Thursday, March 12, 2015

ክፍል 23 በግእዝ አጭር ታሪክ

ግእዝ ክፍል 23 (አጭር የሕይወት ታሪክ በግእዝ ቋንቋ)

የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ክፍል  23 (ታሪክ በግእዝ ቋንቋ)
ሰላም ለክሙ አኃውየ ወአኃትየ አርድእተ ልሳነ ግእዝ ኩልክሙ።

ዮምሰ ፈቀድኩ ከመ እምሀርክሙ ልሳነ ግእዝ በልሳነ ግእዝ ባህቲቱ። ወእስእለክሙ ከመ ትስምኡ ወታጽምኡ በእዝነ ልቡናክሙ፤ ወትነጽሩ በዐይነ ልቡናክሙ። ኅበ ዜና አሐቲ ብእሲት ዘእዜንወክሙ ድኅረ ሰለስቱ ቅጽበታት።

 ዮም በእሥራ ወሰለስቱ ክፍለ ትምህርትነ እዜንወክሙ በይነ አሐቲ ብእሲት ዘስማ አውደ ጥናት።

ቅድመ ሰለስቱ ዓመታት እንዘ አሀውር በፍንወት ረከብኩ እቤርተ ዕድሜ ብእሲተ ዘስማ አውደ ጥናት፤ ወስመ ጥምቀታ ወለተ ማርያም። ወይእቲሰ እምነ ነገደ ኢትዮጵያ። ወብእሲት ነበበተኒ ከመ ወለደት ብዙኃነ ደቂቀ እለ ይነብሩ ዝርዋነ በውስተ ኵሉ ዓለም ወሰአለተኒ ከመ እምሀር ላቲ ደቂቃ ልሳነ ግእዝ ወቅኔ ወአነኒ እቤላ ኦሆ።

ተፈጸመ ዜና ሕይወታ ለብእሲት

ናሁ እጤይቀክሙ ሐምስተ ጥያቄያተ እለ ወጽኡ እምነ ዜናሃ ለብእሲት ዘዜነውኩክሙ በዛቲ ዕለት

1.    ተአምርዋኑ ለዛቲ ብእሲት?
2.   ሰማእክሙኑ ዜናሃ ለዛቲ ብእሲት ቅድመ
3.   ሰማእክሙኑ በይነ ብእሲት ዘዜነውኩክሙ?
4.   ንግሩኒ ስማ  ለብእሲት
5.   እም ኀበ አይቴ ነገዳ ለብእሲት?

ናሁ ፈጸምነ ወበካልእት ዕለት እዜንወክሙ በይነ ዜና ዚአየ በልሳነ ግእዝ ወአንትሙሰ ንበሩ ድልዋኒክሙ ከመ ትዜንዉ ዜና ሕይወትክሙ በአውደ ጥናት ለአርድእተ ግእዝ ወበፍቁራነ አውደ ጥናት  ኵሎሙ።

በሰላም ያስተራክበነ

ትርጉም በአማርኛ


የግእዝ ቋንቋ ተማሪዎች ወንድሞቼ እና  እኅቶቼ ሁላችሁ ሰላም ለእናንተ ይሁን

ዛሬ የግእዝን ትምህርት በግእዝ ቋንቋ ብቻ አስተምራችሁ ዘንድ ወደድኩ። በውስጣዊው ጆሯችሁ (በልብ ጆሯችሁ) እና በልባችሁ ዐይንም ከሦስት የዐይን ጥቅሻ (ሰከንዶች ወይም ቅጽበታት) በኋላ ወደ ምነግራችሁ ወደ አንዲት ሴት ታሪክ ትሰሙና ታዳምጡ ትመለከቱም ዘንድ እለምናችኋለሁ።

ዛሬ በክፍል 23 ትምህርታችን አውደ ጥናት ስለ ተባለች ስለ አንዲት ሴት እነግራችኋለሁ።

ከሦስት ዓመታት በፊት በመንገድ እየሄድኩ ሳለ (እያለሁ) በዓለም ስሟ “አውደ ጥናት” በክርስትና ስሟ ደግሞ ወለተ ማርያም የተባለች የድሜ ባለጸጋ(አሮጊት) ሴትን አገኘሁ። እሷም ኢትዮጵያዊት (ከኢትዮጵያውያን ወገን) ነበረች። ይህቺም ሴት በመላው ዓለም ተበታትነው የሚኖሩ ብዙ ልጆችን እንደ ወለደች ነገረቺኝ። የግእዝን ቋንቋና ቅኔን ልጆቿን እንዳስተምርላትም ለመነቺኝ። እኔም እሺ አልኳት።

የሴትዮዋ ታሪክ ተፈጸመ

አሁን በዚች ቀን ታሪኳን ካወራሁላችሁ ከሴትዮዋ ታሪ ውስጥ የወጡ አምስት ጥያቄዎችን እጠይቃችኋለሁ።

1.      ሴትዮዋን (ያችን ሴትዮ) ታውቋት ነበረ? (ታውቋታላችሁን?
2.     ከዚህ በፊት ስለዚች ሴትዮ ታሪክ ሰምታችሁ ነበር?
3.     ሰለነገርኳችሁ ሴትዮ ሰምታችሁ ነበር?
4.     የሴትዮዋን ስም ይናገሩ(ንገሩኝ)
5.     የሴትዮዋ ትውልድ ከየት ነው? (ትውልዷ) ከየት ነው(ዜግነቷ ምንድነው?

አሁን ጨርሰናል በሌላ ቀን ስለራሴ ታሪክ በግእዝ ቋንቋ እነግራችኋለሁ።

 እናንተም በአውደ ጥናት ለግእዝ ተማሪዎችና ለአውደ ጥናት አፍቃሪዎች ሁሉ የህይወት ታሪካችሁን በግእዝ ቋንቋ ትናገሩ ወይም ትተርኩ ዘንድ ተዘጋጅታችሁ ቆዩ።

እግዚአብሔር በሰላም ያገናኘን!