Sunday, November 21, 2021
Saturday, November 20, 2021
Sunday, October 31, 2021
Friday, October 1, 2021
የ2014/2022 ዓ/ም የግእዝና የአማርኛ ቋንቋዎች ትምህርት በአውደ ጥናት ዘግእዝ ምዝገባ ተጀምሯል!
ለግእዝና ለአማርኛ ትምህርት ይመዝገቡ!
Wednesday, September 29, 2021
Sunday, July 11, 2021
Sunday, May 16, 2021
የመጻሕፍት ትርጓሜ፡ አራተኛው የቤተ ክህነት ትምህርት ክፍል
- የብሉያት = 46 መጻሕፍት
- የሐዲሳት = 35 መጻሕፍት
- የሊቃውንት = 3 መጻሕፍት
- የመጽሐፈ መነኮሳት = 3 ክፍሎች ያሉት አንድ መጽሐፍ ትርጓሜ ዎች ናቸው፡
የትርጓሜ መጻሕፍት
ትርጓሜ መጻሕፍት የሚባለው የትምህርት ክፍል ከስያሜው እንደምንረዳው የቅዱሳት መጻሕፍትን ተደራራቢ
ትርጉም እና ምሥጢር በማመሥጠርና በማራቀቅ ታሪካዊ ምንጫቸውንና ማስተላለፍ የሚፈልጉትን መንፈሳዊ መልእክት በመረዳት ማስረዳት ነው፤
የትርጓሜ መጻሕፍት ትምህርትን መማር የሚችለው የቅኔ ትምህርትን የተማረ ተማሪ ብቻ ነው።
ትርጓሜ መጻሕፍት የሚባለው የትምህርት ክፍል በአራት አበይት ክፍሎች ይከፈላል፤ እነሱም
ከዚህ በታች በተራ በቅደም ተከተል የተጠቀሱት ናቸው።
1. መጻሕፍተ
ብሉያት - 46ቱ የበሉይ ኪዳን መጻሕፍት
2. መጻሕፍተ
ሐዲሳት - 35ቱ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት
3. መጻሕፍተ
ሊቃውንት - ሐይማኖተ አበው፣ ፍትሐ ነገሥት፣ አቡሻክር (ባህረ ሐሳብ)
4. መጻሕፍተ
መነኮሳት - ማርይሳቅ፣ ፊልክስዮስ፣ አረጋዊ መንፈሳዊ
በነዚህ የትምህርት ደረጃዎች ሁሉ መምህራኑ የእምነትን የገብረ ገብነትን እና የትህትናን ባጭሩ የመልካም
ሥነ ምግባርን ትምህርት ያስተምራሉ። እነዚህም
·
ፈሪሀ እግዚአብሔርን- እግዚአብሔርን መፍራት
·
ኀፊረ ገጽን - ታላላቆችን ማክበርና በአክብሮት መፍራት
·
አትሕቶ ርእስን - በታላላቆች ፊት በትህትና ራስን ዝቅ አንገትን ደፋ ማድረግ
·
ገቢረ ሠናይ - መልካም ነገርን መሥራት ወይም ማድረግ ወዘተ ናቸው።
·
ምንጭ፡ “ትዝታዬ” መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ
የመጻሕፍትን ትርጓሜ ትምህርት የጀመሩት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት እንደሆኑ የመጻሕፍት ትርጓሜ ሊቃውንት
ይተርካሉ።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ
