Monday, August 31, 2015
Tuesday, August 11, 2015
ግእዝ ክፍል 17
Part 17 inside The paradise
እግዚአብሔር፣ አዳም፤ ሔዋን፤ እና እባብ
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአዳም፡
“.. አይቴ ሀሎከ አዳም.. ?
ይቤሎ አዳም ለእግዚአብሔር
“.. ሰማዕኩ ቃለከ እንዘ ታንሶሱ ውስተ ገነት ወፈራህኩ እስመ ዕራቅየ አነ ወተኀባእኩ.. ”
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአዳም፡
“.. መኑ አይድዐከ ከመ ዕራቅከ አንተ እም ዕፅኑ ዘአዘዝኩከ ከመ ኢትብላዕ እምኔሁ በላእከ?.. ”
ይቤሎ አዳም ለእግዚአብሔር
“.. ብዕሲት እንተ ወሀብከኒ ምስሌየ ትንበር ይእቲ ወሀበተኒ ወበላእኩ-”
ይቤላ እግዚአብሔር ለብእሲት(ሔዋን)
“.. ለምንት ገበርኪ ዘንተ?.. ”
ትቤሎ ብእሲት፡ ለእግዚአብሔር
“.. አርዌ ምድር አስፈጠተኒ ወበላእኩ.. ”
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአርዌ ምድር
“.. እስመ ገበርኮ ለዝንቱ ግብር ርጉመ ኩን እምኵሉ እንስሳ ወእምኵሉ አራዊተ ምድር ወበ እንግድዓከ ሑር ወመሬተ ብላዕ..”
ይቤላ እግዚአብሔር ለብእሲት(ሔዋን)
“.. (ብዙኃ) አብዝኆ አበዝኆ ለኀዘንኪ ወለሥቃይኪ ወበጻዕር ለዲ..”
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአዳም፡
“.. እስመ ሰማዕከ ቃለ ብእሲትከ ወበላዕከ እም ውእቱ ዕፅ ባሕቲቱ ዘአዘዝኩከ ከመ ኢትብላዕ ርግምተ ትኩን ምድር…”
Friday, August 7, 2015
Wednesday, July 29, 2015
Friday, July 24, 2015
ግእዝ ጽሁፍ ክፍል 28 ዘንድ አንቀጽ
Ge'ez Lessons for Beginners part 28 text (ዘንድ አንቀጽ = in order to)
መሀረ = አስተማረ (ያለፈ ድርጊት) past
ይምህር= ያስተምራል (ወደፊት የሚደረግ ትንቢት) futur
ይምሀር= ያስተምር ዘንድ (ምክንያታዊ ) in order to
እርማት፡ መሀረ = አስተማረይሜህር
እርማት፡ መሀረ = አስተማረይሜህር
ይምሀር
ይምሀር
መሐረ = ይቅር አለ የሚለው ግስ ሲሆን ነው ይምህር በማለት የሚረባው። መሀረ = አስተማረ የሚለው ግን መሀረ (ሐላፊ) ይሜህር (ትንቢት) ማለትም በትንቢት (በሁለተኛው ግስ) የሚገኘው ሆሄ "ም" ሳይሆኝ "ሜ" (ይሜህር) ይሆናል።
ተንሥአ ይምሀር መምህረ ግእዝ =የግእዝ መምህር ያስተምር
ዘንድ ተነሣ
ዘንድ አንቀጽ = In order to
ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች በክፍል 25 ስለ አራቱ
አበይት አናቅጽ ስለ
1.
ሃላፊ፤
2.
ትንቢት፤
3.
ዘንድ እና
4.
