Saturday, May 11, 2019

ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን /Review on Lisane Geez Yegara Quanquachin part 1



ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የተሰኘው የግእዝ ቋንቋ መማርያ መጽሐፍ ጠቅላላ ማብራርያና ለአንባቢዎች የሚጠቅሙ መሠረታውያን የአጠናን ስልቶችን ጨምሮ ስለመጽሐፉ ጠቃሚነት ግምገማ ክፍል አንድ::

“ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” የተሰኘውን የግእዝ ቋንቋ መማርያ መጽሐፍ ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ

“ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ” ይህ መጽሐፍ በአማርኛ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከተጻፉ መጻሕፍት ብቸኛውና የመጀመሪያው ነው፤ 81ዱን እና በዓለም ዙሪያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሁሉ የሚቀበሏቸውን፤ የማይቀበሏቸውን ሁሉ በአንድ ላይ አካቶ እስከ ምክንያቱ ቀላልና ልዩ አጭርም በሆነ መንገድ የሚያስተምር ልዩ መጽሐፍ ነው። ይህንን የመጀመሪያና ብቸኛ መጽሐፍ ለመግዛት ይህንን ይጫኑ። https://amzn.to/2LEyp8A 

Another important self help book in English
Atomic Habit
The instant New York Times bestseller
No matter your goals, Atomic Habits offers a proven framework for improving--every day. James Clear, 
to buy click this link https://amzn.to/2vUCkmZ 

Friday, May 10, 2019

ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበ አምሳሊነ/”Let us make man in our image, after our likeness”


“ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ”
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው ዛሬ ወቅታዊ ታሪክን መሠረት ያደረገ የግእዝ ቋንቋ ትምህርትን አዘጋጅቸላችኋለሁ ።
 በመሠረታዊነት በአውደ ጥናት ዘግእዝ ተመዝግበው ለሚማሩ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች እንደ ልምምድ ይሆን ዘንድ የሚዘጋጅ ነው።

ሆኖም ግን ቋንቋውን መማር ለምንፈልግ ሁሉ በጣም ጠቃሚ ግንዛቤን የሚሰጥ ትምህርት ነው።
በዚህ ዝግጅት የምናየው ስለ አምላክ ሰው መሆን እና ስለ ዓለም ድኅነት  ሲነገር ወይም ሲተረክ በሊቃውንቱ አንደበት ተዘውትረው በግእዝ ቋንቋ ስለሚነገሩ  ጠለቅ ያለ ምሥጢርን ስለያዙ ልዩ ልዩ ጥቅሶች ነው።

·         ታሪኩ በሕገልቡና
·         በሕገ ኦሪት እና
·         በሕገ ወንጌል በሦስቱ ሕግጋት የተከፈለ ነው።

በመሆኑም ከዚህ በላይ ባሉት 3 ሕግጋት ወይም የታሪክ ምዕራፎች ውስጥ የሚከተሉትን ባጭሩ የምናይበት ዝግጅት ነው።
·          እግዚአብሔር ሰውን እንዴት እንደ ወደደውና ፍቅሩም ምክንያት አልባ እንደሆነ፤
·         ሰው እንዴት እንደ ተፈጠረና የአምላኩን ሕግ እንዴት እንደተላለፈ፤
·         ሰው ከክብሩ ከተዋረደ በኋላ ከእግዚአብሔር ስለተሰጠው ተስፋ
·         ስለ አምላክ ሰው መሆን የነቢያት ትንቢት
·         ሰለ አምላክ ሰው መሆንና የትንቢቱ ፍጻሜ እንዴት እንደነበር
ጠቅለል ባለ አገላለጽ ከሰው ልጅ በአምላክ መወደድ ጀምሮ እስከ ዘመነ ትንሣኤ ድረስ ያለውን ታሪክ ለመናገር ከሚጠቀሱ ብዙ ጥቅሶች መካከል ጥቂቶቹን እና ተዘውትረው በግእዝ ቋንቋ የሚጠቀሱትን ጥቅሶች በግእዝ እየጠቀስን ወደ አማርኛ እየተረጎምን ይዘታቸውን የሥራ ድርሻቸውን እያብራራን እንማራለን። እንከታተል።

ለዛሬው የምናየው የመጀመሪያውን አንድ ጥቅስ ብቻ ይሆናል ይህም በመጀመሪያው የሰውልጅ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ስለ ሰው አፈጣጠር የሚናገር የመጀመሪያ ጥቅስ ነው

ቀዳማይ ምዕራፈ ታሪክ
 “ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ” ዘፍ.1፡26
በዚህ ጥቅስ
1.    እግዚአብሔር በአንድነትና በሦስትነት የሚመለክ አምላክ መሆኑን፤
2.    የሰው ልጅ ከሥነ ፍጥረት ሁሉ የበለጠ ክብርን እንዳገኘ
3.    እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሳይፈጥረው አስቀድሞ እንደወደደው የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው

1.    ንግበር
2.    ሰብእ
3.    በ
4.    አርአያ
5.    ነ
6.    ወ
7.    አምሳል
8.    ነ
·         ፍቅር እንበለ ምክንያት ወፈጢር በአምሳሊሁ
 ልዑል አምላክ ለብዎቶ የሐበነ
እም አውደ ጥናት ዘግእዝ


ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን እና “ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ” የሚባሉትን መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ
https://amzn.to/2VWunwn 
 https://amzn.to/2Yix4Wt
Another important book to build life changing habit, The instant New York Times bestseller
https://amzn.to/2LxyL0K
No matter your goals, Atomic Habits offers a proven framework for improving--every day. James Clear, 

Sunday, May 5, 2019

“አባታችን ሆይ” እና “እመቤታችን ማርያም ሆይ”

ዛሬ በዚህ ዝግጅቴ “አባታችን ሆይ” የሚለውን እና “እመቤታችን ማርያም ሆይ” የሚባሉትን ሁለት የጸሎት ክፍሎች በውጭ አገር ተወልዳችሁም ሆነ ወይም በሌላ ምክንያት አማርኛና ግእዝ ለማታነቡና ለማትናገሩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን አማርኛውንና ግእዙን በምታውቁት የእንግሊዘኛ ፊደል አዘጋጅቼ አቅርቤላችኋለሁ ተከታተሉ፤ 
















ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው፡
ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን መጽሐፍ እና ሌሎቹንም መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ

 https://amzn.to/2V2fMLl         ( ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን መጽሐፍ)
https://amzn.to/2DPUStg    (ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ)
ዛሬ በዚህ ዝግጅቴ “አባታችን ሆይ” የሚለውን እና “እመቤታችን ማርያም ሆይ” የሚባሉትን ሁለት የጸሎት ክፍሎች በውጭ አገር ተወልዳችሁም ሆነ ወይም በሌላ ምክንያት አማርኛና ግእዝ ለማታነቡና ለማትናገሩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን አማርኛውንና ግእዙን በምታውቁት የእንግሊዘኛ ፊደል አዘጋጅቼ አቅርቤላችኋለሁ ተከታተሉ፤ ምን ያህል የሚጠቅማችሁ መሆኑን፤ ወይም የበለጠ የተሻለ መንገድ አለ የምትሉትም የአቀራረብ ዘዴ ካለ ተናገሩ፤ አስተያየታችሁን ለመስጠት ወደኋላ አትበሉ።
እንደምታዩት የተዘጋጀው አማርኛውና ግእዙን በእንግሊዘኛ ፊደል በመጻፍ ስለሆነ አማርኛውንም ሆነ ግእዙን የማንበብ ችሎታ ይኖራችኋል፤ የእንግሊዘኛ ትርጉሙንም አብሬ አስቀምጨዋለሁ፤ የአነባበብ ስልቱን ደግሞ በድምጽ ትሰማላችሁ ማለት ነው።

በነዚህ ሁለት ጸሎታት በግእዝም ሆነ በአማርኛ መጻሕፍት ተጽፎ ከሚገኘው ኃይለ ቃል ሌላ በቃል ስንጸልይ የምንጨምራቸው ተጨማሪ ቃላት አሉ፤ እኔ የጻፍኩት በመጻሕፍቶቻችን የተጻፈውን ነው። በቃል የሚጨመሩት እነዚህ ቃላት ችግር የማያመጡና ከይዘቱ አንጻር ተገቢ ቢሆኑም፤ ሁሉም ምእመናን በአንድ ዐይነት መንገድ ስለማያነቡት ልዩነት የተፈጠረ ስሕተት መስሎ እንዳይታያችሁ፤ ከወዲሁ አሳስባለሁ ።
ከሚጨመሩትም ቃላት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል
1.  “እመቤቴ ማርያም ሆይ” ይህ ከመጽሐፉ በግእዝም በአማርኛም የሚገኘው ኃይለቃል ነው። በቃል በአማርኛ ስንል “እመቤታችን ቅድስት፤ ድንግል፤ ማርያም ሆይ” እንላለን፤ እመቤታችን ቅድስ ናት ድንግልም ናት፤ ትክክለኛ አባባል ነው፤ በዚህ የጸሎት ክፍል ከመጽሐፉ ውስጥ ስለማይገኝ፤ ለምን ቀረ ወይም ለምን ተጨመረ ብለን ግራ እንዳንጋባ ነው።
2.  “ወቡሩክ ፍሬ ከርስኪ” ወይም “የማሕጸንሽ ፍሬ” የተባረከ ነው። ይህ ከመጽሐፉ የሚገኘው ሲሆን፤ በቃል “የማሕጸንሽ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባረከ ነው” እንላለን። በዚህ ላይ ምምህራን የሚያስተምሩት፤ አንድ ነጥብ አለ እመቤታችን በድንግልና ጸንሣ በድንግልና የወለደቺው የእግዚአብሔር ቃሉና ልጁ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው። ስለዚህ የማሕጸንሽ ፍሬ ከተባለ ሌላ የማሕጸኗ ፍሬ ስለሌለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብሎ መጥቀስ አይጠበቅብንም ምክንያቱ በስም የሚጠቀሰው ከብዙዎች መካከል ለመለየት እንጅ አሻሚ የለለውን ነገር መጥቀስ አያስፈልግም ይላሉ። ያም ሆነ ይህ የእኔ አላማ ግን ልዩነቱን እንድታውቁ ብቻ ነው።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን

ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው

Thursday, May 2, 2019

አቡነ ዘበሰማያት እና በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ በግእዝ ቋንቋ /Prayers in Ge'ez Language



ግእዝ/ in Ge’ez Language
አቡነ ዘበሰማያት፣
Abune Zebesemayat

ይትቀደስ ስምከ
Yitkedes Smike

ትምጻእ መንግሥትከ
Timtsa-e Mengistike

ወይኩን ፈቃድከ
Weyikun Fekadike

በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር
Be Keme Be Semay Kemahu Bemidr

ሲሳየነ፣ ዘለለ ዕለትነ፣ ሀበነ ዮም
Sisayene Zelele Eletine Habene Yom

ኅድግ ለነ አበሳነ፡ ወጌጋየነ፡
Hidig Lene Abesane Wegegayene

ከመ ንሕነኒ፣ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ፤
Keme Nhineni Nhidig Leze Abese Lene

ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት፤
Etabi- Ane Egzio wiste Mensut

አላ አድኅነነ፡ ወባልሐነ ፡
Ala Adhinene Webalihane

እምኵሉ እኩይ፤
Emkulu  Ekuy

እስመ ዚአከ፡
Esme Ziake

ይእቲ፡ መንግሥት፡
Yi- Eti Mengist

ኀይል ወስብሐት
Hail Wesbihat

ለዓለመ ዓለም። ኣሜን
Le Alem Alem Amen

============================================================


በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ
Beselame Kidus Gebriel Mel-Ak

ኦ፡ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፣
O Egzi-Etiye Mariam Selam Leki

ድንግል በኅሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ
Dingil Behilinaki Wedingil Besigaki

እመ እግዚአብሔር ጸባኦት ሰላም ለኪ
Eme Egiziabiher Tseba-Ot Selam Leki

ቡርክት አንቲ እምአንስት ፡ ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ
Burikt Anti Em- Anist Weburikt Frie Kersiki

ተፈሥሒ ፡ ፍሥሕት፡ ኦ፡ ምልእተ ጸጋ
Tefesihi Fsiht O Mliete Tsega

እግዚአብሔር ምስሌኪ
Egzia Biher Misleki

ሰአሊ ፡ ወጸልዪ ለነ 
Se-Ali wetseliy Lene

ኀበ ፍቁር ወልድኪ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ፡
Habe Fikur Weldiki Eyesus Kirstos

ከመ ይስረይ ለነ ፡ ኀጣውኢነ (ተማሕጸነ ብኪ)
Keme Yisrey Lene HaTawi- Ene


Sunday, March 31, 2019

አባታችን ሆይ እና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አማርኛ ለማያነቡ


አባታችን ሆይ እና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አማርኛ ለማያነቡ/ The Lord's Prayer and the Prayer to Saint Mary the Mother of God for People who not read or for English speakers


አማርኛ፦ አባታችን ሆይ/in Amharic language
አባታችን ሆይ፤
Abatachin Hoy
Our Father

በሰማያት የምትኖር፣
Besemay Yemitnor
which art in heaven,

ስምህ ይቀደስ፣
Simeh Yikedes
Hallowed be thy Name

መንግሥትህ ትምጣ
Simeh Yikedes
Thy Kingdom come

ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች
Fekadeh Besemay Indehonech
As it is in heaven.

እንዲሁም በምድር ትሁን
Fekadeh Besemay Indehonech
Thy will be done in earth

የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ
Ye elet Injerachinin Siten Zarie
Give us this day our daily bread

በደላችንንም ይቅር በለን፤
Bedelachininim Yikir Belen;
And forgive us our trespasses

እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል
Egnam Yebedelunin Yikir Endeminil
As we forgive them that trespass against us

አቤቱ ወደ ፈተናም አታግባን
Abetu Wede Fetena Atagban
And lead us not into temptation

ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ
Kekifu Hulu Adinen Enji
But deliver us from evil.
መንግሥት ያንተ ናትና
Mengist Yante Natina
For thine is the kingdom,

ኃይል፣ ክብር፣ ምስጋናም
Hail, Kibre, Misganna, Lezelalemu
The power, and the glory

ለዘላለሙ
Lezelalemu.
For ever and ever. 
አሜን
Amen

=======================================

የእመቤታችን ጸሎት PRAYER OF ST. MARIAM in Amharic Languge

እመቤቴ ማርያም ሆይ፣
Eme-bietachin Qidist Dingil Mariam Hoy,
O Holy Virgin Mariam

በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ
Be-Mel-aku  Be-qidus  Gabriel Selamta Selam  Elish Alehu
In the peace of the Angel Gabriel, Peace be unto You,

በሃሳብሽ ድንግል ነሽ፣ በሥጋሽም ድንግል ነሽ
Be-hasabishi   dingil   nesh, Be-sigashim   dingil  nesh, 

የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ፤ ላንቺ ሰላምታ ይገባል
Ye-Ashenafi   Ye-Egziabhier  Enat Hoy, Selamta  Le-anchi   yigebal,
O, Mother of Perfect God (Omnipotent) Peace be unto thee (you),Peace be unto thee (you),

ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽና
Ke-sietoch  hulu   teleyitesh,  anchi yetebarekshi  nesh,
Blessed are thou (you) among women

የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው
Ye-mahtsenish  friem yetebareke new,
and Blessed is the fruit of thy (your) womb.

ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ
Tsegan ye-temelash Hoy, Des  yibelish,
Rejoice, O thou who are full of grace,

እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና
Egziabhier  ke-anchi gar newuna
the Lord is with thee. 

ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን
Ke tewededew Lijish kegetachin,  Ke-medhanitachin, Ke-Eeyesus Kristos Zend, Yikirtan lemignilin,
Ask and pray for us to thy (your) Beloved Son, Eeyesus Kiristos,

ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ አሜን
Hatiatachin, yasteseriyilin zend,  lezel alemu Amen
That he may have mercy upon our souls and forgive us our sins  Amen.