Saturday, March 28, 2020

Corona Virus/ኮሮና ቫይረስ

Corona Virus/ኮሮና ቫይረስ 


Corona Virus/ኮሮና ቫይረስ ስያሜ የመተላለፊያ መንገዶች፣ መከላከያ እና ማብራርያ


ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው። ምሕረትና ቸርነት የባሕርዩ የሆነ ልዑል አምላክ በቸርነቱ ብቻ በሕይወት ጠብቆ ለዚች ቅጽበት ስላደረሰን የተመሰገነ ይሁን፤ አሁንም በማይለካው ፍቅሩ የተለመደውን ቸርነቱን አይንፈገን። ስለ እናቱ ስለ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምና ስለ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሁሉ ብሎ እንደ በደላችን አይቁጠርብን።

ዛሬ  ይህንን ቪዲዮ ያዘጋጀሁት ዓለምን ከዳር እስከዳር ስለ ተቆጣጠረው፤ ሰብአዊ ፍጡርን ሁሉ ስላስጨነቀውና ግራ ስላጋባው ተላላፊ ወይም ወረርሽኝ በሽታ የጤና ባለሙያዎች የሚናገሩትን በመተርጎም በተቻለኝ መጠን ግልጽና ቀላል በሆነ አማርኛ ለናንተ መረጃ ለመስጠት ነው። ይህ መረጃ የጤና ባለሙያዎች እና የአካባቢያችሁ ባለሥልጣናት ከሚሰጧችሁ መረጃ ጋር ተጨማሪ ሆኖ ሊረዳችሁ፤ ከዚህ በፊት የሰማችሁትን መረጃም  ሊያስታውሳችሁ የሚችል ነው ብየ አምናለሁ።

መጽሐፉን ለመግዛት ይህንን (ራሱ መጽሐፉን) ይጫኑት



የተላከብን ሕመም አዲስና መድሃኒት የሌለው መሆኑን ሁላችንም ሰምተናል። ስለዚህ መድኃኒታችን መድኃኒት ያልተገኘለትን ዓለም ያዳነው መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ መሆኑን እናምናለን፤ እውነትም ነው።

እግዚአብሔር ራሳችንን የምንጠብቅባቸው መሣሪያዎችን ማለትም እያንዳንዳቸውን የሰውነት ክፍሎቻችንን ሰጥቶናል። ስለዚህ በተቻለ መጠን እርሱ እንድንጠቀምባቸው የሰጠንን መሣሪያዎች እየተጠቀምን ራሳችንን ለመጠበቅ መዘጋጀትና ከአቅም በላይ የሆነብንን ደግሞ ሁሉን ለሚችል ለእርሱ መስጠት ይገባናል። ይህ የትክክለኛ አማኝ ሥራ ነው ብየ አምናለሁ።

እኔ የምሠራበት መሥሪያ ቤት ምድቡ ከጤና ማዕከላት ውስጥ ነው። ከ(CDC) ማለትም ከተላላፊ በሽታወች መቆጣጠሪያ ማዕከላት በጣም የቀረበ ክትትል የሚደረግበት መሥሪያ ቤት ነው። ስለዚህ የተሟላ መረጃ በየቀኑ ይሰጠናል። በመሆኑም እናንተም በተለያዩ መንገዶች መረጃውን የምታገኙ መሆናችሁን ባውቅም እኔም በበኩሌ የሰማችሁትን በተለያየ አቀራረብና መንገድ ደጋግማችሁ ብትሰሙት ይጠቅማል ብየ በማሰብ ነው። ያቀረብኩላችሁ እንደሚጠቅማችሁም ርግጠኛ ነው። ምክንያቱም መረጃን የመሰለ ነገር የለም ሲደጋገምም የበለጠ በአእምሮ ይቀረጻል እንጂ አይከፋም። እግዚአብሔር ሁላችንንም በቸርነቱ ይጠብቀን።

መጽሐፉን ለመግዛት ይህንን (ራሱ መጽሐፉን) ይጫኑት


በመጀመሪያ ከስያሜው እነሳለሁ
ስሙን “ኮሮና ቫይረስ” ስርጭቱን ደግሞ “ፓን ደሚክ” በማለት ይጠሩታል። የወረርሽኝን ሕመም “ኤፒ ደሚክ” እና “ፓን ደሚክ” በማለት ይጠሩታል። ቃላቱ መሠረታቸው ከግሪክ እና ከላቲን ነው። እኔ ግን የማውቀውን የክሪኩን ትርጉም እናገራለሁ።
ኤፒ-ደሚክ፡ = ባጭሩ ይዘታዊውን ትርጉም ስንናገር “አገር አቀፍ ወረርሺኝ” ልንለው እንችላለን
በአንድ አካባቢ፤ በአንድ አገር በሚኖር ሕብረተ-ሰብ ውስጥ የተከሰተና በፍጥነት የሚዛመት ተላላፊ ወይም ወረርሽኝ “ኤፒ ደሚክ” ይባላል።

የቃላቱን ትንታኔ በተመለከተ “ኤፒ” ማለት በ፤ በላይ፤ በውስጥ ወዘተ ማለት ሲሆን “ደሚክ” ማለት ደግሞ “ዲሞስ” ወይም “ዲሞቲክ” ከሚለው የግሪክ ቃል “ሕዝብ” ወይም “የሕዝብ” ማለት ነው። ስለዚህ “ኤፒ ደሚክ” ማለት በአንድ አካባቢ በሚኖር ብዙ ሕዝብ ላይ በፍጥነት የሚሰራች ወይም የሚዛመት ተሐዋሲ ወይም ወረርሽኝ ማለት ነው። “ተሐዋሲ” የምንለው ቫይረሱን ሲሆን “ወረርሽኝ” ስንል ደግሞ ስርጭቱን ነው።

ፓን ደሚክ፡ ደግሞ = ባጭሩ ይዘታዊውን ትርጉም ስንናገር “ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ” ልንለው እንችላለን
የቃላቱ ትንታኔ “ፓን” ማለት በግሪከኛ “ሁሉ”፡ማለት ነው። ለምሳሌ “ፓንዶክራቶስ” “ፓንዶ ዲናሞስ” ማለት ሁሉን የሚገዛ፤ ሁሉን ቻይ ወዘተ ማለት ነው። ስለዚህ “ፓን ደሚክ” ማለት ወይም ይሚባለው በአንድ አገር እና በአንድ አሕጉር ከሚኖር ሕዝብ አልፎ በአብዛኛው የዓለም ክፍል በሚኖር ሕዝብ ላይ በፍጥነት የሚዛመት ተላላፊ ብሽታ ነው።

አንድ ተላላፊ ሕመም ከአንድ አገር አልፎ ወደ ሌላው አገር ሲዛመት ማለትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲዳረስ ቢያንስ በአብዛኛው ዓለም ሲደርስ ስሙ ከ “ኤፒደሚክ” ወደ  “ፓን ደሚክ” ይቀየራል። ወይም ፓን ደሚክ ተብሎ ይጠራል። በቀላል አማርኛ “ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ” ማለት ነው። ይህንን ስያሜ የሚሰጠው የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ወይም ማዕከል ነው።

ታስታውሱ እንደሆነ ኮሮና ባይረስ ገና በቻይና ሲነሣ በሌሎችም የተወሰኑ አገራት ሲዛመት ስሙ ገና አልተቀየረም ነበር። “ኤፒ ደሚክ” የሚለውን ስም እንደያዘ ነበር። በኋላ ግን በአብዛኛው የዓለም ክፍል ሲሰራጭ “ፓን-ደሚክ” የሚለውን ስያሜ አገኘ።
እስከ አሁን ከዚህ በላይ የተነጋገርነው አንድ ተላላፊ በሽታ አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ስያሜ እንዴት እንደሚሰጠውና የስያሜው ትርጉም ምን እንደሆነ ነው።

ኮሮና ቫይረስ ምንድን ነው?
ኮሮና ባይረስ ባጭሩ ቅርጹን መሠረት አድርጎ የተሰየመ ሲሆን እንደ አክልል ክብ ስለሆነ ከቅርጹ በመነሳት “ክብ ወይም ዘውድ መሰል ቅርጽ ያለው ተሐዋሲ” ብለውታል ማለት ነው።
እንዴት ይተላለፋል?
በንክኪ እና በተለያየ መንገድ ቫይረሱ ወደ አካላችን ውስጥ ሲገባ ማለትም ከአካላችን ክፍት በሆኑ የአካል ክፍሎች አልፎ ወደ ውስጥ ሲገባ ማለት ነው፤ ለምሳሌ ክፍት የሆኑ የአካላችን ክፍሎች ከሚባሉት ዋና ዋና ዎቹ እና በቀላሉ ሊጋለጡ የሚችሉት “አፍ” አፍንጫ፤ እና “ዓይን” ናቸው። ሌሎችም እንዳሉን አትርሱ።

እንዴንት መከላከል ይቻላል?
ይህንን ቫይረስ ከምንከላከልባቸው መንገዶች ዋና ዋናዎቹ
1.  እጅን ለ20 ሰከንድ በሳሙና በደንብ መታጥብና ከታጠብን በኋላም በንጹህ ሶፍት ወይም ናብኪን ማድረቅ፤ ወይም ውሃ ካላገኘን በአልኮሆል ወይም የእጅ ማጽጃ (ሃንድ ሳኒታይዘር”) በደንብ መጥረግ።

ለምን እንታጠባለን? የእጅ መታጠብ ውጤት
ብዙ ጊዜ የተለያዩ ነገሮችን ስለ ምንነካ ሰዎችን ስለምንጨብጭ ባይረሱ በእጃችን ላይ ይኖራል ወይም ይገኛል ተብሎ ይታመናል፤ ስለዚህ እጃችንን ለ20 ሰከንዶች በሳሙና እና በውሃ በምንታጠብ ጊዜ ወይም በአልኮል በምናጸዳው ጊዜ በእጃችን ላይ የነበረው ባይረስ ወይም ተሐዋሲ ይሞታል፤ ከሞተ ደግሞ ምንም የሚፈጥረው ሕመም አይኖርም።

2.  ከሰዎች ጋር አለመነካካት፡ 
ከሚስሉ እና ከሚያስነጥሱ ሰዎች በ6 ፊት ወይም ስድስት ጫማ ርቀት መሆን፤ ማለትም አለመቅረብ። ሰላምታችን ያለመነካካትና ያለ መቀራረብ በቃል ብቻ መሆን አለበት።

ለምን በርቀት መሆን አስፈለገ? 
ከሚስሉ እና ከሚያስነጥሱ ሰዎች በርቀት መሆን ያስፈለገበት ምክንያት ወይም የሚሰጠው ጥቅም፦ በምንስልና በምናነጥስ ጊዜ አፋችን እና አፍንጫችን ይከፈታል፤
በዚህ ጊዜ ፈሳሾች ከአፋችን እና ከአፍንጫችን ወጥተው በቅርበት ወዳሉ ሰዎች አካል ሊፈናጠሩና ወደ ሌላው ሰው አፍንጫና አፍ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፤ የሳለው ወይም ያስነጠሰው ሰው ኮሮና ቫይረስ ያለበት ከሆነ ቫይረሱ በምራቆቹ ወይም በፈሳሾቹ ውስጥ አብሮ አለ። ይህ ከሆነ ደግሞ ቫይረሱ ወደ አካላችን ከምራቆቹ ጋር ገባ ማለት ነው እንታመማለን።

3.  አፍን፤ አፍንጫን እና ዓይንን ባልታጠበ እጅ ከመነካካት መቆጠብ፡

ለምን? ባልታጠበ እጅ ፊትን በተለይ ክፍት የሆኑ አካላቶቻችንን ለምሳሌ አፋችንን፤ አፍንጫችንን፤ እና ዓይናችንን ባልታጠበ እጅ ከመነካካት መቆጠብ በቀላሉ በባይረሱ ከመጠቃት እንድናለን ። ከላይ እንዳየነው እጆቻችን ብዙ ነገሮችን ይነካካሉ ስለዚህ ቫይረሱ ያለበትን ነገር ለምሳሌ መዝጊያ፤ ጠረጴዛ፤ ወንበር ልብስ፤ የመኪና በር፤ ወዘተ ልንነካ እንችላለን፤ በዚህ ጊዜ ቫይረሱ ከነካነው ነገር ወይም አካል ወደ እጆቻችን ይሸጋገራል ማለት ነው።