ትዕዛዝ (ዘንድ እና ትዕዛዝ
ሳልሳይ ወይም 3ኛ ይባላሉ) ጠቅለል ባለ መልኩ ተምረን ነበር።
በድጋሚ ለማስታዎስ ያህል
ግሦቹ የሚከተሉት ናቸው።
ሖረ= ሄደ ሃላፊ አንቀጽ
ይሐውር= ይሄዳል ትንቢት አንቀጽ
ይሑር= ይሄድ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይሑር= ይሂድ ትእዛዝ አንቀጽ
በመሆኑም እነዚህን ግሦች መሠረት አድርገን እንደ
መግቢያ ከተማርን በኋላ በመቀጠልም አንድ በአንድ በክፍል 26 ስለ
ሃላፊ ግሥ ወይ አንቀጽ፤ በክፍል 27 ስለ ትንቢት ግሥ ወይም አናቅጽ ተምረናል።
በዛሬው በክፍል 28 ትምህርታችን ደግሞ
ስለ ዘንድ አንቀጽ እንማራለን። ዘንድ አንቀጽ ሳልሳይ ተብሎም
ይጠራል ።ሦስተኛ ማለት ነው። ምክንያቱም በሦስተኛ ተራቁጥር ስለሚገኝ ነው። ዘንድ አንቀጽ
የሚባለውም ዘንድ ተብሎ ስለሚተረጎም ነው። (ይሄድ ዘንድ)
ዘንድ አንቀጽ ከአበይት ግሦች ሦስተኛው አንቀጽ ሲሆን በቀጥታ ማሠሪያ አንቀጽ አይሆንም ማለትም
አያሥርም። (ውእቱን መርምሮ ካልሆነ በስተቀር)፤
ስለዚህ ሌላ ተጨማሪ አንቀጽን ይፈልጋል። ውእቱ (ገብረ ሥላሴ) ተንሥአ ይሁር = እሱ ይሄድ ዘንድ ተነሣ፤ ብንል የዚህ ዐረፍተ ነገር
ማሠርያ የሆነው “ተንሥአ”
የሚለው ግሥ ሲሆን ይሁር
የሚለው ምክንያቱን ይገልጻል እንጂ አያሥርም። ስለዚህ በዚህ ዐረፍተ ነገር ሁለት አበይት ግሦች ሲኖሩ አንዱ ብቻ ማሠሪያ ሆነ።
ለዚህም ነው ዘንድ አንቀጽ በቀጥታ ስለማያሥር ሌላ ሁለተኛ አንቀጽን ይሻል ያልነው።
ዘንድ አንቀጽ አገባባዊ ባሕርይ አለው፤ (ከመ ከሚለው አገባብ ጋር ተመሳሳይ ትርጉም እና ሥራ
አለው። ሁለቱ ማለትም ከመ
እና ዘንድ አንቀጽ በአንድ ላይ
ይነገራሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ዘንድ አንቀጹ
የተለመደውን ትርጉሙን ሲይዝ “ከመ”
የሚለው አገባብ የዘንድ አንቀጹ ሞገሥ ወይም አጃቢ ይባላል።
ለምሳሌ
መርድእ ሖረ ከመ ይትመሀር ልሣነ ግእዝ = ተማሪ የግእዝን ቋንቋ ይማር ዘንድ ሄደ። በዚህ ዐ/ነገር ላይ ከመ የይትመሀር አዳማቂ ሆነ
እንጂ ሌላ አገልግሎት አልሰጠም። ምክንያቱም “ይትምሀር” የሚለው ግሥ ራሱ ትርጉሙ “ይማር
ዘንድ” የሚል ነው። ልዩነታቸው ዘንድ አንቀጽ አንቀጽም
ነው እንደ አገባብም ይተረጎማል፤ “ከመ” ግን “እንደ” የሚል ትርጉም ነው ያለው። ስሙም አገባብ ይባላል። ለሁለቱም ማለትም ለዘንድ አንቀጽና “ከመ” ለሚለው አገባብ ምሳሌዎቹን ተመልከቱ
መነኮስ ቆመ ከመ ይጼሊ= መነኩሴ ይጸልይ ዘንድ ቆመ።
መነኮስ ቆመ ይጸሊ = መነኩሴ ይጸልይ ዘንድ ቆመ።
በነዚህ በሁለቱ ዐረፍተ ነገራት መሠረት ዘንድ አንቀጽና “ከመ” የሚለው አገባብ
