Sunday, October 25, 2015
Saturday, October 10, 2015
ግእዝ ክፍል 29
ትእዛዝ አንቀጽ
ትእዛዝ አንቀጽ ማለት ማዘዣ ወይም የማዘዣ ግሥ
፤ ትዕዛዝ የሚተላለፍበት ቃል ማለት ነው።
ትእዛዝ በቅጥራ የሚተላለፈው ከ1ኛ መደብ ወደ
2ኛ መደብ ሲሆን ቀጣ ባልሆነ መልኩ ግን በመልእክትና በመሳሰሉት ከ1ኛ መደብ በ2ኛ መደ በኩል ሌ3ኛ መደብ ይተላለፋል።
በልዋ ለእምየ ንኢ ኀቤየ
እኔ እናንተን “እናቴን እንድታዝዟት አዘዝኳችሁ
እንዲሁም ከ3ኛ መደብ በ1ኛ መደብ በኩል ለ2ኛ መደብ ይደርሳል።
“ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለእለ ይትለአኩ”
ምልዕዎንኬ ለእላ መሳብክት ማየ”
ምሳሌ፡ለቀጥታ ትዕዛዝ ከ1ኛ መደብ ለ2ኛ መደብ
እኔ አንደኛ መደብ ነኝ፤
እናንተ ደግሞ 2ኛ መደብ ናችሁ፡
አጽምኡ ዘእቤለክሙ
(አኃውየ ወአኃትየ!)
ምሳሌ 2፡ ቀጥታ ያልሆነ እና በታሪክ መልክ ከ1ኛ
መደብ ለ2ኛ መደብ የሚነገር ትእዛዝ፡
ቀጥታ ላልሆነ ትእዛዝ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ያለው ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ለሠርግ አሳላፊዎች የተሰጠው ትእዛዝ ነው።
1.
ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለእለ ይትለአኩ
2. “ምልዕዎንኬ ለእላ መሳብክት ማየ”
አንደኛውን ዐረፍተ ነገር የተናገረው ወንጌላዊው
ነው
ሁለተኛውን ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ነው።
ይህ ትእዛዝ በወቅቱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በሥዕሉ ላይ እንደምታዩት በቀጥታ ያስተላለፈው ወይም የሰጠው ትእዛዝ
ነው።
በኋላ ግን ወንጌላዊው በታሪክ መልክ “አላቸው” በማለት በሓላፊ ግሥ
ነገረን።
ስለ ትእዛዝ አንቀጽ በሰፊው ማወቅ ከፈለጋችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን የምትሄዱ ሰዎች የቅዳሴውን ጸሎት በትኩረት ተከታተሉ።፡በተለይ
ዲያቆናቱ የሚያስተላልፉ ወይም የሚናገሩት የጸሎት ክፍል የሚተላለፈው ቢያንስ 98 ከመቶው በትእዛዝ መልክ ነው።
ትእዛዝ አንቀጽ በሆሄያትና በድምጽ ወይም በአነጋገር
በንባብ ከዘንድ አንቀጽ ጋር ብዙ ጊዜ ተመሳሳይ ነው። መለየት የምንችለው
ከግሥ እርባታ ውስጥ ከሆነ “ትእዛዝ አንቀጽ” የሚገነው መጨረሻ ላይ ንው፤
በሥነ ጽሁፍ ውስጥ ከሆነ ግን መለየት የምንችለው
በትርጉሙ ብቻ ነው።
Friday, September 25, 2015
Thursday, September 10, 2015
Monday, August 31, 2015
Tuesday, August 11, 2015
ግእዝ ክፍል 17
Part 17 inside The paradise
እግዚአብሔር፣ አዳም፤ ሔዋን፤ እና እባብ
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአዳም፡
“.. አይቴ ሀሎከ አዳም.. ?
ይቤሎ አዳም ለእግዚአብሔር
“.. ሰማዕኩ ቃለከ እንዘ ታንሶሱ ውስተ ገነት ወፈራህኩ እስመ ዕራቅየ አነ ወተኀባእኩ.. ”
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአዳም፡
“.. መኑ አይድዐከ ከመ ዕራቅከ አንተ እም ዕፅኑ ዘአዘዝኩከ ከመ ኢትብላዕ እምኔሁ በላእከ?.. ”
ይቤሎ አዳም ለእግዚአብሔር
“.. ብዕሲት እንተ ወሀብከኒ ምስሌየ ትንበር ይእቲ ወሀበተኒ ወበላእኩ-”
ይቤላ እግዚአብሔር ለብእሲት(ሔዋን)
“.. ለምንት ገበርኪ ዘንተ?.. ”
ትቤሎ ብእሲት፡ ለእግዚአብሔር
“.. አርዌ ምድር አስፈጠተኒ ወበላእኩ.. ”
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአርዌ ምድር
“.. እስመ ገበርኮ ለዝንቱ ግብር ርጉመ ኩን እምኵሉ እንስሳ ወእምኵሉ አራዊተ ምድር ወበ እንግድዓከ ሑር ወመሬተ ብላዕ..”
ይቤላ እግዚአብሔር ለብእሲት(ሔዋን)
“.. (ብዙኃ) አብዝኆ አበዝኆ ለኀዘንኪ ወለሥቃይኪ ወበጻዕር ለዲ..”
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአዳም፡
“.. እስመ ሰማዕከ ቃለ ብእሲትከ ወበላዕከ እም ውእቱ ዕፅ ባሕቲቱ ዘአዘዝኩከ ከመ ኢትብላዕ ርግምተ ትኩን ምድር…”
Subscribe to:
Posts (Atom)