 ከዚያ በኋላ ሳንታጠብ አፋችንን፤ አፍንጫችንን፤ እና ዓይናችንን ከነካን ቫይረሱን ወደ አካላችን ውስጥ አስገባነው ማለት ነው። ስለዚህ ባልታጠበ እጅ ፊታችንን መደባበስና መንካት የለብንም።


የኮሮና ቫይረስ በሚከተሉት ነገሮች ከፊት ለፊታቸው የተጻፉን የጊዜ ርዝመቶ ሳይሞት በሕይወት መቆየት ይችላል። ስለዚህ የተጠቀሱትን እና ሌሎችንም ነገሮች ከነካን፤ ወይም በተጠቀሱት አካባቢዎች በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካለፍን ጥንቃቄ ማድረክ አለብን። ካልሆነ ግን ልንጠቃ እንችላለን ማለት ነው።

·         በአየር ላይ፡ = ለ3 (ሦስት) ሰዓታት (አንድ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አፉን ሳይዝ ካስነጠሰ በአካባቢው ላይ ለ3 ሰዓታት ስለሚቆይ በዚያ ካለፍን ልንጠቃ እንችላለን (ስካርብ ወይ ሻፕ መልበስ አፍን እና አፍንጫን መሸፈን መልካም ነው)
·        በመዳብ እና መዳብ ነክ ነገሮች፡ = ለ4 (አራት) ሰዓታት
·        በካርቶን እና ካርቶን ነክ ነገሮች፡ = ለ24 (ለሃያ ዐራት) ሰዓታት
·        በብረትና ብረት ነክ ነገሮች፡ = ከ2-3 (ከሁለት እስከ ሦስት) ቀናት
·        በፕላስቲክ እና ፕላስቲክ ነክ ነገሮች፡= ከ2-3 (ከሁለት እስከ ሦስት) ቀናት ሳይሞት መቆየት ይችላል።

ይህ የሚያሳየን የምንነካው ሁሉ ስጋት ያለው ስለሆነ፡   እጃችንን ሳንታጠብ ምግብ አንደማንበላ ሁሉ በተጠቀሰው ዓይነት መንገድ እጆቻችንን ሳንታጠብ ፊታችችንን መንካት የለብንም።

ልዑል አምላክ በቸርነቱ  ይጠብቀን
ከአውደ ጥናት

Sunday, March 22, 2020

በሥጋዊውና በመንፈሳዊውም ሕይወታችን ልንመራባቸው የሚገቡ የሥነ ምግባር ጥቅሶች/Ethical and Moral vers...



በአውደ ጥናት ዘአማርኛ እየተዘጋጁ የሚቀርቡ


በሥጋዊውና በመንፈሳዊውም ሕይወታችን ልንመራባቸው የሚገቡ የሥነ ምግባር ጥቅሶች
በተለይ ለወጣቶችና ለሕጻናት መልካም ሥነ ምግባርን የሚያስተምሩ ጥቅሶች ስለ ሆኑ 

ወላጆች ለልጆቻችሁ እያብራራችሁ ማስተማር አለባችሁ በማለት አሳስባለሁ

“ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ” የሚለውና እና “ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” ሌሎችንም መጻሕፍቶቼን ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ
  https://amzn.to/2WE6B8f https://amzn.to/2xk8mwB

Friday, February 14, 2020

የቃል ትምህርት: ጸሎተ ሃይማኖት በልሣነ ግእዝ/የሃይማኖት ጸሎት


ጸሎተ ሃይማኖት

ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ።

ወነአምን በአሐዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ አብ ዋሕድ ዘህልው ምስሌሁ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም ብርሃን ዘእምብርሃን አምላክ ዘእምአምላክ ዘበአማን ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ።

ዘቦቱ ኵሉ ኮነ ወዘእንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ ወኢምንትኒ ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ። ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኀኒትነ ወረደ እምሰማያት። ተሰብአ ወተሠገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል ።

ኮነ ብእሴ ወተሰቅለ በእንቲአነ በመዋዕለ ጲላጦስ ጴንጤናዊ ። ሐመ ወሞተ ወተቀብረ ወተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት በከመ ጽሑፍ ውስተ ቅዱሳት መጻሕፍት። ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ።

ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ ዘሠረጸ እምአብ ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት። ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት።

ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለስርየተ ኀጢአት። ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም።

መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ                                                                                                                                          

ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ

የተሰኘው ይህ መጽሐፍ ሦስት ምዕራፎችንና አሥር አበይት  ክፍሎችን የያዘ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ በአማርኛ ቋንቋ  ከተጻፉ መጻሕፍት ሁሉ ባቀራረቡና በይዘቱ ፍፁም 
የመጀመሪያው ነው ። ስለመጽሐፍ ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላለው ሁሉ በዚህ መጽሐፍ ተካቶ ይገኛል ። በቂ ግንዛቤ ከሌላቸው  ጀማሪዎች እስከ መጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ድረስ ከዚህ  መጽሐፍ የማይለካ ዘርፈ ብዙ እውቀትን ያገኛሉ ፤ ይማሩበታል ያስተምሩበታልም ። 




