Know the New Year/አዲስ ዓመቱን ይወቁ
የአዲሱ ዓመት መጠሪያና ዕለት
የዘመኑን ወንጌላዊ ወይም ዓዲሱ ዓመት በየትኛው
ወንጌላዊ ስም የሚሰየም መሆኑን ለማወቅ የሚፈለግበዎ ቀላል የመደመርና የማካፈል እውቀት ብቻ ነው።
ስለዚህ አዲስ ዓመት ከአራቱ ወንጌላውያን (ማቴዎስ፤ማርቆስ፤ሉቃስ፤
እና ዮሐንስ) ውስጥ በየትኛው እንደሚሰየም ወይም ዘመኑን የሚረከበው ወንጌላዊ ማን እንደ ሆነ ለማወቅ ሁለት ነገሮችን ደምረው ለ
4 (አራቱ ወንጌላውያን) ያካፍሉ።
ከሁሉም በፊት የሚከተሉትን ስሞች ያስታውሱ
ዓመተ ዓለም፡ ዓመተ ዓለም የሚባለው ከክርስቶስ በፊትና ከክርስቶስ በኋላ ያሉት ዘመናት ተደምረው የሚሰጡት
ውጤት ወይም ዘመን ነው።
ከክርስቶስ በፊት የነበረው ዘመን በእምነቻችን
መሠረት
5500 ዘመን (ዓመታት) ነው፡፡ ይህም ዓመተ ፍዳ፤ ዓመተኵነኔ ይባላል።
ከክርስቶስ በኋላ ያለው ዘመን (ዓመተ ምሕረት
ወይም የድኅነት ዘመን) ሲባል በዚህ ዓመት እንደ አገራችን አቆጣጠር 2006 ፤
እንደ ፈረንጆቹ ደግሞ 2014 ዓመት ወይም ዓመታት መሆኑ ነው።
5500+2006=7506 ይሆናል። ይህ ዓመተ
ዓለም ይባላል።
ዓመተ ዓለም ወይም 7506 ሲካፈል ለ 4(አራቱ ወንጌላውያን) ማለትም 7506
4 ለ4 (አራቱ ወንጌላውያን) ተካፍሎ የሚቀረው ትርፍ ቁጥር
1 ከሆነ አዲሱ ዘመን የማቴዎስ
2 ከሆነ የማርቆስ
3 ከሆነ የሉቃስ
0 ወይም ምንም ሳይተርፍ ከተካፈለ የዮሐንስ
ነው ማለት ነው።
የወንጌላውያንን መጠሪያ ቁጥር ወይም ቅደም ተከተላቸውን
ማወቅ ከፈለጉ መጽሐፍ ቅዱሰዎን ይግለጡ። መጀመሪያ የሚያገኙት ወንጌል(መጽሐፍ) ማን እንደሆነ ይመልከቱ ማለትም መጀመሪያ ለሚያገኙት
ወንጌላዊ 1 ቁጥርን ይስጡ፤ ሁለተኛ ለሚያገኙት 2 ቁጥርን፤ ሦስተኛ ለሚያገኙት 3 ቁጥርን፤
አራተኛ ለሚያገኙት 4 ቍጥርን ይስጡ። ስለዚህ ቅደም ተከተላቸውን አወቁ ማለት
ነው። ይህ ቅደም ተከተላቸው መጠሪያ ወይም መለያ ስማቸው ነው።
ዓመተ ዓለሙ ለ4 ስለሚካፈል 4 ቀሪ ሊሆን አይችልም በመሆኑም ያለምንም ቀሪ ከተካፈለ 4 እንደ ቀረዎ ወይም ያለምንም ቀሪ ተካፈለ ማለት 0 ቀሪ ማለት ነው። በዚህ ጊዜ ዘመኑ ዮሐንስ ነው ማለት
ነው።
አዲስ ዓመት ወይም መስከረም አንድ ቀን ከሳሙንቱ
ዕለታት በየትኛው ቀን ወይም ዕለት እንደሚውል ለማወቅ የሚከተሉትን ስሌቶች ይሥሩ።
ዓመተ ዓለም (ከክርስቶስ በፊትና ከክርስቶስ በኋላ
ያለው ዘመን) ማለትም 5500+ዓመተ ምሕረት ማለት ነው ሲደመር ወንጌላዊውን ለማግኘት ለአራት አካፍለው ያገኙትን ውጤት ቀሪውን
ሳይጨምር ማለት ነው ደምረው ለ7 ማለትም ለሰባቱ ዕለታት ያካፍሉ። ለሰባት ተካፍሎ የሚቀረውን ቀሪ ቁጥር እንደ ሚከተለው ይመድቡ
ወይም ይስጡ ወይም ይሰይሙ። ቀሪው
1 ከሆነ ማክሰኞ ማለት ነው
2 ከሆነ ረቡዕ
3 ከሆነ ሐሙስ
4 ከሆነ ዓርብ
5 ከሆነ ቅዳሜ
6 ከሆነ እሁድ
ምንም ቀሪ ከሌለ ወይም ዜሮ (0) ከሆነ ሰኞ
ማለት ነው ።
አንድ ቍጥር ለማክሰኞ የተሰጠበት ምክንያት ወይም
ማክሰኞ በአንደኛ ተራ ቋጥር የተቀመጠበት ምክንያት ወይም የሳምንቱ መጀመሪያ ማክሰኞ የሆነበት ምክንያት በሥነ ስሌት ትምህርት ማክሰኞ
