማኅበር ወይም ድርጅት አለ እና 6ኛ ዓመቱን የሚያከብርበት ጊዜ ስለነበረ ዓመታዊ ሪፖርትን ለማዘጋጀት ባጠቃላይ በአሉን
ለማዘጋጀት ጊዜ መውሰድ ስለነበረብኝ ነው እና ለበጎ ነው ማለቴ ነው። በዚህ አጋጣሚ ወደዚሁ ሕይወትን የማዳን ወላጅ ከማጣታቸውም
ሌላ በርኃብ የሚሰቃዩ ሕጻናትን የመርዳት ሥራ መሣተፍ የምትፈልጉ ካላችሁ በኢሜይል ልታነጋግሩኝ እንደምትችሉ ላሳስባችሁ እወዳለሁ።
ባለፈው ትምህርታችን በሁለት ክፍሎች ወይም ሰዎች
መካከል የሚደረግ የግእዝ ውይይት እንደማቀርብላችሁ ቃል ገብቸ ነበረ ሆኖም ግን ሌላ አዲስና ማራኪ ዝግጅት ስላገኘሁ አሁኑኑ ቢቀርብ
መልካም ነው ብየ በማሰብ ውይይቱን ለሚቀጥለው አስተላልፊዋለሁ
በመሆኑም ዛሬ በዚህ የግእዝ ቋንቋ ትምህርታችን
እጅግ አስደናቂ እንግዳን ይዠላችሁ ቀርቤያለሁ በሐገራችን ተዘውትሮ የተለመደ ባይሆንም ከወይዘሮ ገላነሽ ጀምሮ እውቅ የቅኔ ባለሙያዎች
የሆኑ ሴቶች እንደ ነገሩ ታሪካቸውን እናነባለን። አሁንም በዘመናቺን ቅኔ የተማሩ ሴቶችን ማየት እንደሰማይ የራቀ እንደ ትረት የሚወራ
ቢሆንም መኖራቸው ግን እውን ነው።
ከሁሉም በላይ አሁን ያለንበት ዘመን ግን እንኳን
ቅኔ የሚያውቁ ሴቶ ይቅርና ግእዝን የሚያውቁ ወይም የሚማሩ ወንዶች እንደ ልብ የማይገኙበት ጊዜ እየሆነ ነው። በዚህም ምክንያት
ያውም በአሜሪካ ውስጥ የግእዝን ቋንቋ፤ ቅኔን ከነዜማልኩ እና ከነታሪካዊ አመጣጡ ተንትና የምታስረዳ ሴት ባለ ቅኔን ማየት እንደ
ተአምር የሚቆጠር ነው።
የዛሬዋ እንግዳቺን ባለትዳርና የልጆች እናት ስትሆን
የምትኖረውም በሰሜን አሜሪካ ውስጥ ነው።
ይህቺ እኅት የግእዝን ቋንቋ አጣርታ የምታውቅ
ስትሆን ቋንቋውን ብቻ አይደለም የቅኔ ምሁር ናት፤ከዚያም አልፋ ቅኔውን እስከ ዜማው አሳምራ ተምራለቺ።
የዚች ባለቅኔ እኅታችን የግእዝን ቋንቋ በምናጠናበት
በዚህ በአውደ ጥናት መድረክ መቅረብ ለብዙዎቻችሁ በተለይ ለሴቶች እኅቶቻችን እጅግ ታላቅ መልእክት ያለውና ለትምህርት የሚያነሣሳ
ማነኛውም ትምህርት የፆታ ልዩነት የማይገድበው መሆኑን የሚያሳይ መልካም
አርአያ የሚሆን ነው ብየ አምናለሁ። መልካም ግንዛቤ ።ሌሎችም እንዲያዩት ማድረግን እና አስተያየታችሁን እና አድናቆታችሁን መጻፍን
አትርሱ
No comments:
Post a Comment