ስለዚህ ስለእምነትዎ በሚገባ በማወቅም ሆነ በማሳወቅ ራሰዎን ፤ ቤተሰበዎንና ሕብረተሰቡን ሕያው በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ቃል ማነጽ ከፈለጉ ፤ ስለ እያንዳንዱ እምነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ፤ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የሚቀበሉት መጽሐፍ ቅዱስ እርሰዎ ከያዙት ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚለያይ መሆኑን ማወቅየሚሹ ከሆነ ፤ ስለመጽሐፍ ቅዱስ የማስተማርና የመስበክ ሃላፊነት ካለብዎ ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪ ፤ ዲያቆን ፤ ቄስ ፤መነኩሴ ፤ ጳጳስ ፤ ኤጲስ ቆጶስ ወዘተ ከሆኑ፤ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂዱ ከሆነ ፤ በአጠቃላይ ፍፁም የሆነውን ሃይማኖታዊውንና ማኅበራዊውን ሕገ-መንግሥት ሊመሩበት ከወደዱ ፤ከዘፍጥረት እስከ ራእየ-ዮሐንስ  እንዲሁም  2ኛ የቀኖና መጻሕፍትን ጨምሮ በ81ዱ ፤ በ76ቱ ፤ በ73ቱ ፤በ66ቱና በ24ቱ  የዕብራውያን ብሉይ ኪዳን የሚገኙ መጻሕፍት ሁሉ በቀላልና ልዩ በሆነ ዘመዊ አቀራረብ የመጽሐፉ ጸሐፊ ፤ የተጻፈበት ዘመንና ቦታ ፤ የመጽሐፉ ፍሬ-ሐሣብ ባጭሩ ፤ የመጽሐፉ ጠቅላላ ይዘት ባጭር ትንታኔ ምርጥ ጥቅሶች ፤ ልዩና ያልተለመዱ ፤ እንዲሁም የመጽሐፉ መልዕክት በሚሉ መሠረታውያን አርእስት የያንዳንዱመጽሐፍ ይዘት ማራኪ በሆነ መንገድ የመጽሐፉን ጠቅላላ ሐሣብ ባጭሩ ተምሮ በሰፊው  መረዳት በሚያስችል ዘዴ ቀርቧል ።

በእኔ እይታ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ከልጅ እስካዋቂ  ይህንን መጽሐፍ ሊይዝ ይገባልእላለሁ ። በመሆኑም እርሰዎም ከመጽሐፍ ቅዱሰዎ ጋር ተዋውቀው ያስተዋውቁት እላለሁ ።

"ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን 

"Lisane Ge'ez Yegara Quanquachin" is a study book for Ge'ez Language. This book is part one and teaches Ge'ez language for Amharic speakers however, includes also some basic English grammars and vocabularies to help the people who are interested to learn some basic Ge'ez words.


 ይህ "ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የተሰኘው መጽሐፍ በአቀራረቡ ለየት ያለ ቀላልና በጣም ዘመናዊ የሆነ አቋራጭ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴን የተከተለ ነው።

ከዚህ መጽሐፍ የግእዝን ቋንቋ በአማርኛ የሚማሩ ሲሆን መጠነና የሆነ የእንግሊዘኛ ቃላትንና አገባቦችንም ያስተምራል። ይህ መጽሐፍ በመሠረታዊነት የተዘጋጀው ቋንቋውን ምንም ለማያውቁ ጀማሪዎችና መጠነኛ ግንዛቤ ኖሯቸው ሰዋስዋዊ አካሄዱን ግን ለማያውቁ ሲሆን ከዚያም በላይ የእውቀት ደረጃ ላሉም ቢሆን በተለይ የአገባብ መዋቅሮችን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤን እንዲሰጥ ታስቦ ነው።

መጽሐፉን ካህናት፤ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፤ በየአብያተ ክርስቲያናት ሕጻናትንና ወጣቶችን በመሰብሰብ የእምነትንና የሥነ ምግባርን ትምህርት የሚያስተምሩ መምህራን ለማስተማሪያነትም ሆነ የግል እውቀትን ለማዳበር እንዲሁም በማነኛውም የቋንቋ ጥናት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የቋንቋን አካሄድ፤ የቃላትን ቅንብርና አገባብ ለመገንዘብ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ለወጣንያንና ለማዕከላውያን የተዘጋጀ 1ኛ መጽሐፍ እንደ መሆኑ መጠንም በውስጡ የሚገኘው እያንዳንዱ ርእስ የተሰጠው ትርጉም፤ አገልግሎትና ትንታኔ ያለቀለት ሳይሆን ለክፍል አንድ የተመጠነ ብቻ ነው።

 ማለትም በክፍል ሁለትና በቀጣዮቹም ክፍሎች ትምህርቱ እየሰፋና እያደገ ወይም እየጨመረ የሚሄድ ነው። ስለዚህ አንድ ቃል ወይም አገባብ እናንተ የምታውቁትን ሁሉ አካቶ ባለመገኘቱ የተረሣ ወይም ሳይታወቅ የታለፈ እንዳይመስላችሁ፤ ለክፍል አንድ ተመጥኖ የቀረበ ስለሆነ ብቻ ነው። ለወደፊቱ በእኔ የሚዘጋጁ የግእዝ መማሪያ መጻሕፍት ከዚህ መጽሐፍ የሚቀጥሉ እንጅ ይህንን ክፍል የማያካትቱ ስለሚሆኑ የቋንቋው ሙሉ ፍላጎት ያለው ሁሉ ከዚህ ከመሠረታዊው ትምህርት መጀመር አማራጭ የሌለው በመሆኑ ይህን መጽሐፍ ማግኘት ይኖርበታል ብየ አምናለሁ። እንደዚህ ከሆነ ማለትም መሠረቱን በሚገባ መገንዘብ ከቻላችሁ ጽኑ እና በአለት ላይ የተመሠረተ መሠረት ስለሚኖራችሁ ቀጣዩ ትምህርት በጣም ቀላል እና ግልጽ እንደ ሚሆንላችሁ አልጠራጠርም።

Monday, February 10, 2020

“ነአኵተከ እግዚኦ ወንሴብሐከ..” የሚባለው የዘወትር ጸሎት በግእዝ ቋንቋ


ነአኵተከ ፡

ነአኵተከ ፡ እግዚኦ ፡ ወንሴብሐከ ፡ ንባርከከ ፡ እግዚኦ ፡ ወንትአመነከ ። ንገኒ ፡ ለከ ፡ እግዚኦ ፡ ወንትቀነይ ፡ ለስምከ ፡ ቅዱስ ። ንሰግድ ፡ ለከ ፡ ኦ ፡ ዘለከ ፡ ይሰግድ ፡ ኵሉ ፡ ብርክ ፡ ወለከ ፡ ይትቀነይ ፡ ኵሉ ፡ ልሳን ። አንተ ፡ ውእቱ ፡ አምላከ ፡ አማልክት ፡ ወእግዚአ ፡ አጋዕዝት ፡ ወንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ለኵሉ ዘሥጋ ፡ ወለኵላ ፡ ዘነፍስ ፡ ወንጼውዐከ ፡ (ንሕነ ፡) በከመ ፡ መሐረነ ፡ቅዱስ ፡ ወልድከ ፡ እንዘ ፡ ይብል ፡ አንትሙሰ ፡ ሶበ ፡ ትጼልዩ ፡ ከመዝ ፡ በሉ  ::        
                                             

