"Learn Geez Language/የግእዝ ቋንቋ ትምህርት Part 15
የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ክፍል
15 ውይይት ወይም ጥያቄና መልስ በወይዘሮ ሶፍያና በአንድ ካህን መካከል። እንግሊዘኛ ለሚፈልግ በእንግሊዘኛም አዘጋጅቸላችኋለሁ
ጽሁፍን መመልከት ትችላላችሁ ማለት ነው። ማስተዋሉን ያድለን።
ተስእሎት ወአውሥዖት/ጥያቀና
መልስ /ውይይት
Questions and
Answers or Dialogues
የግእዝ ትምህርት ክፍል 15 ውይይት
Geez: lessons part 15 Dialogues (በግእዝ፤ በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ)
Sofia፡/ሶፍ
እፎ ሐደርከ አቡየ?
Good Morning Father?
አማርኛ፡
እንደ ምን አደርክ/አደሩ/አባቴ?
ካህን፡Clergy/Pries:
እግዚአብሔር ይሰባህ እፎ ሐደርኪ ሶፍያ?
Thanks to God! Good Morning Sofia!
አማርኛ፡
እግዚአብሔር ይመስገን እንደ ምን አደርሽ ሶፍያ?
ሶፍያ/Sofia፡
እግዚአብሔር ይሰባህ። ባርከኒ አቡየ!
Thanks to God bless me my Father
አማርኛ፡
እግዚአብሔር ይመስገን ባርከኝ አባቴ/ባርኩኝ አባቴ(በግእዝ ቋንቋ አንቱታ
የለም)
ካህን/ Clergy/Pries፡
እግዚአብሔር ይባርኪ ወያብርህ ገጾ ላእሌኪ፡
God (The Lord) bless you and make
his face shine on you
አማርኛ፡
እግዚአብሔር ይባርክሽ ፊቱንም ያብራልሽ/ፊቱንም ወደአንቺ ይመልስ
ሶፍያ/Sofia፡
ፍትሐኒ አቡየ! አስተስሪ ኃጢአትየ
My Father, Please forgive my sin
አማርኛ፡
ይፍቱኝ አባቴ ኃጢአቴን አስተስርይልን/ይቅር በል
ካህን/Clergy/Pries፡
እግዚአብሔር ይፍታህ/ ይፍታህኪ/እግዚአብሔር ያስተስሪ ለኪ ኃጢአተኪ
God (the Lord God) forgive your
sin
አማርኛ፡
እግዚአብሔር ይፍታሽ/ኃጢአትሽን ይቅር ይበል
Sofia፡/ሶፍያ
አሜን፡ /ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ
Amen
አማርኛ፡
ይሁን ይደረግ/እንዳልከው ይህንልኝ
ካህን/ Clergy/Pries፡
እፎ ውእቶሙ(ሀለዉ) ደቂቅኪ ሶፍያ?
How are your children Sofia?
አማርኛ፡
ልጆችሽ እንዴት ናቸው ሶፍያ?
Sofia፡/ሶፍያ
እግዚአብሔር ይሰባህ (ወውእቶሙ) ሰላመ ሐለዉ
Thanks to God they are fine
አማርኛ፡
እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ናቸው/ደህና አሉ
ካህን/Clergy/ Priest;
ሶፍያ, ለምንት ኢመጽኡ (ደቂቅኪ) ኅበ ቤተ ክርስቲያን ምስሌኪ?
Sofia; Why they did not come with you to the church?
አማርኛ፡
ሶፍያ፣ ልጆችሽ ለምን ወደ ቤተ ክርስቲያን ካንቺ ጋር አልመጡም?
Sofia/ሶፍያ፡
አቡየ, አነ ፈተውኩ ከመ አምጽኦሙ ምስሌየ አላ ኢክህሉ ከመ ይትነሥኡ እምነ ንዋሞሙ፡
My Father, I would like them to come with me, but, they could not
walkup!
አማርኛ፡
አባቴ፣ ልጆቼን ከእኔ ጋር ወደ ቤተክርስቲይና እንዲመጡ /አመጣቸው ዘንድ ወድጀ ነበር፤ ነገር
ግን ከእንቅልፋቸው ሊነሱ አልቻሉም።
ካህን/Priest:
ሶፍያ, ኢይደልወኪኑ ትንሥእዮሙ ለደቂቅኪ ኅበ ቤተ እግዚአብሔር?
Sofia, shouldn’t bring your kids
to the temple of God?
አማርኛ፡
ሶፍያ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘሻቸው ትመጪ ዘንድ ይገባሽ አልነበረም?
ሶፍያ/Sofia፡
አአምር አቡየ; አላ ውእቶሙ ኢፈቀዱ ከመ ይምፅኡ (ኢፈቀዱ ይምፅኡ)
ኅበ ቤተ ክርስቲያን ምስሌየ
I know my father but they did not
want to come with me to the church.
አማርኛ፡
አውቃለሁ አባቴ፤ ነገር ግን እነሱ ከእኔ ጋር ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጡ ዘንድ አልወደዱም።
ካህን፡/Priest
ወአነ አአምር!
ሰላመ እግዚአብሔር የሀሉ ምስሌኪ ወሑሪ በሰላም
I know too! The Peace of God May Be with You ! Go(walk) in Peace!
አማርኛ፡
እኔም አውቃለሁ! የ እግዚአብሔር ሰላም ከአንቺ
ጋር ይሁን በሰላም ሂጂ/በሰላም ግቢ።
ሶፍያ/Sofia:
አሜን አቡየ!
ወአንተሰ እቱ ኀበ ቤትከ በሰላም
Amen my father, to you too!
አማርኛ፡
አሜን/ይሁን ይደረግ አባቴ፤ አንተም በሰላም ወደ
ቤትህ ግባ።