Tuesday, January 31, 2017

ልሣነ ግእዝ መግቢያ 2

ሰላም ለክሙ ፍቁራነ ልሣነ ግእዝ "ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን" መግቢያ ሁለት እንሆኤ! ከ7 ቀናት በኋላ ዋናው ትምህርት ይጀመራል፤ የመጀመሪያ ትምህርት ለምንማረው ርእስ መሠረት ስለሆነ በዝግጅት መቅረብን ወይም መከታተልን አትርሱ፤ ላልሰሙ አሰሙ፤ ሸር አድርጉ ፤ ሐሣባችሁን ግለጡ፤ ከወደዳችሁትም ላክ አድርጉ፤ መልካም ትምህርት! ከአውደ ጥናት

Monday, January 16, 2017

ልሣነ ግእዝ በ/ር መላኩ

Selam Everyone, Awde Tinat will start to teach Ge'ez Language based on the new publishe book "Lisane Ge'ez" yegara quanquachi. In order to spread this news, please Share,Share, and Share to every one you know. ሰላም አርድእተ ግእዝ፣ "ልሣነ ግእዝ" የጋራ ቋንቋችን በተሰኘው አዲስ መጽሐፍ መሠረት በአውደ ጥናት አዲስ የግእዝ ትምህርት በዚህ ወር ሊጀመር ስለሆነ ይህንን ዜና ላልሰሙት በማስተላለፍ እንድታሰሙ ተጋብዛችኋል።

Wednesday, August 3, 2016

ልሣነ ግእዝ መጽሐፉን ለመግዛት



Lisane Geez Yegara Quanquachin/ ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የተሰኘውን ይህንን የግእዝ ቋንቋ መማርያ ክፍል አንድ መጽሐፍ ከአማዞን ለመግዛት ይህንን ይጫኑ.

Lisane Geez Yegara Quanquachin

Friday, June 3, 2016

ክፍል 34 ተናባቢ ፊደላት


ተናባቢ ሆሄያት


ተናባቢ ማለት ተያያዥ ማለት ሲሆን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ቃላት በአንድ ላይ ተያይዘው ሲጻፉና ሲነበቡ “ተናባቢ”ወይም ኃረግም ይባላሉ። ባለቤትነትን ከምናመለክትባቸው መንገዶች መካከልም ተናባቢ ቃላት ናቸው። 

ቃላት የሚናበቡበት ምክንያት ለሦስት አበይት ሥራዎች ነው
1.      ባለቤትነትን ወይም ባለንብረትነትን ለመጠቆም ወይም ለማመልከት
2.     ምንነትን ማንነትን ወዘተ ለመግለጽ
3.     ንግግርን ለማራዘምና ሥርዓተ ዜማን  ወይም ንባብን ለማስተካከል የሚሉት ሲሆኑ ከነዚህም ውጭ  ሌሎች ተመሳሳይ  አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።

ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ቃላትን ለማናበብ የምንፈልገውን ቃል ወይም ንብረቱን መጀመሪያ ላይ፤ ባለንብረቱን ቀጥለን እናስቀምጣለን ፤ሆሄያትን ለማናበብ  የቃሉን የመጨረሻ ሆሄ መሠረት ያደረገ ሕግን መከተል አለብን። ይህም

·       ሳልስን ወደ ሐምስ (በሣልስ የሚጨርስ ቃል ሲሆን ማለት ነው)
·       ሳድስን ወደ ግእዝ መቀየር አለብን (በሳድስ የሚጨርስ ቃል ሲሆን ማለት ነው)
·       ግእዝ(በግእዝ ሆሄ የሚጨርስ ቃል)
·       ራብዕ(በራብዕ ሆሄ የሚጨርስ ቃል)
·       ሐምስ (በሐምስ ሆሄ የሚጨርስ ቃል) እና
·       ሳብዕ (በሣብዕ ሆሄ የሚጨርስ ቃል)  ሳይቀየሩ መናበብ ይችላሉ::