ተመሳሳይ አገልግሎት አላቸው። ነገር ግን “ከመ” ከአንቀጽ ጋር በመሆን አንቀጹ እንዳያሥር ለመከላከል ነው የሚያገለግለው፤ ዘንድ
አንቀጽ ግን ብቻውን በመሆን ነው የሚነገረው የራሱ የሆነ አገባባዊ
ባሕርይ አለው ማለት ነው።
ዘንድ አንቀጽ ከሁሉም ግሦች (ከሐላፊ፤ከትንቢት፤
እና ከትእዛዝ አናቅጽ ) ጋር አብሮ ይሠራል።
ምሳሌ፡
·
ይብላእ ሆረ
= ይበላ ዘንድ ሄደ (ሃላፊ)
·
የሐውር ይብላእ=
ይበላ ዘንድ ይሄዳል (ትንቢት)
·
ይሁር ይብላእ= ይበላ ዘንድ
ይህድ(ትእዛዝ)
ዘንድ አንቀጽ በዓረፍተ ነገር ሲገባ ለሌላ ድርጊት ወይም አንቀጽ እንደ ምክንያት በመሆን ይገባል።
ለምሳሌ “ መርድእ ሖረ ይትምሀር” ቢል የዓረፍተ
ነገሩን ባለቤት የጎዞ ምክንያት ይገልጽለታል። ማለትም ተማሪው የሄደበት ምክንያት “ይማር ዘንድ” ወይም ለመማር ነው። በማለት ምክንያቱን
ገለጸለት ማለት ነው።
ከግሡ መጀመሪያ ላይ ባእድ ሆሄን ይጨምራል ሆሄያቱም “አሥራው” ይባላሉ
ምሳሌ
መሀረ መሠረታዊ ግሥ ሲሆን
ይትመሀር
“ይ እና ት’ ባእድ ሆሄ ይባላሉ ። ምክንያቱም ከመሠረታዊው ግሥ ያልነበሩ የመሠረታዊው ግሥ ወገን ስላልሆኑ
ነው። ከግሡ መጀመሪያ ላይ ስለሚገኙ ደግሞ “አሥራው” ይባላሉ በአማርኛ ሥሮች
ማለት ነው፤፡
ስለዚህ ለማጠቃለል ያህል የዘንድ አንቀጽ መሠረታዊ
ወይም አበይት መለያዎችን ባጭሩ እንደሚከተለው ይመልከቱ።
·
ዘንድ አንቀጽ ከአበይ አናቅጽ መካከል ሦስተኛው አንቀጽ ነው በዚህም ሳልሳይ “ሦስተኛ” ይባላል
·
ዘንድ ተብሎ ስለሚተረጎም “ዘንድ አንቀጽ” እየተባለ ይጠራል። ስለዚህ ስሙ ከትርጉም ጋር የተያያዘ ነው።
·
ብቻውን ስለማያሥር ሌላ ግሥ (ሃላፊ፤ ትንቢት፤ ወይም ትእዛዝ “ አናቅጽ) ያስፈልገዋል።
·
ከሁሉም አበይ አናቅጽ ማለትም ከሃላፊ፤ከትንቢት፤ እና ከትእዛዝ አናቅጽ ጋር እየተቀናጀ ያገለግላል
·
አገባባዊ ትርጉምና ሥራ አለው። ለምሳሌ “ከመ” ከሚለው አገባብና ከመሰሎቹ ጋር በትርጉምና በአገልግሎት ይመሳሰላል
·
ሁለት ነገሮችን በአንድ ላይ ይዟል፡ ዘንድ የሚል አገባብ(ከ) እና አንቀጽ “ያእምር”= ያውቅ ዘንድ= ያውቅ(አንቀጽ) ዘንድ=አገብባብ(ከ) ስለዚህ አገባብና አንቀጽ በአንድ ላይ ይበኙበታል።
·
የዐረፍተ ነገርን ምክንያታዊ ተግባር ይገልጻል
·
ከግሡ መጀመሪያ ላይ “አሥራው የሚባሉትን ሆሄያት ይጨምራል።
Friday, July 10, 2015
Sunday, June 28, 2015
ግእዝ ክፍል 27 ትንቢት አንቀጽ
ክፍል 27 ትንቢታዊ አንቀጽ/ ካልዓይ
ባለፉት ሁለት ተከታታይ ክፍሎች ማለትም በክፍል
25 ስለ አበይት አናቅጽ፤ማለትም ስለ ሐላፊ ወይም ቀዳማይ፤ ትንቢት ወይም ካልአይ፤ እንዲሁም ዘንድ እና ትእዛዝ ወይም ሳልሳይ፤
ስለሚሉት ግሦች ጠቅለል ባለመልኩ ተምረናል። በክፍል 26 ደግሞ ከነዚሁ 4 አናቅጽ መካከል አንዱ ስለሆነው ስለ ሐላፊ ግሥ ተምረናል።