Sunday, February 2, 2020

አስተርዕዮታ ለማርያም ድንግል

አስተርዕዮታ ለማርያም ድንግል


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አምላካችን እግዚአብሔር በሰላም እና በጤና ጠብቆ ከዕድሜያችን ተጨማሪ የሆነችውን ይህችን ልዩ ዕለት ያለ ምንም ዋጋ በነፃ በመስጠት የእናቱን እና የእናታችንን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የዕረፍቷን መታሰቢያ በአል እንድናከብር ስለፈቀደ የተመሰገነ ነው። አሁንም በተለመደው ቸርነቱ የንስሐ ዕድሜን ጨምሮልን ለሚቀጥለው ዓመት በሕይወት አቆይቶን ይህንን በአል ለማሰብ እና ለማክበር ያብቃን አሜን።


በመግቢያችን እንዳየነው አስተርዕዮታ ለማርያም እያልን በየዓመቱ ጥር 21 ቀን የምናስበው በአል የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የዕረፍት ወይም ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ የተለየችበትን በአል ነው።

አዎ! በሥነ ፍጥረት ታሪክ አቻ ወይም አምሳያ ያልተገኘላት፥ ከምድራውያን ሰዎችም ሆነ ከሰማያውያን መላእክት የሚመስላት የሌለ፣ በፍጡር ሕሊና ሊመረመር በማይችል ምሥጢር ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ሕያው አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ፀንሣ የወለደች፣ ያሳደገችም ልዩ ፍጥረት እንደ ማነኛውም ፍጡር በሞተ ሥጋ ተለየች ማለት ለሰዎች አእምሮ ይከብዳል። ለዚህም ነው ታላቁ የዜማ ደራሲ ቅዱስ ያሬድ በሁኔታው እየተደነቀ “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም ያአጽብ ለኵሉ”

= ለሚሞት ሞት ይገባል፤ ነገር ግን የማርያም ሞት ሁሉን ያስደንቃል(ያስገርማል)  በማለት ለማነኛውም ሰብአዊ ታሪክ ላለው፣ ሞት ያለ፤ የነበረና የሚኖር ስለሆነ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን የተለየና በተፈጥሮ ታሪክ ሊፈጸም የማይችል ታሪክ ለተሰጣት ለእመቤታችን የሆነው ሞት አስደናቂ የሆነበት።

ምክንያቱም፡ ለእመቤታችን የተሰጠው ለማንም ፍጡር አልተሰጠም፤ የእሷን ዓይነት ምርጫ የተመረጠ የለም፤ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ታሪክ ያላት፤ ዓለም ከተፈጠረም በኋላ ከመወለዷ በፊት ምርጫዋ የተሰበከላት፤ ስለ እርሷ ያልተነበየ ነቢይ የሌለ፤ ለሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመናት የሕሊና ተስፋ የሆነች፤ አሁንም በአማላጅነቷ ዓለም የሚማፀናት ልዩ ፍጥረት፤
ዓለምን ለማዳን ኃያሉን አምላክ በድንግልና ጸንሣ በድንግልና እንደምትወልድ አዲስ እና ለዓለም እንግዳ የሆነ፣ በሥነ ተፈጥሮ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ፣ የተፈጥሮን ሕግ የጣሰ ታሪክ በነቢያትና በመላእክት የተነገረላት፤
የትንቢቱ ፍጻሜ በተቃረበ ጊዜ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የሚያበሥር መልአክ ወደሷ የተላከላት፤ ዓለም የሚጠባበቀው የድኅነት ሥራ በእርሷ እናትነት እንደሚፈጸም በግልጽ ያበሠራት።

ታዲያ ሁሉን ማድረግ የሚቻለው፣ የሚሆነውን እንዳይሆን፣ የማይሆነውን እንዲሆን ወይም የሚቻለውን የማይቻል፤ የማይቻለውን የሚቻል የሚያደርገውን፤ ለሚያደርገው ሁሉ ለምን በማለት ማንም የማይጠይቀውን ሁሉን ቻይ አምላክ ለወለደች እናት እንዴት ሞት ተገባት? ሲል ነበር ቅዱስ ያሬድ “ያስደንቃል፤ያስገርማል” በማለት የገለጸው። እውነትም ያስገርማል!

በሰብአዊ ባሕል ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ከኀዘን ቀጥሎ የሚደረግለት ነገር ቢኖር ከልደት እስከ ሕልፈት ያሳለፈውን ምድራዊ ታሪክ መተረክ ነው። ታዲያ የእመቤታችን የዕረፍት ታሪክ ከልደቷ ወይስ ከወላጆቿ  ከቅዱስ ኢያቄምና ከቅድስት ሐና ልደት! ከየት ነው መጀመር ያለብን?
ምክንያቱም፣ የእመቤታችን ታሪክ ከታሪክ በፊት ነው። ዓለም ከመፈጠሩ፣ ጊዜ ከመቆጠሩ በፊት፤ ዓለም የራሱን ታሪክ ከመጀመሩ በፊት እመቤታችን አስደናቂ ታሪክ ነበራት፤ ታዲያ ከየት ይጀመር? ያዐፅብ ለኵሉ” እውነትም ያስደንቃል።

ታሪኳ ልዩ፣ ምርጫዋ አስደናቂ፣ ከፍጡራን ሕሊና በላይ ቢሆንም “እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ” ብለን በማለፍ የእኛ ሕሊና በሚችለው መጠን በሚገባን እና በገባን ደረጃ መጻሕፍት የሚነግሩንን ታሪክ መናገራችን ግድ ነው። ለዚህም ነው ቅዱሳን አባቶች ለእመቤታችን ሰብእና ምሳሌ ስላጡለት “በመኑ ወበአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ” = በማን እና በምንስ እንመስልሻለን” በማለት የሚናገሩ።

ስለዚህ የእመቤታችንን ታሪክ ግልጽና ቀላል ለማድረግ በ 3 ዐበይት ክፍሎች ከፋፍየ ባጭሩ ለማስረዳት እሞክራለሁ ። ምክንያቱም ረጅሙን የእመቤታችንን ታሪክ ተርኮ መጨረስ የሚችል ማንም የለም፣ ቅዱሳንም አልጨረሱትም። በመሆኑም እኔም አልሞክረውም።

የመጀመሪያውን የታሪክ ክፍል

“እግዝእትነ ማርያም ነበረት እምቅድመ ዓለም በሕሊና አምላክ” የሚለው ዐረፍተ ነገር ይገልጸዋል ይህ ጽሁፍ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፎ ይገኛል። ቃሉ ወደ አማርኛ ሲተረጎም እመቤታችን ከዓለም በፊት በአምላክ ሕሊና ወይም ሐሳብ ውስጥ ነበረች ማለት ነው።

ዓለም ማለት ቃሉ ግእዝ ሲሆን በቀጥተኛ አማርኛ ፍጥረት ማለት ነው፤ ስለዚህ ከሥነ ፍጥረት በፊት ማለትም አዳም ተፈጥሮ በድሎ በኃጢአት ከመውደቁ በፊት እመቤታችን በአምላክ ሐሣብ ለድኅነተ  ዓለም ለሥጋዌው ተመርጣ ነበር ማለት ነው።
ይህ ምሥጢር በሰዎች አእምሮ በእኛ አቅም የሚመዘን ከሆነ መቸም ቢሆን ሊገባን አይችልም፤ በመሆኑም የሚመዘነው ሁሉን ማድረግ በሚችለው ለሚያደርገው ሁሉ ለምን? ብሎ ጠያቂ በሌለው ልዑል አምላክ አቅም ብቻ ነው። “እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ” የሚሳነው ነገር የለም።

እነ ነቢዩ አርምያስ፣ ኢሳይያስ መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎችም ቅዱሳን ገና ሳይወለዱ በእናታቸው ማሕፀን እግዚአብሔር መርጧቸዋል። አንዱን ብቻ ለመጥቀስ ያህል ነቢዩ ኢሳይያስ በ49ኛው ምዕራፍ አምላኩ አስቀድሞ እንዴት እንደመረጠው  “እም ከርሠ እምየ ሰመየኒ ስምየ፣ ወረሰዮ ለአፉየ ከመ መላፂ በልህ፣ ወከደነኒ ታሕተ ጽላሎተ እዴሁ” = በእናቴ ማኅፀን ስሜን ኢሳይያስ ብሎ ሰየመኝ፣ አንደበቴን እንደ ተሳለ ምላጭ አደረገው(አንደበተ ርቱዕ አደረገኝ) በእጁ ጥላ ሥርም ጠበቀኝ ። በማለት ይገልጸዋል።
ታዲያ ከነቢያት የምትበልጥ ከመላእክትም የምትልቅ ቅድስተ ቅዱሳን የአምላክ እናት በፈጠራትና ለታላቅ የሥጋዌው ምሥጢር ባቀዳት በአምላኳ ከዓለም በፊት መመረጧ ምን ያስደንቃል። ምንም የሚያስደንቅ የሚያስገርም ነገር የለም ምክንያቱም በአምላክ እቅድ የተለየ ክብር የተሰጣት የተለየች ፍጡር ናት፤ የተለየ ነገር በእርሷ ብቻ መታየቱ የአምላክ ልዩ ጥበብ ነው።

ሁለተኛው የታሪክ ክፍል

“በሐሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእትቤዘወከ በመስቀልየ ወበሞትየ” የሚለው ቃል ኪዳን ወይም ዐረፍተ ነገር ይገልጸዋል።  ሁለተኛው የታሪክ ክፍል ዓለም ከተፈጠረ በኋላ  በቅዱሳን ነቢያት አንደበት በሰፊው የተተረከ የታሪክ ክፍል ነው። አዳም በደለ በደሉም የሞት ዋጋን የሚያስከፍል ነበረ፤ የዚህ ዕዳ ተካፋይም አዳም በደሎ ሞት ሳይፈረድበት በፊት በአምላክ ሕሊና ከነበረቺው ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በስተቀር ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ነበር።

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከወላጆቻችን ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ በወላጆቹ በደል የሞተው ዓለም በአምላክ ሕሊና ለድኅነተ ዓለም አምላክ ለሥጋዌው የመረጣትን የቅድስተ ቅዱሳንን መወለድ በተስፋ ይጠባበቅ ነበር።

“አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት” = በሠራው ኃጢአት ምክንያት ከገነት በተባረረ ጊዜ እንደ ገና ወደ ክብሩ ለመመለስ ተስፋ የሚያደርገው አንቺን ነበር። ምክንያቱም ዓለምን የሚያድነው ሁሉን ማድረግ የሚችለው ኃያሉ አምላክ ቢሆንም ይህንን የድኅነት ሥራ ከእርሷ በመወለድ በፍጹም ተዋሕዶ እንደሆነ አስቀድሞ ስለ ነገረው ነበር።

በመቀጠልም ብዙ ነቢያት በልዩ ልዩ ምሳሌ ስለ እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ተነበዩ በ4800 ዓ/ዓ አካባቢ ነቢዩ ኢሳይያስ በግልጽ “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወትሰምዮ ስሞ አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ” = እንሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፤ አማኑኤል ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። በማለት በማያሻማ መልኩ ተናገረ። ታዲያ ይህ የነቢዩ ትንቢት እመቤታችን ከመወለድዋ ማለትም ከ5486 ዓመተ ዓለም 700 ዓመታትን ቀድሞ የተነገረ ትንቢት ስለሆነ እመቤታችን ከዓለም በፊት በአምላክ ሕሊና የተሟላ ታሪክ ነበራት የሚለውን እውነት ያረጋግጥልናል። ምክንያቱም ነቢዩ ሲተነብይም እመቤታችን አልነበረችም ወላጆቿም አልተወለዱም።

ይህ የነቢዩ የኢሳይያስ ቃል “ድንግል” አለ እንጂ ድንግል ማርያም ስለማይል በምን እናውቃለን ለምትሉና በትክክል ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም መነገሩን ማረጋገጥ ለምትፈልጉ ወንጌላዊው ማቴዎስ በምዕራፍ 1፡ ቍጥር 20 ጀምሮ
“ወዝ ኵሉ ዘኮነ ከመ ይትፈጸም ዘተብህለ እምኀበ እግዚአብሔር በነቢይ እንዘ ይብል። “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤል” ዘበትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ።

= ከእርሷ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። ልጅም ትወልዳለች እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። በነቢይ ከጌታ ዘንድ እንሆ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል፣ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው። በማለት ትንቢተ ኢሳይያስ ም 7 ቍ 14ን ጠቅሶ ይነግረናል።

 ይህ ቃል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የተናገረው ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ የጻፈው የማያጠራጥር ምስክርነት ነው።

ሦስተኛው የታሪክ ክፍል

“ወበሳድስ ወርኅ ተፈነወ ገብርኤል መልአክ እምኀበ እግዚአብሔር ኀበ አሐቲ ሀገር ዘገሊላ እንተ ስማ ናዝሬት። ኀበ ድንግል እንተ ተፍኅረት ለብእሲ ዘስሙ ዮሴፍ ዘእም ቤተ ዳዊት ወስማ ለይእቲ ድንግል ማርያም። ወቦአ መልአክ ኀቤሃ ወይቤላ ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ  እግዚአብሔር ምስሌኪ ወቡርክት አንቲ እምአንስት። ወርእያ ደንገፀት እምቃሉ።”

= በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፣ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። መልአኩም ወደ እርሷ ገብቶ ደስ ይበልሽ ጸጋ የመላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።

ይህ ቃል እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በአምላክ ሕሊና የመኖሯን አላማ፣ ዓለም ከተፈጠረ በኋላ ሲጠበቅ የነበረውን የሥጋዌ እና የድኅነተ ዓለም ተስፋ የነቢያትን ትንቢት ሁሉ እውን የሚያደርግ፤ በእመቤታችን ቅድመ ታሪክ ሁሉ ሲጠራጠሩ ለነበሩት ተግባራዊ እውነት ነበር።

የእመቤታችን ምርጫ ልዩና የተፈጥሮ ሕግን የጣሰ፣ በሥነ ፍጥረት ታሪክ ውስጥ ታስቦም ተፈጽሞም የማያውቅ በመሆኑ ለራሷ ለእመቤታችን ጭምር ፈጥኖ የሚታመን አልነበረም፤ በመሆኑም እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር ዘንድ በቀጥታ ተልኮ ከመጣው ከመላእክት አለቃ ከመልአኩ ከቅዱስ ገብርኤል ጋር ተከራክራ ነበር፤ እንዴት እንደዚህ ይሆናል በማለት ጠይቃ ነበር።

“ወርእያ ደንገፀት እምቃሉ ወኀለየት ወትቤ እፎኑ እንጋ ዘከመዝ አምኃ ይትአምኁ”
“እፎኑ ይከውነኒ ዝንቱ እንዘ ኢየአምር ብእሴ”

= እርሷም ባየቺው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች።

“ወአውሥአ መልአክ ወይቤላ መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ ወኀይለ ልዑል ይጼልለኪ ወዘኒ ይትወለድ እምኔኪ ቅዱስ ውእቱ ወይሰመይ ወልደ እግዚአብሔር ልዑል…”

“እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር” እመቤታችንን ያሳመናት ቃል ይህ ነበረ። ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም። አዎ የለም “በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሐለየ ይፌጽም”

እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ የተለየ ጸጋ የተለየ ምርጫ ስላላት ከፍጡራን ሁሉ የተለየ ክብር ተሰጥቷታል፤ ቅድስተ ቅዱሳን ማለትም ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ የተቀደሰች ማለት ነው፤ ከቅዱሳን መላእክትም ሆነ ከቅዱሳን ሰዎች እንደ እመቤታችን ያለ ፍጡር አልተገኘም ። ቅዱስ ኤፍሬም በድርሰቱ “የአቢ ክብራ ለማርያም እምኵሎሙ ቅዱሳን፤ ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል፤ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሐዱ ዘእም ቅድስት ሥላሴ” በማለት ስለ እመቤታችን ልዩ ፍጡርነት እና ክብር ይናገራል።

ኪሩቤል እና ሱራፌል የሚባሉት የአምላክን መንበር ተሸክመው ቅዱስ ቅዱስ እያአሉ የሚኖሩ ናቸው አምላክን በዐይናቸው እንኳን ማየት አይችሉም ፤ እመቤታችን ግን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማሕጸኗ ተሸከመቺው። ለዚህም ነው ከሁሉም የምትልቀው። አባ ሕርያቆስም “ነጸረ አብ እምነ ሰማይ ወኢረከበ ዘከማኪ” በማለት እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ዓለሙን ሁሉ ተመለከተ አየ እንዳንቺ ያለ አላገኘም የቅድስናሽን ደም ግባትም ወደደ አንድ ልጅንም ወደ አንቺ ላከ። ይላል።

በመግቢያየ እንደ ተናገርኩት ስለ እመቤታችን የተነገረውን ተርኮ የሚጨርስ ባለመኖሩ። እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የተነገረው የተተነበየው ሁሉ እውን ከሆነ በኋላ፤ ከእግዚአብሔር በቀጥታ የተላከው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የተናገረውን አስደናቂ መልእክት፤ ቅድስት ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱስ ተመልታ የሰጠቺውን ምስክርነት፤ ከሰማች በኋላ፤ ለመረጣት ለአምላኳና ለልጃ ያቀረበቺውን ምስጋና በመናገርና ከወላጆቿ ከተወለደችባት ቀጽበት ጀምራ እስከ ጥር 21 ቀን 50 ዓ/ም ድረስ የነበራትን ሥጋዊ ዕድሜ ጠቅሼ ትረካየን እገታለሁ።

ወትቤ ማርያም/ ማርያምም እንዲህ አለች።

“ታዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ወትትሐሠይ መንፈስየ በአምላኪየ ወመድኀኒየ፤ እስመ ርእየ ሕማማ ለአመቱ ናሁ እም ይእዜሰ ያስተበፅዑኒ ኵሉ ትውልድ። እስመ ገብረ ሊተ ኀይለ ዐቢያተ ወቅዱስ ስሙ ። ወሣህሉኒ ለትውልደ ትውልድ ለእለ ይፈርህዎ። ወገብረ ኀይለ በመዝራዕቱ ወዘረወሙ ለእለ ያዐብዩ ኀሊና ልቦሙ። ወነሠቶሙ ለኀያላን እመናብርቲሆሙ አዕበዮሙ ለትሑታን። ወአጽገቦሙ እምበረከቱ ለርኁባን ወፈነዎሙ  ዕራቆሙ ለብዑላን። ወተወክፎ ለእስራኤል ቍልዔሁ ወተዘከረ ሣህሎ። ዘይቤሎሙ ለአበዊነ ለአብርሃም ወለዘርዑ እስከ ለዓለም።” ሉቃስ 1፡47

ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥
መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና።
እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤
ስሙም ቅዱስ ነው።
ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።
በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤
ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ 
ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤
ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤
የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤
ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥
ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።

እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም
·        ነሐሴ 7 ቀን በ5486 ዓ/ዓ ከአባቷ ከቅዱስ ኢያቄምና ከእናቷ ከቅድስት ሐና ተፀነሰች
·        ግንቦት 1 ቀን 5486 ዓ/ዓ ተወለደች
·        ለ 3 ዓመታት በአባት በእናቷ ቤት ከቆየች በኋላ የሥዕለት ልጅ በመሆኗ በ3 ዓመቷ
ታሕሣስ 3 ቀን በ5489 ዓ/ዓ በሥዕለት ልጅነት ለቤተ መቅደስ ተሰጠች
·        ለ12 ዓመታት በቤተ መቅደስ ኖረች
·        3 ዓመት ከ 9 ወር ከ 5 ቀን በጠባቂዋ በቅዱስ ዮሴፍ ቤት፤ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር የግብፅ ስደትን ጨምሮ ኖረች
·        30 ዓመት ከ 2 ወር ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ኖረች
·        15 ዓመታት ከጌታ ስቅለት በኋላ በወንጌላዊው በዮሐንስ ቤት ኖራ ጥር 21 ቀን በ50 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለየች።

ልመናዋ ክብሯም በእውነት ይደርብን
ይሁን ይደረግ አሜን

ከአውደ ጥናት ዘግእዝ


Wednesday, January 8, 2020

ለግእዝ ቋንቋ ተማሪዎች መልካም ዜና/Good news for Ge'ez learners


6in1(፮በ፩)
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው፦

 በመጀመሪያ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ ልዑል አምላክ ለመጪው ዓመትም በሰላም ያድርሰን። በመቀጠልም የሚከተለውን መልካም ዜና አስታውቃችኋለሁ በትኩረት ተመልክታችሁ ተግብሩት



Download the best free open source video creator software Streamlabs OBS
https://streamlabs.com/editor?promo=melakubesetegn-e38b-10  

አውደ ጥናት ዘግእዝ “የግእዝ ቋንቋ ለሁሉም” በሚለው መርሕ መሠረት የትምህርቱ ፍላጎት ኑሯችሁ የመክፈል አቅም ላነሳችሁ ሁሉ ከተወሰኑ ፍላጎት ካላቸው እኅቶችና ወንድሞች ጋር በመሆን የትም ቦታ ልታገኙት በማትችሉት ልዩና ቀላል እንዲሁም  አቋራጭ በሆነ መንገድ የግእዝን ቋንቋ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ትማሩ ዘንድ በሚከተሉት መመሪያዎች መሠረት በመደራጀት ተመዝግባችሁ መማር እንድትችሉ መልካም ዜናን እንደሚከተለው አበሥራችኋለሁ ይህ ፕሮግራም እናንተንም እኔንም ሕብረተሰቡንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ስለሆነ የዚህ መልካም ሥራ ተካፋይ ብቻ ሳትሆኑ አስተባባሪም ልትሆኑ ይገባል እላለሁ፤ ምክንያቱም ብዙዎች ይህንን ትምህርት ለመማር ጥልቅ ፍላጎት አላቸውና ነው።



ክፍያና መመሪያ (በሚከተለው መልኩ መመሪያውን በተግባር በማዋል ፈጥናችሁ መጀመር ትችላላችሁ።)
በመጀመሪያ እርስ በርሳችሁ ለመተዋወቅ ይረዳችሁ ዘንድ ትክክለኛ ስማችሁን እና የምትኖሩበትን አገር ከተቻለ ፎቷችሁንም ጭምር በዋትስአፕ ፕሮፋይላችሁ ላይ አድርጉ(ወይም ጻፉ)

1.  ክፍያ፦ ለያንዳንዱ ሰው (6ቱ ግሩፖች) ለአፍሪካ(ኢትዮጵያን ጨምሮ) $32 (ሠላሳ ሁለት) ዶላር እያንዳኑ ሰው ማለት ነው። ለሌሎቹ አገራት ሁሉ፦ $50(ሃምሣ ዶላር) (6ቱም እያንዳንዳቸው)

2.  6(ስድስት) ሰዎች በአንድ ላይ ለመክፈል ተስማሙ
(ከተቻለ በአንድ አካባቢ የምትኖሩና የምትተዋወቁ ብትሆኑ መልካም ነው፣ ካልሆነ ግን ከዚህ በፊት ባትተዋወቁም፣ በአንድ አገር ባትኖሩም በዚህ ግሩፕ ላይ ከተስማማችሁ ይቻላል)

3.  በያላችሁበት ሁናችሁ $50(ሃምሣ ዶላር) ወደ ባንክ ታስገባላችሁ
 ወይም በሌላ መንገድ ከፍላችሁ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ትልካላችሁ፣ ሁላችሁም ማለትም 6ቱ ሁሉ ክፍያቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ ግሩፑ አስገባችኋለሁ።

·        በአንድ ላይ የምትከፍሉ ሰዎች ስድስታችሁ ማለት ነው በደምብ መነጋገር አለባችሁ ምክንያቱም ሁሉም በያሉበት ከፍለው ካላጠናቀቁ የከፈሉት ሰዎች ያልከፈሉትን መጠበቅ ስላለባቸው ነው(ከተቻለ አንድ ሰው ሃላፊነቱን ወስዶ በደንብ ማስተባበር አለበት)

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