ምሳሌ፦ በግእዝ “መጽሐፍ” ማለት በአማርኛም በቁሙ መጽሐፍ ነው፤ ይህ የያዝሺው ወይም የያዝከው  የምታነቡት ማለቴ ነው መጽሐፍ የማን መሆኑን ከምንገልጽባቸው መንገዶች አንዱ  በማናበብ ነው ብለናል ስለዚህ “መጽሐፍ” የነበረውን ቃል  ከባለ መጽሐፉ ጋር ለማናበብ ማለት መጽሐፉ የማን እንደሆነ ለመናገር ቃሉ በሳድስ ከጨረሰ ወደ ግእዝ ይቀየራል ብለናል ስለዚህ መጽሐፍ የሚጨርሰው በሳድስ ስለሆነ የመጨረሻዋን ሳድስ ፊደል ወደ ግእዝ በመቀየር “መጽሐፈ መላኩ” ብትሉ ወደ አማርኛ ሲቀየር “የመላኩ መጽሐፍ” ይሆናል። ስለዚህ መጽሐፉ የማን ንብረት ነው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ የመላኩ ይሆናል። 

ተናባቢ ቃላትን ስንተረጉም ብዙ ጊዜ “የ” የሚል አመልካች ሆሄ ከሁለቱ ቃላት መካከል ይወጣል። የሚከተሉትን ምሳሌዎች ይመልከቱ
·        መጽሐፈ ነገሥት = የነገሥታት መጽሐፍ

https://amzn.to/2IhIfvs
·       

የክርስትና ስም ሁሉ ተናባቢ ነው
መድኃኔ ዓለም= የዓለም መድኃኒት
·        ጽጌ ገነት = የገነት (የጓሮ) አበባ
·        ደመና ሰማይ =  የሰማይ ደመና
·        ተወክፎ ነግድ = እንግዳን መቀበል
















Sunday, March 13, 2016

ግእዝ ክፍል 33

Ge'ez Lessons for beginners part 33














እም (እምነ) ጳውሎስ ሐዋርያሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ በትእዛዘ እግዚአብሔር መድኃኒነ ወኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋነ፡ ለጢሞቴዎስ ወልድየ ዘአፈቅር በሃይማኖት፤ ሰላም ለከ ወሣህል ወጸጋሁ ለእግዚአብሔር አቡነ ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ።

 እስመ አስተበቋዕኩከ ትንበር ኤፌሶን (በኤፌሶን) አመ አሐውር መቄዶንያ ከመ ትገሥጾሙ ከመ ኢያምጽኡ ካልአ ትምህርተ።

ጸጋ ምስሌከ ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን።

ዝንቱ መልእክት ተጽሕፈ በእደ ጳውሎስ በውስተ አቴና ወተፈነወ በእደ ቲቶ ኀበ ጢሞቴዎስ።

በመድኃኒታችን በእግዚአብሔር አብ፤ በተስፋችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝ ለኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆንኩ ከእኔ ከጳውሎስ በእምነት(በሃይማኖት) ለምወደው ለልጄ ለጢዎስ።
እንደምን አለህ? (ሰላም ለአንተ ይሁን)፤ ይቅርታም ይደረግልህ፤ የአባታችን የእግዚአብሔር የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋው(ስጦታው)  ይደርብህ (ይደረግልህ)፤
ወደ መቄዶንያ በሄድኩ ጊዜ ሌላ (እንግዳ ትምህርትን እንዳያመጡ (እንዳይማሩ) ትመክራቸው ዘንድ በኤፌሶን እንድትቆይ ለመንኩህ----።


ጸጋ ይደርብህ፤
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን
ይሁን

ይህ መልእክት በአቴና ውስጥ በጳውሎስ እጅ ተጽፎ በቲቶ እጅ ወደ ጢሞቴዎስ ተላከ።