ዛሬ ደግሞ ስለ ትንቢት ወይም ካልአይ አንቀጽ እንማራለን።
ትንቢት ወይም ካልአይ ተብሎም ይጠራል። ካልአይ ሁለተኛ ማለት ነው
በግእዝ ቋንቋ የመጀመሪያው ግሥ ሐላፊ ነው፤ ማለትም
ማነኛውም የግእዝ ግሥ ተጽፎ የሚገኘው በሐላፊ ጊዜ ነው። ቀጥሉ ሁለተኛው ትንቢት ወይም ካልአይ ይባላል። (ስናረባው ማለት ነው)
ስለዚህ ዛሬ ከግሥ ርባታ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ስለሚገኘው ስለ ትንቢት አንቀጽ እንማራለን ማለት ነው። ለምሳሌ
ግሡ “ወሀበ”
ቢሆን ይህ ግሥ “ሐላፊ” ይባላል። ምክንያቱም ትርጉሙ ሰጠ ማለት ነው። ሰጠ ማለት ደግሞ ያለፈ ድርጊትን
ነው የሚነግረን። የዚህ ግሥ ሁለተኛው ወይም ትንቲታዊው “ይሁብ” ይሆናል። ይሁብ
ማለት ደግሞ ይሰጣል ማለት ነው። ይሰጣል ስንል ያለፈ ድርጊት ሳይሆን ወደፊት
የሚደረግ ነው። ስለዚህ ትንቢት አንቀጽ የሚባለው ለዚህ ነው።
የትንቢት አንቀጽ አበይት መለያወች እና አገልግሎቶች
1.
ወደ ፊት ለሚደረግ ድርጊት
የሚያገለግል ነው (Futur tense )
2.
ተዘውትሮ ለሚደረግ () ድርጊትም
ይሆናል(present tense)
3.
አገባቦችን በመጠቀም በመደረግ
ላይ ለሚገኝ ድርጊትም ይሆናል።(present continuous) ስለዚህ በብዙ ዓይነት መልኩ
እንጠቀምበታለን ማለት ነው።
4.
ከግሡ መጀመሪያ ላይ ባእድ
ሆሄን ይጨምራል (እነዚህ ባዕድ ሆሄያት ስማቸው አሥራው ሲባሉ ቁጥራቸው 4 ነው። በአማርኛ “ሥሮች” ማለት ነው። ይ፤ት፤ን፤እ፤ ናቸው።
በ ሀ እና በ አ ግሦች ግዕዛቸውና
ራብአቸውም ይገኛል። (በትንቢት ፤ በዘንድ፤ በትእዛዝ፤ አናቅጽ ብቻ የሚገቡ ናቸው) ለወደፊቱ ስለነዚህ ፊደላት ሙሉ ትምህርት እንማራለን፤
ለአሁኑ ግን ጠቅለል አድርገን ነው የምናያቸው።
ከዚህ ቀጥሉ ካልአይ ግሥ ለትንቢታዊ ፤ ተዘውትሮ ለሚደረግ፤
እና በመደረግ ላይ ላለ ድርጊት እንዴት እንደሚገባ እናያለን። በመጨረሻም ስለሚጨምራቸው ባዕድ ፊደላት በሦስት ግሦች እንደ ምሳሌ
እናያለን።
መሳሌ፡1 ለትንቢታዊ ድርጊት
·
አነ አሀውር
ኀበ ብሔረ ግብፅ ድኅረ ሰለስቱ ዓመታት
ምሳሌ፡2 ዘወትር ለሚደረግ ድርጊት
·
“ይብል ዓብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር”
(ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል)
·
አንትሙ ተአምሩ
ልሳነ ግእዝ
·
ሕጻን ይበኪ እንዘ ይበልእ
ምሳሌ 3፡ በመደረግ ላይ ላለ ድርጊት
ምንተ ትገብሩ አኀውየ? እንዘ ንትሜሀር ልሳነ ግእዝ
ምሳሌ
4፡ ከግሡ መጀመሪያ ላይ ባእድ ሆሄን ሲጨምር
ሰአለ
=ይስእል (ለመን)
ባረከ=ይባርክ
ገብረ=ይገብር
Subscribe to:
Posts (Atom)



