Saturday, February 11, 2017
Tuesday, January 31, 2017
ልሣነ ግእዝ መግቢያ 2
ሰላም ለክሙ ፍቁራነ ልሣነ ግእዝ "ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን" መግቢያ ሁለት እንሆኤ! ከ7 ቀናት በኋላ ዋናው ትምህርት ይጀመራል፤ የመጀመሪያ ትምህርት ለምንማረው ርእስ መሠረት ስለሆነ በዝግጅት መቅረብን ወይም መከታተልን አትርሱ፤ ላልሰሙ አሰሙ፤ ሸር አድርጉ ፤ ሐሣባችሁን ግለጡ፤ ከወደዳችሁትም ላክ አድርጉ፤ መልካም ትምህርት! ከአውደ ጥናት
Tuesday, January 24, 2017
Monday, January 16, 2017
ልሣነ ግእዝ በ/ር መላኩ
Selam Everyone, Awde Tinat will start to teach Ge'ez Language based on the new publishe book "Lisane Ge'ez" yegara quanquachi. In order to spread this news, please Share,Share, and Share to every one you know. ሰላም አርድእተ ግእዝ፣ "ልሣነ ግእዝ" የጋራ ቋንቋችን በተሰኘው አዲስ መጽሐፍ መሠረት በአውደ ጥናት አዲስ የግእዝ ትምህርት በዚህ ወር ሊጀመር ስለሆነ ይህንን ዜና ላልሰሙት በማስተላለፍ እንድታሰሙ ተጋብዛችኋል።
Sunday, August 14, 2016
Wednesday, August 3, 2016
ልሣነ ግእዝ መጽሐፉን ለመግዛት
Lisane Geez Yegara Quanquachin/ ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የተሰኘውን ይህንን የግእዝ ቋንቋ መማርያ ክፍል አንድ መጽሐፍ ከአማዞን ለመግዛት ይህንን ይጫኑ.
Lisane Geez Yegara QuanquachinFriday, June 3, 2016
ክፍል 34 ተናባቢ ፊደላት
ተናባቢ ሆሄያት
ተናባቢ ማለት ተያያዥ ማለት ሲሆን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ቃላት በአንድ ላይ ተያይዘው ሲጻፉና ሲነበቡ “ተናባቢ”ወይም ኃረግም ይባላሉ። ባለቤትነትን ከምናመለክትባቸው መንገዶች መካከልም ተናባቢ ቃላት ናቸው።
ቃላት የሚናበቡበት ምክንያት ለሦስት አበይት ሥራዎች ነው
1.
ባለቤትነትን
ወይም ባለንብረትነትን ለመጠቆም ወይም ለማመልከት
2. ምንነትን ማንነትን ወዘተ ለመግለጽ
3. ንግግርን ለማራዘምና ሥርዓተ ዜማን
ወይም ንባብን ለማስተካከል የሚሉት ሲሆኑ ከነዚህም ውጭ ሌሎች ተመሳሳይ
አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።
ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ቃላትን ለማናበብ የምንፈልገውን
ቃል ወይም ንብረቱን መጀመሪያ ላይ፤ ባለንብረቱን ቀጥለን
እናስቀምጣለን ፤ሆሄያትን ለማናበብ የቃሉን የመጨረሻ ሆሄ መሠረት
ያደረገ ሕግን መከተል አለብን። ይህም
·
ሳልስን
ወደ ሐምስ (በሣልስ የሚጨርስ ቃል ሲሆን ማለት ነው)
·
ሳድስን
ወደ ግእዝ መቀየር አለብን (በሳድስ የሚጨርስ ቃል ሲሆን ማለት ነው)
·
ግእዝ(በግእዝ
ሆሄ የሚጨርስ ቃል)
·
ራብዕ(በራብዕ
ሆሄ የሚጨርስ ቃል)
·
ሐምስ
(በሐምስ ሆሄ የሚጨርስ ቃል) እና
·
ሳብዕ
(በሣብዕ ሆሄ የሚጨርስ ቃል) ሳይቀየሩ መናበብ ይችላሉ::
ምሳሌ፦ በግእዝ “መጽሐፍ” ማለት በአማርኛም በቁሙ መጽሐፍ
ነው፤ ይህ የያዝሺው ወይም የያዝከው የምታነቡት ማለቴ ነው መጽሐፍ
የማን መሆኑን ከምንገልጽባቸው መንገዶች አንዱ በማናበብ ነው ብለናል
ስለዚህ “መጽሐፍ” የነበረውን ቃል ከባለ መጽሐፉ ጋር ለማናበብ ማለት መጽሐፉ የማን እንደሆነ ለመናገር ቃሉ
በሳድስ ከጨረሰ ወደ ግእዝ ይቀየራል ብለናል ስለዚህ መጽሐፍ የሚጨርሰው በሳድስ ስለሆነ የመጨረሻዋን ሳድስ ፊደል ወደ ግእዝ በመቀየር “መጽሐፈ መላኩ” ብትሉ ወደ አማርኛ ሲቀየር “የመላኩ መጽሐፍ” ይሆናል። ስለዚህ መጽሐፉ የማን ንብረት ነው?
ለሚለው ጥያቄ መልሱ የመላኩ ይሆናል።
ተናባቢ ቃላትን ስንተረጉም ብዙ ጊዜ “የ” የሚል አመልካች ሆሄ ከሁለቱ ቃላት መካከል ይወጣል። የሚከተሉትን ምሳሌዎች ይመልከቱ
·
|
የክርስትና
ስም ሁሉ ተናባቢ ነው
|
·
ጽጌ ገነት = የገነት (የጓሮ) አበባ
·
ደመና ሰማይ = የሰማይ
ደመና
·
ተወክፎ ነግድ = እንግዳን መቀበል
Subscribe to:
Posts (Atom)