“ጥንተ ቀመር” ይባላል። ጥንተ ቀመር ማለት ሥሌት ወይም ቆጠራ፤ አቆጣጠር ወዘተ ማለት ነው። ስለዚህ ጥንተ ቀመር ሲባል የሥሌት
መጀመሪያ ማለት ነው። ሥነ ሥሌት ወይም ቆጠራ የተጀመረው በዕለተ ማክሰኞ ነው ተብሎ ስለሚታመን ማክሰኖ በሥነ ሥሌት ትምህርት የቀኖች
መጀመሪያ ነው።
ከዚህ ቀጥለን ቍጥሮችን ብቻ በምሳሌነት በቀላሉ
እናያለን። ከዚህ በላይ የተዘረዘረውን ሁሉ ማወቅ አይጠበቅባችሁም ብቻ የሚከተሉትን ቁጥሮች በትክክል መደመርና ማካፈል ቀሪውን ለሚገባው
ወንጌላዊና ዕለት መስጠት ብቻ ነው።
1፡ ዓመተ ዓለም፡ ማለት 5500+ ዓመተ ምሕረት ማለት ነው ለምሳሌ ዓሁን ያለንበት ዓመተ ምሕረት እንደ ኢትዮጵያ
አቆጣጠር 2006 ዓ/ም እንደ ፈረንጆቹ ደግሞ 2014 ዓ/ም ነው። ስለዚህ ዓመተ ዓለም ሲባል 5500+2006 =7506 ወይም 5500+2014 = 75014 ይሆናል።
የሚቀጥለውን ወይም የ2007ን ለማወቅ የራሱን
ማለትም ማወቅ የምንፈልገውን ዘመን ማለትም የሁለትሺ ሰባትን(2007ን) ወንጌላዊ
ወይም የሚውልበትን ዕለት ማወቅ ስለምንፈልግ የ2007ን ዘመን መጠቀም አለብን ። የ2006ን ማወቅ የምንፈልግ ከሆነም ራሱን
2006 መጠቀም አለብን።
አሁን ምሳሌውን በጥንቃቄ እንመልከት ምሳሌያችን
የ2006ን ወንጌላዊና የዋለበትን ዕለት ለማወቅ ስለሆነ የምንጠቀመው ራሱን የ2006ን ዘመን ነው።
ምሳሌ 1፡ የ2006 ዓ/ም ወንጌላዊ ማነው?
5500+2006=7506
4=1876 ደርሶ 2(ሁለት) ይቀራል።
ሰለዚህ የ2006 ዓ/ም ወንጌላዊ ማርቆስ ነበር ወይም ነው ማለት ነው።
ምሳሌ2፡ የ2006 ዓ/ም አዲስ ዓመት የዋለበት
እለት ወይም ቀን ማን ነበር?
7506+1876=9381
7=1340 ደርሶ 2(ሁለት) ይቀራል።
ስለዚህ የ2006 ዓ/ም አዲስ ዓመት የዋለበት እለት ወይም ቀን ረቡዕ ነበር ማለት
ነው።
ዓመተ ፍዳ + ዓመተ ዓ/ም ወጤቱን ለ4 በማካፈል
ወንጌላዊውን ያገኛሉ።
ዓመተ ዓለሙን እና ዓመተ ዓለሙ ለ4 ተካፍሎ የተገኘውን
ውጤት ደምረው ለ7 በማካፈል የዓዲሱን ዓመት መጀመሪያ ቀን ያውቃሉ ። (ዓመተ ፍዳ+ ዓመተ ምሕረት ሲካፈል ለ4 = ወንጌላዊ። ዓመተ
ዓለም + ለ4 ተካፍሎ የተገኘው ውጤት ሲካፈል ለ7 = የዓዲስ አመት መጀመሪያ ቀን) ይሆናል።
አሁን የ2007ን ወንጌላዊና የሚውልበትን ዕለት
ማግኘት የ እናንተ ድርሻ ይሆናል።
5500+2006=7506÷4=1876 ደርሲ ቀሪ
2 = 2ኛው ወንጌላዊ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዓመተ ዓለም= 5500+ ዓመተ ምህረት (5500+2007=7507)
7507(ዓመተ ዓለም) ÷4 = 1876 ተካፍሎ ቀሪ 3 ይሆናል ስለዚህ
ሦስተኛው ወንጌል
የዘመኑ ወንጌላዊ ነው ማለት ነው።
ዓመተ ዓለም (7507)+1876 = 9383÷7=1340 ደርሶ 3
ይቀራል በሥነ ስሌት ትምህርት ከሳምንቱ 3ኛው ቀን ሐሙስ ስለሆነ የ2007 ዓ/ም አዲስ ዓመት ሐሙስ ይውላል፡
ዘመኑ ሉቃስ ዕለቱ ሐሙስ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር