Sunday, February 24, 2019

10 ነገሮች ስለ ግእዝ ቋንቋ/Ten things about Ge’ez language

ስለ ግእዝ ቋንቋ ማወቅ ካለብን ብዙ ምሥጢራት ዐሥሮቹን እንሆ ያዳምጡ/Here are 10 things out of many about Geez language

          መጽሐፍ ለመግዛት ይህንን ይጫኑ

                                                          
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው። ዛሬ ስለ ግእዝ ቋንቋ ማወቅ ካለብን ልዩ ልዩ አስደናቂ ነገሩች ውስጥ ስለ አሥሩ  እንነጋገራለን
            

በመጀመሪያ ከስያሜው ስንነሣ ግእዝ ከሚጠራባቸው ወይም በግእዝ ስም ከሚጠሩት ነገሮች  የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፤
·         ግእዝ የሚለው ቃል “አግአዘ” ወይም “ተግእዘ” ነፃ ወጣ ወይም ነጻ አወጣ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ነፃነት ማለት ነው፤ እንዲሁም አንደኛ፤ መጀመሪያ ማለትም ነው፤
·         የፊደሎቻችን የመጀመሪያ የመጀመሪያ ሆሄ ሁሉ “ግእዝ” እየተባሉ ይጠራሉ
·         የቋንቋችንም ስም ግእዝ ይባላል “ልሣነ ግእዝ” ማለት የግእዝ ቋንቋ ማለት ነው
·         ይዘቱንና የሚሰጠውን ጥቅም መሠረት በማድረግ “መጽሔተ አእምሮ” ተብሎ ተሰይሟል፡
·         ከንባብ ክፍሎች የመጀመሪያ የአነባበብ ስልት ግእዝ ይባላል
·          ከሦስቱ የቅዱስ ያሬድ የዜማ ስልቶች አንዱ ግእዝ ይባላል (ስልቶቹ ግእዝ ፤ ዕዝል፤ አራራይ)
·         ከ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ በፊት ጀምሮ ለሥነ ጽሁፍ እንደዋለ የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ
1ኛ. የመጀመሪያው የሥነ ፍጥረት ቋንቋ እንደ ነበር በአገር ውስጥና በውጭ አገር የቋንቋና የሃይማኖት ምሁራን ይታመናል። እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረበት ቋንቋ ነው ለማለት ለማስረጃነት ከሚጠቀሱት መካከልም የሚከተሉት ይገኙበታል
·        የመጀመሪያው ሰውአዳምአደመ አማረ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ስም ሲሆን ያማረ የተዋበ ፍጡር ማለት ነው፤ ይህ ግእዛዊ ስም በዓለም ዙሪያ ሳይቀየር መጠሪያ ሆኖ ቀርቷል፤ ስለዚህ ስም ሊሰየም የሚችለው በወቅቱ በነበረው ወይም በሚያውቁት ቋንቋ ስለሆነ ግእዝ የመጀመሪያው ቋንቋ መሆኑን ይጠቁማል፤
·         መጽሐፈ ሄኖክ የተጻፈው በግእዝ ቋንቋ ሲሆን ሄኖክ የነበረበት ዚዜም በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ በፊት ነበር፤ ይህም በኤቦር እብራይስጥ ተብሎ ከተሰየመው ቋንቋ ከዕብራይስጥ በፊት ግእዝ ቀድሞ የነበረ መሆኑ ነው።
·        የታሪክ ተመራማሪዎችም የመጀመሪያው የሰብአዊ ፍጡር ቋንቋ በምሥራቅ አፍሪካ ሲነገር የነበረ ወይም የምሥራቅ አፍሪካ ቋንቋ ነው በማለት ጽፈዋል። የአፍሪካ ቀንድ በማለት የምትጠራው የምሥራቅ አፍሪካ አገርም ኢትዮጵያ መሆኗ ነው።
2ኛ. የግእዝ ቋንቋ ከቋንቋዎች ሁሉ ለየት ያለ ይዘቱን እና የጥበብ ቋንቋነቱን የሚገልጽ ልዩ ስም አለው። እሱም “መጽሔተ አእምሮ” ይባላል፤ የእውቀት መስታዋት/ጥበብን የሚያሳይ ማለት ሲሆን በዚሁ ስም የሚጠራ የግእዝ መዝበበ ቃላት መጽሐፍ አለ፤ የዚህ መጽሐፍም ሙሉ ርእስ “
መጽሐፈ ሰዋስው
ብሔራዊ ቋንቋ ዘኢትዮጵያ
መጽሔተ አእምሮ” ይባላል
3ኛ. ከአብዛኛዎቹ ቋንቋዎች ተለይቶ ለያንዳንዱ ፆታ የራሱ የሆነ የስም ተለዋጭ አለው
·        በሌሎች አብዛኛዎቹ ቋንቋዎች ግን እየተዳበሉ ይጠራሉ እንጅ እንደ ግእዝ የየግላቸው ስያሜ የላቸውም ለምሳሌ
·          የአማርኛ የስም ተለዋጮች 8 ሲሆኑ (እናንተ የሚለው ተውላጠ ስም ሴቶቹንም ወንዶችንም የሚወክል ነው)
·        የእንግሊዘኛ ደግሞ 6 ሲሆኑ በግእዝ አንተ፤አንቲ፤ አንትሙ፤አንትን የሚባሉትን አራት ተውላጠ ስሞቾች በአንድ ተውላጠ ስም “ዩ” በማለት ያዳብላቸዋል
4ኛ. በግእዝ ቋንቋ አንቱታ የለም፤ ፆታን ደብቆ ምሥጢር መነጋገር፤ አይቻልም
·        ምክንያቱም ለያንዳንዱ ፆታ የራሱ የሆነ ተውላጠ ስምና ግሥም ስላለው ነው
·         በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከሴት ጋር ይሁን፤ ከወንድ ጋር፤ ከብዙ ሰዎች ጋር ይሁን፤ ወይም  ከአንድ ሰው ጋር እንደምናወራ በቀላሉ ማወቅ አይቻልም፤ ምክንያቱም በእንግሊዘኛ የሁለተኛ መደቦች ግሥ ለአንድም ለብዙም፤ ለሴትም ለውንድም የሚጠቀሙት አንድ ግሥና አንድ ተውላጠ ስምን ብቻ ነው። (ግሣቸውም ሆነ የስም ተለዋጫቸው አንድ ዓይነት ነው)
5ኛ.በዓለም ላይ ጠፍተው የነበሩ መጽሐፈ ሄኖክና መጽሐፈ ኵፋሌ የተባሉት ሁለቱ ቅዱሳት መጻሕፍት ቁምራን/ወይም ኩምራን በተባሉ ዋሻዎች ውስጥ በከርሰ ምድር ተመራማሪዎች በ1956 (በ1948 ኢትካ) ዓ/ም የተገኙት በግእዝ ቋንቋ የተጻፉ ነበሩ፤ ዓለምም ስለ ሁለቱ መጻሕፍት ማወቅ የቻለው ከግእዙ ጽሁፍ በመተርጎም ነው
6ኛ. አንድ የግእዝ ቋንቋ ዘር ግስ ቢያንስ ከ80 በላይ በሆነ የአረባብ ስልት ይረባል፤ ለምሌ ያህል አእመረ የሚለውን ግስ እንደሚከተለው እንመልከት።
·          አእመረ  አእመሮ - አእመረከ - አእመሮሙ - አእመረክሙ- አእመራ - አእመረኪ - አእመሮን - አእመረክን- አእመረኒ - አእመረነ
·        አእመርከ
·        አእመሩ
·        አእመርክሙ
·        አእመረት
·        አእመርኪ
·        አእመራ
·        አእመርክን
·        አእመርኩ
·         አእመርነ እነዚህ ዐሥሩ እርስ በርሳቸው ሲተዋወቁ ከነዚህም በተጨማሪ በውስጡ የሚወጡት ንዑሳን አናቅጽ፤ ቅጽሎች፤ ስሞች ከአንድ ግስ ይወጣሉ ወይም ይወለዳሉ።
7ኛ. የግእዝ ፊደላት አናባቢዎች እንደ ሌሎች ቋንቋዎች በአናባቢና በተናባቢ የተከፋፈሉ አይደሉም
በዚህም ምክንያት አንድን ቃል በግእዝ ቋንቋ ለመጻፍ ብዙ ፊደላት አያስፈልጉም፤ ለማንበብ ግራ አያጋባም፤ ለመጻፍ የምንወስደውን ጊዜ ይቆጥብልናል፤ የወረቀን እና የቀለምን ወጭም ይቀንሳል፡
8ኛ. በግእዝ ቋንቋ ግሥ ብቻውን ሙሉ የዐረፍተ ነገር ትርጉምን ይሰጣል፤ ማለትም ለሩቅ ለቅርብ፤ ለወንድ፤ ለሴት ለአንድ ለብዙ መሆኑን በግሡ ብቻ እናውቀዋለን፡
ምሳሌ፦ አጥረየ  ይህ ግሥ ለ3ኛ መደብ 1 ወንድ የሚናገር መሆኑን ግእዝን የተማረ ሰው ሁሉ ያውቀዋል ምክንያቱም ከያንዳንዱ ግሥ መጨረሻ ላይ ያሉት ፊደላት ሁሉንም ይተርካሉ። በመሆኑም አጥረየማለት እና አለማየሁ አጥረየ ወይም ውእቱ አጥረየ ማለት አንድ ነው።
 አናባቢዎች የተናባቢ ሆሄያት አካላት ናቸው፤ ለምሳሌ አውደ ጥናት ለማለት በግእዝ 6 ፊደላት ብቻ ሲሆኑ Awude Tinat በእንግሊዘኛ 10 ወይም 9 ፊደላት ናቸው፤ ምክንያቱም አናባቢዎቻቸው የተለዩ አካላት ስለሆኑ ነው፤ Awude Tinat ሲጻፍ 5ቱ ተናባብ ሲሆኑ አምስቱ አናባቢዎች ናቸው።

9ኛ. ዓለም ስለግእዝ ቋንቋ ምሥጢራዊነትና የጥበብ ቋንቋነት በሚገባ የተረዳ በመሆኑ በተለያየ ሕገወጥ መንገድ የግእዝ ቋንቋ መጻሕፍትን በመዝረፍ ላይ ይገኛል፤
 በአሁኑ ጊዜ በትክክል የታዎቁ 5515 በግእዝ ቋንቋ የተጻፉ የብራና መጻሕፍት በውጭ አገራት ቤተ መጻሕፍት ውስጥ እንደሚገኙ የታሪክ ምሁራን ዘግበዋል(ጽፈዋል) እነዚህ በትክክል የተረጋገጠ ማስረጃ ያላቸው ሲሆኑ ሌሎች ብዙ የብራና መጻሕፍት በውጭው ዓለማት እንደሚገኙ የታመነ ነው።
ከፍተኛ ቍጥር ያላቸው የብራና መጻሕፍት ከሚገኙባቸው አገራትም የሚከተሉት 4 ተቀዳሚ ተጠቃሽ ናቸው።
·        በብሪታንያ 2804
·        በፈረንሳይ 854
·        በጀርመን 511
·        በአሜሪካ 401
·        በእሥራኤል 386
·        በጣልያን 108  መጻሕፍት ይገኛሉ። በዚህም እሥራኤላውያንና የግእዝ መጻሕፍት የማይገኙበት ዓለም የለም ይባላል።
10. በአሁኑ ጊዜ የግእዝ ቋንቋ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ መልኩ የሰዎችን ትኩረት ስቧል፤ ተፈላጊነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት እያደገ መጥቷል፤
ለዚህም ማረጋገጫ
·         በአገር ውስጥና በውጭውም ዓለማት የሚገኙ የሥነ ጽሁፍ ሰዎች ስለ ግእዝ እየጻፉ ይገኛሉ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለማት በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደ አንድ ትምህርት በመሰጠት ላይ ይገኛል
·        በአገራችን ውስጥ በግእዝ ቋንቋ ዓለማዊ ዘፈኖች ጭምር ተሠርተው ቀርበዋል
·         መቀሌ ውስጥ ኤፍ ኤም 104 የሚባል የራድዮ ጣቢያ በግእዝ ቋንቋ ልዩ ልዩ ስርጭቶችን በማስተላለፍ ላይ ይገኛል
·        በልዩ ልዩ የሕዝብ መገናኛዎች በማኅበር በመሰባሰብ የግእዝን ቋንቋ በመማር ላይ ይገኛሉ

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ
ዐሥር ነገሮች ስለ ግእዝ ቋንቋ

Wednesday, February 13, 2019

ንሴብሖ: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያሬዳዊ መዝሙር በቤዛና ቤቴል ይስሐቅ/ EOT Church S...


እምአፈ ደቂቅ ወሕጻናት አስተዳሎከ ስብሐተ
ንሴብሖ ለእግዚአብሔር፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያሬዳዊ መዝሙር በቤዛና ቤቴል
ይስሐቅ/ Ethiopian Orthodox Tewahido Church Song by Beza & Bethel Yishak
መዝሙሩን ለመግዛት ይህንን ስልክ ይጠቀሙ፡ 703 606 1976
https://amzn.to/2BGxAVn

Sunday, February 10, 2019

በአውደ ጥናት ዘግእዝ ስለሚሰጠው የግእዝ ቋንቋ ተከታታይ ትምህርት ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ሙሉ መልስ


                                           


                                                                                  https://amzn.to/2IhIfvs
“ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” የተሰኘውን የግእዝ ቋንቋ መማርያ መጽሐፌን ለመግዛት ይህንን ይጫኑ
https://amzn.to/2WUPz3x